እነዚህ ትንንሽ የለውጥ ሂደቶች ተደምረው ትልቅ ለውጦችን ይፈጥራሉ። የሚጠባ ህፃን አድጎ መራመድ ይጀምራል፣ ሊነሳ ሲል ይጋጭ የነበረ ህፃን አድጎ ድክ ድክ ማለት ይጀምራል ፤ አለፍ ብሎም ወንድምና እህት ለመሆን ይበቃል።
በዚህ ጊዜ ደግሞ እኛም የምናልፍባቸው ለውጦች አሉ። ይህም እኛ ለዛ ለውጥ ስለሰራን ሳይሆን፣ ለዛ ስለተፈጠርን ነው። ምሳችሁን ስትበሉ፣ ሰውነታችሁ ለተረገዘው ልጅ ምግብ አድርጎ የበላችሁትን ይቀይረዋል። ለህፃኑ ቀጥታ ቢሰጥ ትልቅ ይሆንበት የነበረውን ነገር ለልጁ በመጠኑ ቀይሮ የሚያስፈልገውን ምግብ ይሰጠዋል። ይሄ ደግሞ ልጆች እራሳቸውን ለመመገብ ብቁ እንዲሆኑ አርጎ ማየትን ግብ ያረገ ነው።
እርግዝና እና ህፃናትን መንከባከብ ልጆችን የማሳደግ ትንሹ ክፍል ነው። ይህ ሂደት ደግሞ በሚታየው አለም ውስጥ ያለ ብቻ አይደለም። በመንፈሳዊው አለም ላይ ያለው ምግብ በይበልጥ አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን ስለዚህ ብዙ ጊዜ አይወራም። በክርስትና ያሉ እናቶች ያለማቋረጥ ልጆቻቸውን መመገብ አለባቸው - ስጋዊውንም መንፈሳዊውንም።
የምናደርገው የምናምነውን ነው
የምንበላውን ምግብ ሰውነታችን ወስዶ ካለእኛ ፍቃድ ህፃናት እንዲጠቀሙት እንደሚያደርግ ሁሉ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለወንጌል፣ ስለእምነትና ህይወት የምናምናቸውን ነገሮች ሁሉ ወስደን ትንሽ በሚመስሉ ነገሮች ሁሉ ላይ እንተገብራቸዋለን።
በኩሽና ውስጥ በጣም ለደከማቸውና ከግማሽ ሰአት በፊት መብላት ለነበረባቸው ህፃናት ምግብ ስታዘጋጁ እራሳችሁን አስቡት። ያላችሁ የመሰላችሁ ነገር ላይኖር ይችላል። ህፃናቶቹ እርስ በእርሳቸው ሊጣሉ ይችላሉ። ከሁሉም ትንሹ ህፃን እግራችሁ ላይ ቆሞ ያደረጋችሁትን ልብስ ሊጎትት ይችላል። እንደውም ያደረጋችሁትን ልብስ ሊያወልቀው ይሞክራል። ሞቋችኋል፣ ደክሟችኋል፣ ሰልችቶአችኋል።
በዚህ ሰአት ስለወንጌል ለመናገር ምንም ጊዜ አይኖራችሁም። ጊዜ የለም! ዕራት ለማዘጋጀት በብዙ እየደከማችሁ ነውና ስለወንጌል ለማውራት የሚመች ሁኔታ የለም። ይህ ወንጌልን መንገሪያ ጊዜ አይደለም፤ ምክንያቱም ይህ ወንጌልን መተግበሪያ ሰዓት ነው። እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠንን የተትረፈረፈ ፀጋ ወስደን ለልጆቻችንን የምናካፍልበት ስዓት ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ያሳየው ምህረት፣ ርህራሄ እና ሁሉን ቻይነት ወስደን ልጆቻችን በሚገባቸው መልኩ ለእነርሱ የምናፈስብት ሰዓት ነው። ነገር ግን እኛ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ አልተረጋጋንም ማለት ልክ ህፃናት ለወተት እንደሚያለቅሱት በዚህ ሁኔታ ውስጥም መንፈሳዊ ወተትን ተርበው እያለቀሱ ነው እንደማለት ነው። የሚያስፈልጋችው መንፈሳዊ ወተት ነው። እነሱ እንድትመግቧቸው ይፈልጋሉ፤ በቃላት ገለፃ ሳይሆን ወንጌልን በመተግበር።
የምትፈልጉት ሁሉ በእጃችሁ ነው
የእናትነት ስራ በጣም ከባድ ሁኔታዎች የሞሉበት ነው። ሱፐር ማርኬት ውስጥ እቃ እየገዛዛችሁ የልጆቻችሁ ዳይፐር ሊቆሽሽ ይችላል ወይ መኪና እየነዳችሁ ልጃችሁ ከኋላ ሊያስመልስ ይችላል። በእንደዚህ አይነት ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ የምታምኑትን መተግበር ያስፈልጋችኋል። መፅሀፍ ቅዱስ እግዚአብሄር የእኛ ድካም እንደሚያንገሸግሸው ይነግረናል እንዴ? የእኛንስ ሸክም መሸከም አይፈልግም እንዴ? ከእኛ ጋር ለመነጋገር አቅም ያጣል እንዴ?
መልካሙ ዜና ወንጌልን የምትተገብር እናት ለመሆን ልዩ ስልጠና መውሰድ አያስፈልግም። እግዚአብሔርን ልታምኚው፣ ልታመሰግኚው እና ልትደሰቺ ያስፈልጋል! ይህም እምነትሽ ለልጆችሽ ምግብ ይሆናል። በእግዚአብሔር ዕረፊ፣ ልጆችሽ ማረፍን ከአንቺ ይማራሉ። የእግዚአብሔር ርህራሄ ለራስሽና ለልጆችሽ አሳይ። እግዚአብሔር አንቺን ይቅር እንዳለ ሁሉ አንቺም ይቅር በያቸው። ክርስቶስ እስካለሽ ድረስ ልጆችሽን በመንፈሳዊ ምግብ ለመመገብ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ አለሽ።
ወንጌል በእሁድ ጠዋት ለቤተክርስትያን ለመሄድ ንፁህ ልብስ በመልበስ ስትዘገጃጁ ለልጆችሽ የምትነግሪያቸው ነገር ብቻ አይደለም።ወንጌል በጥሞና ሰአት የሚኖረን ጊዜም ብቻ የሚወሰን አይደለም። ወንጌል በከባድ ሁኔታዎች ለምሳሌ መኪና ውስጥ በመቀመጫው ላይ ልታስሪው ስትሞክሪ ለመጫወት የሚሞክረው እና አፍንጫው የቆሸሸበት ህፃት ጋር ስትታገይ የምትገብሪው ነገር ነው ።
ለእግዚአብሔር የምናልፍባቸው ሁኔታዎች ከባድ ሆነውበት አይደለም፤ ነገር ግን በሁኔታዎች ውስጥ ሊያስተምረን ሊያነፃን እና ሊያጠራን ይፈልጋል። እምነታችንን በተግባር ማየት ይፈልጋል። እሱ በሰጠን ፀጋ ልጆቻችንን ስንመግብ ማየት ይፈልጋል።
እግዚአብሔር በሰጠን ፀጋ ልጆቻችንን ስንመግብ ማየት ይፈልጋል።
ወንጌሉን ምሰሉ
በእርግጥ በዚህ ምድር ያለውን መንፈሳዊ ህይወት በፍፁምነት አናደርገውም፤ ከባድ ቃሎችን እንናገራለን፤ ትዕግስታችን ይመነምናል፤ ህይወት ያዛለን እናቶች ድካማችን መታየት ይጀምራል። ይህ ሲሆን ሀጢያታችን ከወንጌሉ አያርቀንም ይልቅስ ሁኔታዎቹ ወንጌሉ እንደሚያስፈልገን አጉልቶ ያሳየናል። እንዲያውም ለምን ወንጌሉ እንደሚያስፈልገን ገልጦ አሳየን። የራሳችሁን ጥፋቶች መጥፎ እናት ነኝ ብላችሁ እንድታጉረመርሙ ምክንያት አይሁናችሁ። ንሰሀ በመግባት፤ ምህረቱን በመፈለግ ነገሮችን በማስተካከል ተነሱና ኑሮአችሁን ቀጥሉ። በእምነት የሀጥያታችሁን ይቅርታ ተቀበሉ። ይህንንም ምህረት፣ እምነት እና ደስታ ለልጆቻችሁ አሳዩ።
በየቀኑ የምታልፉበት የለውጥ ሂደት ልባችሁን በቃሉ እውነት ላይ አሳርፉ። በምታደርጉት ነገር ሁሉ ወንጌልን ምሰሉ። ወደእናንተ የመጣውን ሰላምን፣ስርሃት፣ ደስታን አሳዪ። ለእናንተ እንዲሁ እንደተሰጣችሁ ሰጪዎች ሁኑ። ወንጌል በሕይወታችሁ ባሉ ትንንሽ በሚመስሉ ሁኔታዎች ለመተግበር አያንስም ይልቅስ ይበዛበታል እንጂ።