Tuesday, 22 October 2024

ትምህርት ሚኒስቴር (የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ) ባሳለፍነው አርብ መስከረም 24 ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች (ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) የተማሪዎችን ምደባ ይፋ አድርጓል። እንደ ምንጊዜውም ሁሉ ለአንዳንዶች ሲመደብላቸው ለሌሎች ደግሞ ተመድቦባቸዋል። እንደእውነታው ከሆነ ብዝሃው ወደሚፈልግበት ቦታ አይደለም የሚሸኘው። ከዚህ መነሻ ብዙ ክርስቲያን ተማሪዎችም ግር ሲሰኙ እና በተመደቡበት ዩኚቨርሲቲ ለመማር እና ላለመማር ፣ ለመሄድ እና ላለመሄድ እንዲሁም ለመቀየር እና ላለመቀየር ሲያመነቱ ይታያል። ይህ የሚጠበቅ ስሜት ሲሆን እዚህ ላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ሃሳብ እና ፈቃድ ምን ሊሆን እንደሚችል እንዲጠይቁ ማበረታታቱ መልካም ነው።

Posted On %PM, %05 %780 %2018 %20:%Oct Written by

"ይሄ ደሞ ምንድን ነው?" አልኩት በእጄ የሆራ አርሰዲ ዙሪያ ረግረጉን ይዞ የበቀለውን ሳር ቀንጥሼ ውሃው ውስጥ እየነከርኩ። ስለማደርገው ነገር ምንም አልገባኝም። ነገር ግን ይህንን ስርዓት በመፈጸም ከብዙ ሺህ ሰዎች ጋር ተቀላቅያለሁ። ከብዙ ሺህ ሰዎች መካከል ደግሞ ይህንን ስርዓት ከልቡ የሚያከብር ወላጅ አባቴ አለ። አይን አይኔን እያየ ጥያቄዬን ካደመጠ በኋላ "ይህ በኦሮሞ ባህል መሰረት ለምድራችን ለምነት ፈጣሪን የምንማጸንበት ስርአት ነው። ውሃውና ሳሩ የሚወክሉትም ይህንን ነው። ከዚህም በላይ በአባቶች ጸሎት የተመረቀ ውሃ ነው። ለእኛ እንደጸበል ነው" አለኝ።

Posted On %PM, %29 %870 %2018 %22:%Sep Written by

ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል!

ክፍል 3 - ከፖርኖግራፊ ሱስ እንዴት መውጣት ይቻላል?

በዚህ ተከታታይ ፅሁፍ የመጀመሪያ ክፍል ላይ ‘ፖርኖግራፊ’ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከፍተኛ አቅም እንዳለው፣ በሁለተኛው ደግሞ የሱሰኝነቱን ምልክቶች /Symptoms/ አይተናል።በዚህ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ እንዴት ከዚህ ሱስ እንዴት መውጣት እንደምንችል እናያለን።

Posted On %PM, %04 %794 %2018 %21:%Jul Written by

ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል!

ክፍል ሁለት - የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ

በቀደመው ክፍል ላይ ‘ፖርኖግራፊ’ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከፍተኛ አቅም እንዳለው አይተናል። ለዛሬ ደግሞ የሱሰኝነቱን ምልክቶች /Symptoms/ እናያለን።

Posted On %PM, %27 %750 %2018 %20:%Jun Written by

ከፓርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል!

ክፍል አንድ - ፖርኖግራፊ ምንድን ነው? 

በአንድ ወቅት ‘ጉግል’ አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሐገራት መካከል እናንተ ኢትዮጵያውያን ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር። ይህ የሚያሳየን በሐገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው የፖርኖግራፊ ተጠቃሚ  ወይም በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ መሆኑን ነው። ይህ ሱስ እንደሌሎች ሱሶች በግልጽ በሱሰኛው ላይ የማይታይ በመሆኑ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት በቂ መረጃ ስለሌለ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል። 

Posted On %AM, %20 %048 %2018 %03:%Jun Written by

እናትነትን ለመግለፅ አንድ ቃል መምረጥ ቢኖርብኝ “መለወጥ” የሚለውን ቃል እመርጣለሁ።

ስራ የበዛባት እናት እያንዳንዱ ቀኗ ቢታይ ብዙ ስራዎችን ትሰራለች። በዘወትር ቀኗም ውስጥ የምታደርገውን ነገሮች እንዳለ ብናይ ነገሮችን የመለወጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች  እናያለን፤ የቆሸሹትን ልጆቿን አጥባ ማንፃት ፣ ሲርባቸው መመገብ፣ ሲደክማቸው ማስተኛት፣  የተዘበራረቀውን ማስተካከል፣ የቆሸሹትን ልብሶች ማጠብ፣ የከፋቸውን ልጆች ማጫወትና ባዶ የሆነውን መሶብ መሙላት፣ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። እኛም ሁልጊዜ የተዘባረቀን ነገር፤ ረሀብ እና ስርዓት አልበኝነትን ስንዋጋ እንውላለን አንዳንዴም ይሳካልናል። ኋላም ቀን መሽቶ ቀን ሲተካም ሁሉ ነገር ይገለጥና በማለዳ ይህንኑ የለውጥ ሂደቱን እንቀጥላለን።

