Tuesday, 19 March 2024

እንደምን አላችሁ?

ጥፋተኛ ብሆንም እነዚህ ቃላት እንደ ጥያቄ ሳይሆን እንደ ሠላምታ ሲቀርቡልኝ ትንሽ ይረብሸኛል። ተጨባጭ መልስ ሳንፈልግ “እንዴት ናችሁ?” ብሎ መጠየቅ ቀላል ነገር። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከእርምጃቸው እንኳን ሳያቋርጡ ደህና ነህ? ብለውኝ ያልፋሉ። በእነዚህ ጊዜያት ብቸኛው ተገቢ መልስ “ደህና ነኝ” ነው የሚሆነው ምንም እንኳን ነገሮች ላይሆኑ ቢችሉም። የዚህ አይነቱ ጥልቅ ያልሆነ ሰላምታ ብዙውን የየዕለት መስተጋብራችንን ይሸፍናል። ግንኙነቶቻችንን ብዙ ጊዜ ከላይ ከላይ እንፈጽማለን ነገር ግን ወደ ልባችን ስላለበት ትክክለኛ ሁኔታ ጠልቀን አንገባም።  

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና”። (ኤፌሶን 2፡4-5)

ነገር ግን እግዚአብሔር” የሚሉት እኚህ 3 ቃላት በወንጌል የተትረፈረፉ ናቸው። እንደኔና እንደእናንተ ላሉት ጠፍተው ለነበሩ፤ እራሳቸውን ከእግዚአብሔር ላይ ከተደቀነ አመፃ ሊያድኑ የማይችሉ ኃጢያተኞች ከእነዚህ የዘለሉ ሌላ ሦስት የተስፋ ቃላት ላይኖሩን ይችላል። 

አልዛይመር በሚባል በሽታ ለብዙ ዓመት ስትሰቃይ ከቆየች በኋላ አያቴ በ2002 ዓ.ም.  ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። የቀሩ ትውስታዎች ቢኖሯትም አብዛኛዎቹ የማስታወስ አቅሟ ግን ደክሞ ነበር። 

እግዚአብሔራዊ ሕይወት ወደ እግዚአብሔር በማዘንበል የሚኖር ነው። ፊታችንን ከእርሱ ሳይሆን ወደእርሱ ነው የምናዞረው። መገኘቱን ማስተዋላችንን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደድነው እንሄዳለን። እናስታውሰዋለን፤ አንረሳውም። በቀኑ መጨረሻ ላይ ተስፋችንን በእርሱ ላይ እንጥላለን። ከሞት እንደሚያድነን ብቻ ሳይሆን በሚቀጥለው ሰዓት እንኳን በእርግጥ እንደሚረዳን በእርሱ እንታመናለን።

አንዳንድ ጊዜ ለሰዎች ከዛ በፊት ሰምተውት የማያውቁትን አዲስ ሃሳብ ታካፍሏቸዋላችሁ። ከዛም ይህ ሃሳብ ስለራሳቸው ወይንም ስለሌሎች ምናልባትም ስለ እግዚአብሔር ያላቸውን አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ሲቀይር ታያላችሁ። ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ገብቷቸው ስታዩ በጣም የሚያስደስት ነገር ነው። በሕይወታቸው ውስጥ ፍሬውን ማየት አጅግ የሚያረካ ነገር ነው። ይሁን እንጂ ብዙ ጊዜ ደግሞ አይመጣም። ብዙውን ጊዜ ለሰዎች የላቀ የመረዳት ምክር ሳይሆን የሚያስፈልጋቸው የሚያውቁትን ነገር መተግበር የሚችሉበትን ብልሃት መስጠት ነው።   

የዚህን መልስ ማወቅ ሁላችንም እንፈልጋለን አይደል? ከዚህ በላይ ውጥረትን ሊፈጥር የሚችል ርዕስ ሊኖር ይችላል? ስለፈጠረን ፣ ደግሞም በሕይወት እያቆየን ስላለው ፣ ሊያድነን ልጁን ስለሰጠን ስለ ስለ ሉአላዊው እግዚአብሔር እያወራን ነው። በሰጠን እንፋሎት በሆነች በዚህች ሕይወት ውስጥ ምን እንድናርግለት ይፈልጋል? 

ስለግል የፀሎት ጊዜያችሁ መለስ ብላችሁ የምታዩበት እና በመጪዎቹ ቀናት አንድ ወይንም ሁለት ነገሮችን ለማስተካከል የምታልሙበት ጊዜ አሁን ነው። በተለምዶ ለማደግ እና ረዘም ያለ መንገድን ለማቅናት የተሻለ የሚባለው አማራጭ አጠቃላይ እድሳት ሳይሆን አንድ ወይንም ሁለት የተወሰኑ ችግሮችን ለይቶ ማውጣቱ ነው።

ያጣችሁት ነገር ላይ ዓይንን እንደመጣል እምነትን የሚያደክም ነገር የለም። 

እንደተረዳሁት ከሆነ ዓይኖቼን በቁሳዊ ማጣቶቼ ላይ ፣ በሌሉኝ ጥንካሬዎች እና በሌሉኝ ድክመቶች ላይ ባደረግሁ ጊዜ ያለማመን ሸክም ይከብድብኝና ሩጫዬን ከባድ ያደርግብኛል (ዕብራዊያን 12፡1)። 

ህዝቡ ሁሉ የኢየሱስን መሰቀል ይጠይቃል።

በትረካው ውስጥ ማንን አያችሁ?

ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? (ሮሜ 8፡35)

Page 1 of 2

ክርስቲያን ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንዲማሩ የሚያበረታ…

ትምህርት ሚኒስቴር (የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ) ባሳለፍነው አርብ መስከረም 24 ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች (ከፍተኛ የትምህርት ተቋማ...

Naol Befkadu - avatar Naol Befkadu

ጨርሰው ያንብቡ

መንገዱ ከባድ ነው።እርሱ ግን ጠንካራ ነው።

ኢየሱስም አለ “መንገዱ ከባድ ነው” (ማቴዎስ 7፡14) በቀደሙት ዘመኖቻችን “ከባድ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ የምናውቅ ይመስለን ነበር። ከባድ ጥብቅ የሆነ...

Jon Bloom - avatar Jon Bloom

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.