Tuesday, 19 March 2024

እግዚአብሔር እኔ ምን እንደሆንኩ ያስባል?

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ሁላችንም ማን እንደሆንን ማወቅ እንፈልጋለን። እራሳችንን ፈልገን ለማግኘት እንጥራለን። ብዙዎቻችን የስብዕና ፈተናዎችን እና ሌላም ግምገማዎችን ወስደናል። 

ይሁንና እነዚህ ፈተናዎች ጠቃሚዎች ሆነው ሳሉ፤ ቆም ብላችሁ ግን “እግዚአብሔር እኔ ምን እንደሆንኩ ያስባል?” “እኔ ማን እንደሆንኩ ይላል?” ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?


ቆም ብላችሁ ግን “እግዚአብሔር እኔ ምን እንደሆንኩ ያስባል?” “እኔ ማን እንደሆንኩ ይላል?” ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?


ክርስቲያን በነበርኩባቸው አመታት ሁሉ እንደዚህ ብዬ መጠየቅ የጀመርኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቻ ነው። ያገኘሁትም ነገር ቢኖር እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ሰለ እኛ የሚያስበውን የሚለው ነገር አለው። አሳጥረን ለማቅረብ ብንሞክር ግን የሚከተለውን ይመስለላል።

ዋጋችሁ ውድ ነው

እኔ ፈጣሪ እናንተም ፍጥረቶቼ ናችሁ። በአፍንጫችሁ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ብዬባችኋለሁ (ዘፍጥረት 2፡7)። በመልኬ ፈጥሬአችኋለሁ (ዘፍጥረት 1፡27)። አይኖቼ ያልተሰሩ አካሎችህን አይተዋል (መዝሙር 139፡16)። በእናትህ ማህፀን ሳለህ ሰርቼሃለሁ (መዝሙር 139፡13) በራስህ ላይ ያሉትን ፀጉሮችህን በቁጥር አውቃቸዋለሁ ከምላስህም አንዳች ቃል ሳይወጣ ምትናገረውን አውቃለሁ (ማቴዎስ 10፡30፤ መዝሙር 139፡4) ግሩምና ድንቅ ሆናችሁ ተፈጥራችኋል (መዝሙር 139፡14)።

ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ ትበልጣላችሁ (ማቴዎስ 10፡31)። በምድር ሁሉ በጎች እና በሬዎች የምድር አውሬዎች እና የሰማይ አዕዋፋት እና የባህር አሳዎች ላይ ስልጣንን ሰጥቼአችኋለሁ። (መዝሙር 8፡6-8፤ ዘፍጥረት 1፡26፤28)። የስድስቱ ቀን ፍጥረት ቁንጮ እና የመጨረሻው ትልቁ ነገር አድርጌ በክብር አንግሻችኋለሁ። (መዝሙር 8፡5፤ ዘፍጥረት 1፡26)

ነገር ግን ከመጀምሪያው ጀምሮ ስለእኔ ያለውን እውነት በውሸት ቀየራችሁት። ከእኔ ይልቅ በእጅ የተሰሩ ነገሮችን አመለካችሁ አገለገላችሁም (ሮሜ 1፡25)። ኃጢያት ሰርታችሁ ከክብሬ ጎድላችኋል (ሮሜ 3፡23)። ለአዳም እና ሄዋን እንዳልኳቸው የኃጢያታችሁ ደመወዝ ሞት ነው (ሮሜ 6፡23፤ ዘፍጥረት 2፡17)። በኃጢያታችሁም ሙታን ነበራችሁ (ኤፌሶን 2፡1)። በፍጥረታችሁ የቁጣ ልጆች ለእኔም ጠላት ነበራችሁ (ኤፌሶን 2፡3፤ ሮሜ 5፡10)። ከእኔ ዘወር አላችሁ። ተበላሻችሁ። በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድስ እንኳ (መዝሙር 14፡2-3)። የሚገባችሁ የጽድቅ ቁጣዬ ነው (መዝሙር 7፡11-12)። 

