Tuesday, 19 March 2024

የእግዚአብሔር ጸጋ ከአዕምሮ በላይ ነው

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by
የእግዚአብሔር ጸጋ ከአዕምሮ በላይ ነው Daily Injera

መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቸር አምላክ እንደሆነ ይናገራል። ብዙ ሰዎች ግን ይህንን ለማመን ይቸገራሉ። አንዳንዶች ጸጋ ምን እንደሚመስል ሲያስቡ ይገረማሉ። የእግዚአብሔርን ጽድቅና የእኛን የየዕለት አስከፊ ኃጢያት በጥልቀት ብናስብ እግዚአብሔርን “አሁንም ትወደኛለህ ወይ?” ወይንም “ለምንድን ነው እንደዚህ የታገስከኝ?” ወይንም “ስላደረግሁት ነገር ስለምን አልገደልከኝም?” ብለን  ስንጠይቅ እራሳችንን ልናገኘው እንችላለን።

ለኃጢያት ያለን ጥላቻ እና ማስተዋል ሲጨምር ስለ እግዚአብሔር ጸጋ መጽሀፍ ቅዱሳዊ መልስ አጥብቀን እንፈልጋለን። እግዚአብሔር ማን እንደሆነ እና በክርስቶስ ኢየሱስ ምን ያህል እንሚወደን መጽሀፍ ቅዱስ ግልጽ ምስል እንዲስልልን ያስፈልገናል። በምህረቱ ከአዕምሮ በላይ ባለጸጋ ወደሆነው ወደ የመጽሀፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ልንመለከትና ወደ ንስሃ ልንመጣ ያስፈልጋል። 

ስለ እግዚአብሔር ያለን አመለካከት

በሚክያስ 6:6-7 እስራኤላውያን ስለ እግዚአብሔር የተዛባ አመለካከት እንዳላቸው እናያለን። ከአንድ እስከ አምስት ባሉት ምዕራፎች ላይ “ምን አደረግኋችሁ?” የሚል የፍቅር ወቀሳ ያቀርብላቸውና ከግብፅ እጅ እንዴት እንዳወጣቸው በእነርሱም ስም ያደረገላቸውን ሌላ የጽድቅ ሥራዎች ያስታውሳቸዋል። 

ከቁጥር 6-7 የሚመልሱት መልስ ግን እጅጉኑ የሚያስገርም ይሁን እንጂ በሚያም ሁኔታ የተለመደ ነው። 

"ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?"

በምስጋና ከመመለስ ይልቅ እራሳቸውን ያጋልጣሉ። አስበውበት ይሁን ሳያውቁ እግዚአብሔርን ከእነርሱ ብዙ የሚጠብቅ፤ ጨካኝ እና ለማስደሰት የሚከብድ አድርገው ስለውታል። ንግግሩ ግልጽ አይደለም። ተናጋሪው የእውነት ንሰሃ ለመግባት እየሞከረ ነው ብለን ልናስብ እንችላለን ወይንም ደግሞ ተናጋሪው ተቆጥቷል ብለንም ልናስብ እንችላለን። ስለእግዚአብሔር ያላቸው እይታ ከእውነታው ጋር አብረው አይሄድም።

ኮሌጅ እያለሁ ከአንድ ውድ ጓደኛዬ ጋር ኃጢያታችንን እየተናዘዝን እየጸለይን ነበር። በመናዘዝ እና ጸሎት ጊዜአችን ላይ ስለ እግዚአብሔር ተመሳሳይ የሆነ ምስል እንዳለን ተረዳን። ሁለታችንም እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ እንደገና ኃጢያት ስለሰራን የተናደደ ቁጡ አባት አድርገን ነበር ምናየው። የሳልነው እግዚአብሔር ትዕግስት የሌለው፤ ቁጡ አና በእኛም ያዘነ አይነት ነበር። የሰማዩ አባታችን በማይታዘዙት ልጆቹ ምክንያት በቋሚ ሀዘን ውስጥ እንደሚኖር ነበር የሚሰማኝ። ሚኪያስ 6፡6-7ን በቅርቡ ሳነበው የእስራኤለውያንን ስሜት መረዳት እችል ነበር።

የእግዚአብሔር ጸጋ እንደሰው ጸጋ አይደለም

በተወሰነ መልኩ የእግዚአብሔርን ጸጋ የምንመለከትበት መንገድ እርስ በእርስ ካሉን ግንኙነቶች የመነጨ ነው። ወላጆች፣ ዘመዶች ወይንም በአጠቃላይ ስለ ሰው ልጆች ያለን አመለካከት ይሁን ከኃጢያተኛ ሰዎች ጋር የሚኖረን ቆይታ ቅዱስ እና ጻድቅ ስለሆነው እግዚአብሔር ያለን አመለካከት ላይ ተፅእኖ ያመጣል። በኃጢያት ያልተበረዘ የጸጋ፣ የምህረት እና የእውነት ዕውቀት የለንም። በሰውኛ አነጋገር ምንም ጸጋን ተለማምደን ብናውቅ ጸጋን ግን ሙሉ በሙሉ የለበሰ ሰው ግን አግኝተን አናውቅም።

ፍቅር እና ጸጋን ለሌሎች ስለማሳየት ሳስብ ሰዎችን ይቅር ለማለት ስላለን መነሳሳት ሁለት ነጥቦች ታሰቡኝ፡-

• ተፈጥሮአዊ ሰው ይቅር የሚለው እርሱም ይቅርታ እንዳስፈለገው ሰው ጥፋተኛ እንደሆነ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ስለሚያውቅ ነው።

