1. እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እንደ ፍቃዱ ያደርጋል (ሉአላዊ ፍቃድ)
በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል እጁንም የሚከለክላት ወይም ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም (ዳንኤል 4፡35)
አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው በሰማይም በምድርም የፈቀደውን ሁሉ አደረገ። (መዝሙር 115፡3)
2. አንዳንድ የእግዚአብሔር ፍቃዶች ያልሆኑ ግን ይፈጸማሉ (ግብረ ገባዊ ፍቃዶች)
“የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል” (1 ዮሐንስ 2፡17)። አንዳንዶች እንደማያደርጉት ያመላክታል።
“ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል” (2 ጴጥሮስ 3፡9) ነገር ግን የሚጠፉ እንዳሉ እናውቃለን።
በሌላ አገላለጽ መጽሐፍ ቅዱስ በምንም ሁኔታ ሊከለከል ስለማይችለው የእግዚአብሔር ፍቃድ፣ በመቀጠልም ደግሞ በተወሰነ መልኩ እንድንሄድ የሚያዝዙን በግብረ ገባዊ ትዕዛዞች የሚባሉ ሁለት ነገሮች እንዳሉ ግልጽ አድርጎ ያስቀምጣል።
በእግዚአብሔር ሉአላዊ ፍቃድ እና በ ግብረ ገባዊ ፍቃዱ መሀከል ያለው ልዩነት በግልጽ ከሚታዩበት ማስረጃ አንዱ እግዚአብሔር መግደልን መከልከሉ ነው።
“ንጹሕንና ጻድቅን አትግደል” (ዘጸአት 23፡7)።
ይሁን እንጂ የልጁን ሞት ሲፈቅድ ደግሞ እናያለን።
“በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ” (የሐዋርያት ሥራ 4፡27-28)
ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎች በምንገዛበት ጊዜ እግዚአብሔር ከምንቀበላቸው ዋነኛውና ቅዱሱ እውነት ውስጥ እግዚአብሔር ኃጢያት እንዲኖር ሲፈቅድ እርሱ ኃጢያትን እንዳልሰራ ነው። በመስቀል ላይ ያለው የእግዚአብሔር እቅድ እዚህ ላይ ስለተመሰረተ ይህ መሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው።
እግዚአብሔር መንገዱ እና ፍቃዱ ቅዱስ ናቸው። ሁሉም እንዲሆኑ በመወሰኑ ውስጥ ቅዱስ አላማ አለው።
“እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ . . .” (ኤፌሶን 1፡11)
“ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ፍርድ ነውና” (ዳንኤል 4፡37)
ለዚህ ምላሽ እናምልከው በፊቱም እንስገድ።
Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe