ሁልጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደማደርገው በሰው ልጆች ታሪክ ሁሉ ውስጥ ከታተሙት መጽሐፍት ታላቅ ከሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ባለኝ አመታዊ የንባብ ጉዞዬ ዘፍጥረትን በማንበብ ላይ ነኝ ። አሁን አስራ አምስተኛ አመቴ ላይ ነኝ ። ሙሉ የጎልማሳ ሕይወቴን መጽሐፍ ቅዱስን ሳነብ እና ሳጠና ስላሳለፍኩ ወደጠለቀው ደረጃ የደረስኩ ይሰማኛል ። ምናልባት እራሴን እየካብኩ ነው ።
ሁላችንም ማን እንደሆንን ማወቅ እንፈልጋለን። እራሳችንን ፈልገን ለማግኘት እንጥራለን። ብዙዎቻችን የስብዕና ፈተናዎችን እና ሌላም ግምገማዎችን ወስደናል።
ይሁንና እነዚህ ፈተናዎች ጠቃሚዎች ሆነው ሳሉ፤ ቆም ብላችሁ ግን “እግዚአብሔር እኔ ምን እንደሆንኩ ያስባል?” “እኔ ማን እንደሆንኩ ይላል?” ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቸር አምላክ እንደሆነ ይናገራል። ብዙ ሰዎች ግን ይህንን ለማመን ይቸገራሉ። አንዳንዶች ጸጋ ምን እንደሚመስል ሲያስቡ ይገረማሉ። የእግዚአብሔርን ጽድቅና የእኛን የየዕለት አስከፊ ኃጢያት በጥልቀት ብናስብ እግዚአብሔርን “አሁንም ትወደኛለህ ወይ?” ወይንም “ለምንድን ነው እንደዚህ የታገስከኝ?” ወይንም “ስላደረግሁት ነገር ስለምን አልገደልከኝም?” ብለን ስንጠይቅ እራሳችንን ልናገኘው እንችላለን።
እግዚአብሔር ህዝቡን በፍቃዱ ውስጥ ሊመራባቸው የሚችላቸው ቢያንስ አራት መንገዶች ይታዩኛል።
ያጣችሁት ነገር ላይ ዓይንን እንደመጣል እምነትን የሚያደክም ነገር የለም።
እንደተረዳሁት ከሆነ ዓይኖቼን በቁሳዊ ማጣቶቼ ላይ ፣ በሌሉኝ ጥንካሬዎች እና በሌሉኝ ድክመቶች ላይ ባደረግሁ ጊዜ ያለማመን ሸክም ይከብድብኝና ሩጫዬን ከባድ ያደርግብኛል (ዕብራዊያን 12፡1)።
ስለግል የፀሎት ጊዜያችሁ መለስ ብላችሁ የምታዩበት እና በመጪዎቹ ቀናት አንድ ወይንም ሁለት ነገሮችን ለማስተካከል የምታልሙበት ጊዜ አሁን ነው። በተለምዶ ለማደግ እና ረዘም ያለ መንገድን ለማቅናት የተሻለ የሚባለው አማራጭ አጠቃላይ እድሳት ሳይሆን አንድ ወይንም ሁለት የተወሰኑ ችግሮችን ለይቶ ማውጣቱ ነው።
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል (ሮሜ 5፡8)።
“እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ" (ይሁዳ 20-21)።
የእግዚአብሔርን ሞራላዊ (ግብረ ገባዊ) እና ሉአላዊ ፍቃዶች መለየት እንድትችሉ ልረዳችሁ እፈልጋለሁ። ቀጥሎ ባሉት ሁለት ሃሳቦች መሀከል ያለውን ተቃርኖ መረዳት እንድትችሉ ይረዳችኋል።
የዚህን መልስ ማወቅ ሁላችንም እንፈልጋለን አይደል? ከዚህ በላይ ውጥረትን ሊፈጥር የሚችል ርዕስ ሊኖር ይችላል? ስለፈጠረን ፣ ደግሞም በሕይወት እያቆየን ስላለው ፣ ሊያድነን ልጁን ስለሰጠን ስለ ስለ ሉአላዊው እግዚአብሔር እያወራን ነው። በሰጠን እንፋሎት በሆነች በዚህች ሕይወት ውስጥ ምን እንድናርግለት ይፈልጋል?
Daily Injera is a Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible each day.
The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.