• ተፈጥሮአዊ ሰው ሌሎችን ይቅር የሚለው ይቅርታ የሚደረግለትን ሰው ጥፋት በጥቂቱ ብቻ ስለሚያውቅ ነው። 

ይቅር ለማለት ሌላም ሰውኛ መነሳሳቶች እንዳሉን አስባለሁ። ነገር ግን ከነዚህ ሁለት ምክንያቶች ውጪ ይቅር የማለት አቅማችን ላይ ተፅዕኖ በማሳደር ታላቅ ሚና የሚጫወቱ ሁለት ምክኒያቶች አሉ እነሱም ኃጢያታችን እና ቸልተኛነታችን ናቸው።

ከአዕምሮ በላይ የሆነ ጸጋ

ስለዚህ ማሰብ ስጀምር ከአዕምሮዬ በላይ ነው የሆነብኝ። እግዚአብሔር በእራሱ ኃጢያትን አያበረታታም እንዲሁም በቸልተኝነቱ ብቁ አይሆንም። እርሱ ሙሉ በሙሉ ከኃጢአት የነፃ በመልካምነት እና ፍቅር የተሞላ ቅዱስ እና ጻድቅ አምላክ ነው። ምንም ስህተት ሰርቶ አያውቅም፤ ነገር ተበላሽቶበትም እንዲሁ። በመንገዱ ሁሉ ፍፁም ነው። ሃኪም ቢሆን ኖሮ የማይድን ታካሚ አይኖረውም ነበር። ጠበቃ ቢሆን የማያሸንፈው ክርክር አይኖም ነበር። ቅን እና ያለነቀፋ የመሆኑን ልክ የሚለካ ሚዛን የለም።


እርሱ ሙሉ በሙሉ ከኃጢአት የነፃ በመልካምነት እና ፍቅር የተሞላ ቅዱስ እና ጻድቅ አምላክ ነው። ምንም ስህተት ሰርቶ አያውቅም፤ ነገር ተበላሽቶበትም እንዲሁ። በመንገዱ ሁሉ ፍፁም ነው። ሃኪም ቢሆን ኖሮ የማይድን ታካሚ አይኖረውም ነበር። ጠበቃ ቢሆን የማያሸንፈው ክርክር አይኖም ነበር። ቅን እና ያለነቀፋ የመሆኑን ልክ የሚለካ ሚዛን የለም።


የሆነ ሆኖ ኃጢያተኛ እና አመፀኛ ልጆቹ ፊቱ ላይ ስንተፋበት በኃጢያታችን ስንዘፈቅ መንፈሱንም ስናሳዝን “ልጄ ሆይ ወደቤትህ ና” እያለ በተዘረጉ የፍቅር እጆቹ ወደ ንሰሃ ይጠራናል።

በእርሱ ላይ የሰራናቸውን ኃጢያቶች በሙሉ በቸልተኝነት አያልፋቸውም። ያደረግናችውን ነገሮች በሙሉ ያውቃል ሊሸከማቸውም ይችላል። ስለእኛ ያለው እውቀት ለእኛ ያለውን ፍቅር አይቀንሰውም። ከመልካም ሥራዎቻችን ጀርባ ያለውን ክፋት ሳይቀር ያስባል። ማንነታችንን እያወቀ እንደልጆቹ ሊወድደን መቻሉ በጣም የሚደንቅ ነው። የእግዚአብሔር ጸጋ ከአዕምሮ በላይ ነው። የማመልከው አምላክ ፍቅሩና ጸጋው ያስደንቁኛልና ይህንን ሳስብ አይኖቼ በእንባ ይሞላሉ።  

እግዚአብሔርን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማወቅ

በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ጸጋ ሲሰበክ እናየዋለን። አምላካችን እግዚአብሔር “መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፤ እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል” ነው (ዘጸአት 34፡6-7)። ይህ ጸጋ ለክርስቲያን እምነት ብቻ የሚገኝ ነው። ሌላ ማንኛውም ሀይማኖት ስለ ሰማያዊ ጸጋ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገር አይናገሩም።

ለዚህ ነው ለክርስቲያናዊ የተቃና ጉዞ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብና ከእግዚያብሔር ጋር ህብረት ማድረግ አስፈላጊ የሆነው። ባልጸለይን እና መጽሐፍ ቅዱስን ባላነበብን ቁጥር ስለ እግዚአብሔር ያለን አመለካከት የተዛባ ይሆናል። የእግዚአብሔር ጸጋ አሁንም ከአዕምሮአችሁ በላይ ሆኖ እንዲያሰደንቃችሁ ከፈለጋችሁ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አንብቡ።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %873 %2016 %22:%Dec
Phillip Holmes

Phillip Holmes served as a content strategist at desiringGod.org. He’s married to Jasmine. They have a son.

https://twitter.com/phillipmholmes

መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ የሚረዱ ሁለት ጠቃሚ መንገዶች

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጠቃሚ እንደሆነ የሚያስረዱ ምክንያቶችን መናገር ላያስፈልጋችሁ ይችላል። ጠቃሚ መሆኑን ግን ጠንቅቃችሁ ታውቃላችሁ። ትንሽ ማበረታቻም ሊያ...

Andy Naselli - avatar Andy Naselli

ጨርሰው ያንብቡ

አስታውሱ ፤ ይወድዳችኋል

“እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን ...

Joseph Tenney - avatar Joseph Tenney

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.