Tuesday, 19 March 2024

መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ አራት ጸሎቶች

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by
መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ አራት ጸሎቶች Daily Injera

መጽሐፍ ቅዱሳችንን ልናነብብ ስንከፍት ለብቻችንን አይደለንም ። መንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ ክብር ሲል ልባችንን ሊያነሳሳ አዕምሮአችንን ሊያበራ ሕይወታችንን ሊቀይስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሰፍፎ አለ (ዮሐንስ 16፡14) ። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ዋነኛው መስፈርት መንፈስ ቅዱስ ነው ። ተራ የሚመስልን ነገር ወደ ኃያል ነገር ይቀይረዋል ። ስለዚህም ለዓይኖቻችን ለአዕምኖአችን እና ለልባችን ሳንጸልይ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ ሞኝነት ይሆንብናል ።

ፀሎት ንግግር ነው ። ይሁን እንጂ እኛ የምንጀምረው አይደለም ። እግዚአብሔር ነው መጀመሪያ የሚናገረው ። ድምፁ በመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ደግሞ በክርስቶስ ስራ እና ማንነት ውስጥ ጎልቶ ይደመጣል ። እናም በሚደንቅ ሁኔታ እኛን ሊሰማን ቆም ይላል ጆሮውን ወደእኛ ያዘነብላል ። ፀሎት አቅሙ ማመን ከሚያቅተን በላይ ነው ። የእኛ ዓይኖች በቃሉ ላይ ሆነው እርሱም ጆሮውን ያዘነብልልናል ።

ታዲያ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ለማንበብ እንዴት መጸለይ አለብን? የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብ ስትከፍቱ እነዚህ አራት ጥቅሶች ልትጸልዩ ትችላላችሁ ። 

1. መዝሙር 119፡18 “ለተአምራቶችህ ዓይኖቼን ክፈት

ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተአምራትህን አያለሁ” (መዝሙር 119፡18) ። በእራሳችን ልናየው የማንችለውን የክብሩን ውልብታ ያሳየን ዘንድ  ዓይኖቻችንን እንዲከፍትልን እግዚአብሔርን እንጠይቀዋለን ። ያለ እርሱ እርዳታ ተፈጥሮአዊ አይን ያላቸው ተፈጥሮአዊ ሰዎች ብቻ ነው የምንሆነው ። “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም” (1 ቆሮንቶስ 2፡14-15) ።

በማቴዎስ ወንጌል 13፡13 ላይ “እያዩ ስለማያዩ” የሚሉትን ቃላት ኢየሱስ የተጠቀመው እርሱን እና ትምህርቱን በተፈጥሮአዊ አይኖቻቸው ብቻ ለሚያዩ ያለ መንፈስ ቅዱስ የማንቃት ስራ ላሉት ነበር ። ለዚህም ነው ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ሲጸልይ “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው” (ኤፌሶን 1፡17-18) የሚለው ።

ልክ እንደ መዝሙረኛው ለመንፈሳዊ እይታ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተዓምራቶችን ማየት እንድትችሉ ጸልዩ ። ተዓምር ለመቅበዝበዝ ትልቅ መድኃኒት ነው ። በእግዚአብሔር መደነቅን የሚያሳድጉ ልባቸውን ከፈተና እና ከመቀዝቀዝ ይጠብቃሉ ። 

2. ሉቃስ 18፡38 “ማረኝ

በመንገድ ዳር ላይ ሆኖ “የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ” እያለ እንደለመነው እንደ ዕውሩ ሰው ጸልዩ። ኃጢያት በዚህ ምድር ላይ እስካለን ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር በቃሉ የሚኖረንን ግንኙነት ይገዳደራል ። በየዕለቱ ቤተሰቦቻችንን እና ጓደኞቻችንን ከማንም በላይ ደግሞ እግዚአብሔርን እናሳዝናለን ። ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችንን “እግዚአብሔር ሆይ ለእኔ ለኃጢያተኛው ይቅርታ አድርግልኝ!” (ሉቃስ 18፡13) በሚል ፀሎት መጀመር የሚገባ ነው ።

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ በየዕለቱ ለሚገጥሙን ውድቀቶች ማሸነፊያ፣ እንደ አዲስ ንሰሀ መግቢያ እና እራሳችንን መልሰን ጸጋው ውስጥ የምንጨምርበት መንገድ ነው ። ፀሎት ደግሞ በጸጋው መደነቅ እንድንቀጥል የሚያደርግ እውነተኛ ትህትናን የምናሳድግበት መንንድ ነው ።