Posted On %PM, %13 %637 %2018 %17:%May Written by

በ9ኛው ክፍለ ዘመን የሰራተኛው መደብ የቀን የስራ ሰዓትን ስምንት ሰዓት ለማድረግ ትግል ያደርጉ ነበር። ለዚህም ምክንያት የሆናቸው በቀን አስር ብሎም አስራ-ስድስት ሰዓታትን ያለዕረፍት መስራታቸው፤ ብሎም ደህንነታቸውን ባልተጠበቀ መልኩ የነበረ መሆኑ እና ለብዙዎች ህልፈትና ጉዳት ምክንያትም የነበረ በመሆኑ ጭምር ነበር።በዚህም ወቅት የሶሻሊዝም ርዕዮት አዲስና በሰራተኛው መደብም ቀልብን ሳቢ ሆኖ የነበረበትም ወቅት ለመሆን ችሏል።ይህንንም (የሶሻሊዝም) ርዕዮት የሰራተኛው መደብ የበለጠ በማናፈስ ከካፒታሊዝም ርዕዮት የመውጣትና የሰራተኛውን መደብ ገዢነት የማረጋገጥ ፍላጎቱን መጠቀሚያ አረገው።በዚህም ትግል ከተቀዳጁት ቀደምት ድሎቻቸው መካከል እ.ኤ.አ በ1884 በሀገረ አሜሪካ በቺካጎ ግዛት ብሄራዊ ስብሰባ ላይ በህገ-መንግስቱ ላይ የቀን የስራ ሰዓትን ስምንት ሰዓት አድርጎ በ ሜይ 1 ታወጀ።

Posted On %AM, %01 %360 %2018 %10:%May Written by

‹‹እላችኋለሁም ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሃቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግስተ ሰማያት ይቀመጣሉ።›› ማቴ 8፡10-11

Posted On %PM, %24 %799 %2018 %21:%Apr Written by
“እጆቼን እና እግሮቼን ተመልከቱ፡እኔው ራሴ ነኝ ደግሞም ንኩኝ እና እዩ ይህንንም ብሎ እጆቹን እና እግሮቹን አሳያቸው” ሉቃ 24፡39
Posted On %AM, %08 %916 %2018 %00:%Apr Written by

አሁን ሃገራችን ስላለችበት ሁኔታ ሳስብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የኖረበት ዘመን (የመጀመርያው ክፍለዘመን) ላደገበት የአይሁድ ማህበረሰብ የመረጋጋት እና የሰላም ጊዜ አልነበረም። አይሁዶች በሮም ተገዝተው የነበረበት፣ በዚህም ምክንያት ከዚህ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት እየታገሉ የነበረበት ጊዜ ነበር። በዚህም ምክንያት አይሁድ ራሳቸው በዚህ ሃሳብ ተከፋፍለው ነበር። ቀናተኛዎቹ (“Zealots”) የተባሉት የአይሁድ ክንፍ በጦርነት ትግል ሮምን ለመጣል የተነሱ እና ሽምቅ ውጊያ የሚያደርጉ ነበሩ። ፈሪሳውያኑ ደግሞ ሁሉን “አስማምተው” ለመኖር የሚሞክሩ ነበሩ። እንዲሁም ከማህበረሰቡ ተገልለው በበረሃ የሚኖሩ (የመነኑ) የአይሁድ ሰዎችም ነበሩ።

Posted On %PM, %14 %806 %2018 %21:%Mar Written by
Page 1 of 8

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ

የሰው ህይወት በምድር ላይ ብዙ ሰልፍ፣ ብዙ መከራ፣ ብዙ ፈተና እንዳለበት የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። የመከራውም ሆነ የፈተናው ዓይነት ብዛቱም ሆነ ዐይነቱ ...

Eyob B Kassa - avatar Eyob B Kassa

ጨርሰው ያንብቡ

መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ አራት ጸሎቶች

መጽሐፍ ቅዱሳችንን ልናነብብ ስንከፍት ለብቻችንን አይደለንም ። መንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ ክብር ሲል ልባችንን ሊያነሳሳ አዕምሮአችንን ሊያበራ ሕይወታችንን ሊቀይ...

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.