Tuesday, 22 October 2024

ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።

በሩጫ ውድድር የሚሮጡ ብዙዎች እንደሆኑ፣ ሽልማቱን የሚቀበለው ግን አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁምን? ስለዚህ ሽልማቱን እንደሚቀበል ሰው ሩጡ። ለውድድር የሚዘጋጅ ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል።

በመልካም መሬት ላይ የወደቀውም ቃሉን ቅንና በጎ በሆነ ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፣ ታግሠውም በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።

ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ …እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።

ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው። ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።

ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፥ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው? 

እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፥ነገሬንም ወደ እግዚአብሔር አቀርብ ነበር። የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል።

ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።

እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኁሩኆችና ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ ብክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።

እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። 

Download More Wallpapers

የያዕቆብ መልእክት 1:19

ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤

Download

የዮሐንስ ወንጌል 6:68

ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤

Download

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:15

በቃላት ሊገለጥ ስለማይቻል ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ።

Download

መጽሐፈ ምሳሌ 10:28

የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤የኀጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል። 

Download

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:14-15

ማንኛውንም ነገር ሳታጉረመርሙና ሳትከራከሩ አድርጉ፤ ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንፁሕና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ...

Download

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:13

ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሱም ዘንድ...

Download

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.