3. ያዕቆብ 1፡22 “ቃልህን አድራጊ እንድሆን አድርገኝ

እግዚአብሔር ዓይናችሁን ከከፈተላችሁ ጸጋው ብቻ በቂ እንደሆነ ካስታወሳችሁ፤ በሕይወታችሁ ደግሞ እውነተኛ ለውጥ እንዲያመጣ ጸልዩ ። የቃሉ ዘር እውነተኛ እና በሚታይ መልኩ ተጨባጭ የሆነ ለሌሎች መስዋዕታዊ ፍቅርን የሚያደርግ ሥራ እንዲያፈራ ጸልዩ ። “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ” (ያዕቆብ 1፡22) ። ሰው ሰራሽ በሆነ መልኩ ከእያንዳንዱ ጥቅስ የትግበራ ነጥቦችን ፍለጋ ላይ ማተኮር የለባችሁም ነገር ግን ቃሉ ተግባራዊ ኑሮአችሁን እንዲመራ እና እንዲቀርፅ ጸልዩ ። 

ቃሉን በማንበብ እና በማጥናት ከወሰዳችሁት ጊዜ የተነሳ የበለጠ መውደድ የምትችሉ እንዲያደርጋችሁ ጸልዩ።

4. ሉቃስ 24፡45 “ዓይኖቼ ኢየሱስን እንዲያዩ ክፈት

እግዚአብሄር ዓይኖቻችንን ለተአምራቶቹ እንዲከፍት የምንጸልይበት ሌላ መንገድ ይህ ነው። የእግዚአብሔር ሥራዎች እንደ ተራራ ክምር ሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፤ ነገር ግን ከፍተኛው ቦታ እና አስደናቂ መገለጥ የልጁ ማንነት እና ሥራ ነው።

ከትንሳኤው በኋለ እራሱ ኢየሱስ እንዳስተማረው ለእያንዳንዱ ቃል ፣ ለእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፈት እና ለእያንዳንዱ ታሪክ ቅርብ የሆነ መፍቻ ቁልፉ እርሱ እንደሆነ ነው። መጀመሪያ “ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው” (ሉቃስ 24፡2)። ቀጥሎም “ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው” (ሉቃስ 24፡44)። እንዲህም በማድረጉ “መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው” (ሉቃስ 24፡45)።

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እና ጥናት ዋነኛ አላማው ኢየሱስን ማየት እና በእርሱ መደሰት ነው። ስለሚመጣው የመንግስተ ሰማይ ደስታ በምድር ያለው ጣዕሙ ይህ ነው። “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” (ዮሐንስ 17፡3)። እንዲህ መሆኑ ለጥናታችን አቅጣጫ ፣ ትኩረት እና አላማ ይሰጠዋል። “እንወቅ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ እንደ ዝናብም ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ መጨረሻ ዝናብ ይመጣል” (ሆሴዕ 6፡3)። “ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ዕውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ” (ፊልጵስዩስ 3፡8) ይሄ በነፍሳችን ውስጥ ታላቅ ናፍቆት እና ስሜትን ይፈጥራል።

ሁለቱንም ዓይኖቻችሁን ለኢየሱስ ክፍት አድርጉ። የምናነብበው ክፍል ከኢየሱስ እና ሥራው ጋር ያለውን ግንኙነት እስካላየን ድረስ የንባባችንን ዋነኛ ክፍል ገና አልፈፀምንም። 

ለማየት እንችል ዘንድ የእግዚአብሔር የማያቋርጥ እርዳታ ያስፈልገናል፤ ስለዚህም ምክንያት እንፀልያለን።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %823 %2016 %21:%Dec
David Mathis

David Mathis is executive editor for desiringGod.org, pastor at Cities Church in Minneapolis/Saint Paul, and adjunct professor for Bethlehem College & Seminary. He is author of Habits of Grace: Enjoying Jesus through the Spiritual Disciplines.

https://twitter.com/davidcmathis

እናትነት ትልቅ ኃላፊነት ነው

እናትነትን ለመግለፅ አንድ ቃል መምረጥ ቢኖርብኝ “መለወጥ” የሚለውን ቃል እመርጣለሁ። ስራ የበዛባት እናት እያንዳንዱ ቀኗ ቢታይ ብዙ ስራዎችን ትሰራለች። በ...

Rachel Jankovic - avatar Rachel Jankovic

ጨርሰው ያንብቡ

ምስጋና ለመስጠት 32 ምክንያቶች

እንግሊዛዊው ፓስተር እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ማቲው ሄነሪ (1662-1714) ከመሞቱ 2 ዓመት በፊት ስለ ጸሎት መጽሐፍ ጽፎ ነበር። ለጸሎት የሚሆን መንገድ...

Donny Friederichsen - avatar Donny Friederichsen

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.