Tuesday, 19 March 2024

ጽናት - ከሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻ የምድር ላይ ጊዜያት የምንወስደው ትምህርት


‹አንተ ግን … ጽናቴን ሁሉ ታውቃለህ› 2ኛ ጢሞ 3፡10

የሐዋርያው ጳውሎስ የዕለት ተዕለት ሕይወት እና አገልግሎት በከባድ ኩነቶች የተሞላ ነበር። ይበልጥ ደግሞ በአገልግሎቱ የመጨረሻ ጊዜያት ማለትም በሁለተኛው የሮሜ እስራቱ ወቅት ሕይወቱ እና አገልግሎቱ እጅግ ፈታኝ እና እጅግ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ነበር። ሐዋርያው በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት በጽናት እምነቱን ጠብቆ ሩጫውን የፈጸመ ታላቅ የእምነት አርበኛ ነው። በቀጣዮቹ ስምንት ቀናት ከሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻ ቀናት ገጠመኞች ውስጥ በጽናት ስላለፋቸው ተግዳሮቶች የሐዋርያውን የመጨረሻ ደብዳቤ የሆነውን 2ኛ ጢሞቴዎስ መልዕክትን ተንተርሰን እንማራለን። በዚህም ለእግዚአብሔር መንግስት በሚኖረን አገልግሎት እንዲሁም በዕለት-ተዕለት የክርስትና ጉዟችን የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች በጽናት ለማለፍ አቅም እንደምናገኝ እምነቴ ነው።

ጳውሎስን ከጎኑ ቆሞ ያበረታ እና ያጸና አምላክ (ሐዋ 23፡11) እኛንም ያበርታን ደግም ያጽናን! አሜን

Naol Befkadu

Naol Befkadu Kebede (BTh, student of MA in Ministry and Medical Doctorate student at AAU) is the founder and contributor of Lechristian Blog, an online ministry that aims to redeem cultures for the glory of God and to inspire and encourage believers for the completion Great Commission. Naol has authored an Amharic book titled "ተነሺ ፤ አብሪ" (2015) that motivates young believers for a meaningful and radical life.

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.