እንደዚህም ሆኖ ከታላቅ ፍቅሬ የተነሳ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙ እንጂ እንዳይጠፉ አንድያ ልጄን ሰጠኋችሁ (ዮሐንስ 3፡16)። ገና ኃጢያተኛ ሳላችሁ ክርስቶስ ሞተላችሁ። ከእኔ ጋ በጠላትነት ሳላቸሁ በልጄ ሞት አስታረቅኋችሁ።(ሮሜ 5፡8፤ 10) የመጨረሻውን ፍርድ ኃጢያት ሳይሆን ጸጋ አደረገ (ሮሜ 5፡20)።

አሁን የኢየሱስን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል (ሮሜ 10፡13)። ያመናችሁ እናንተ ዳግም ተወልዳችኋል (1 ጴጥሮስ 1፡3)። ልጆች አድርጌአችኋለሁ (ኤፌሶን 1፡5)። የእግዚአብሔር ልጆች ወራሾች ናችሁ (1 ዮሐንስ 3፡2፤ ሮሜ 8፡16-17)። ከእንግዲህ ወዲህ ወላጅ አልባ አይደላችሁም። የእኔ ናችሁ (ዮሐንስ 14፡18፤ 1 ቆሮንቶስ 6፡19)። እንደ ፍፁም  አባት እወዳችኋለሁ (1 ዮሐንስ 3፡1፤ ሉቃስ 15፡20-24)

አዲስ ናችሁ

በአይኖቼ ፊት አዲስ ፍጥረት ናችሁ። አሮጌው ነገር አልፎ አዲስ መጥቷል (2 ቆሮንቶስ 5፡17)። ለኃጢያት ሞታችሁ ለእኔ ስለምትኖሩ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢያት አይገዛችሁም። (ሮሜ 6፡11፤ ኤፌሶን 2፡4)

ከኃጢያትና ከሞት ባነት ነፃ ወጥታችኋል። አሁን ለእናንተ ኩነኔ የለባችሁም (ሮሜ 8፡1-2)። ሁሉም ኃጢያታችሁ ይቅር ተብሎላችኋል (1 ዮሐንስ 1፡7፤ 9)። በልጄ ጽድቅ ልክ አሁን በፊቴ ጻድቅ ናችሁ (ሮሜ 4፡5) ።

በጸጋ ድናችኋል (ኤፌሶን 2፡8)። በእምነት ጸድቃችኋል (ሮሜ 5፡1)። በእኔ ውሰጥ የተጠበቃችሁ ናችሁ። በክርስቶስ ኢየሱስ ካለኝ ፍቅር ማንም ሊለያችሁ አይችልም (ሮሜ 8፡39)። ማንም ከእጄ ሊያወጣችሁ አይችልም (ዮሐንስ 10፡29)። ደግሞም አልለቃችሁም ከቶም አልተዋችሁም (ዕብራዊያን 13፡5)።

መንፈሴ አላችሁ

አዲስ አባት ብቻ ሳይሆን ወንድምና እህቶችም ያለው ቤተሰብ አላችሁ (ሉቃስ8፡21)። አሁን የእግዚአብሔር ህዝብ አንድ ክፍል ናችሁ (1 ጴጥሮስ 2፡9)። በአንድነት የምትኖሩት ሕይወት በልጄ ላይ ባለ እምነት ነው (ገላትያ 2፡20)።

ኢየሱስን ተመልከቱ አይናችሁን በእርሱ ላይ አድርጉ። እርሱ የእምነታችሁ ጀማሪና ፈፃሚ ነው። (ዕብራውያን 12፡2)። ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ በመንፈሴ ይኖራል እናንም በክርስቶስ ውስጥ ናችሁ (ዮሐንስ 15፡5፤ ቆላስይስ 1፡27)። ለኢየሱስ ቀረቡ። ሕይወታችሁ የሚገኘው በእርሱ ውስጥ ነውና (ዮሐንስ 14፡6፤ ቆላ 3፡3-4) በእርሱ ኑሩ (ዮሐንስ 15፡4)። ሕይወት ክርስቶስ፤ ሞትም ጥቅም ነው (ፊሊጲስዩስ 1፡21)

በእናንተ ውስጥ ባለው በመንፈሴ ኑሩ እንጂ በራሳችሁ ሃይልም ሆነ መረዳት አትኑሩ (ዘካሪያስ 4፡6፤ ምሳሌ 3፡5)። አስታውሱ መንፈስ ቅዱስን የሰጠኋችሁ ከእናንተ ጋር እንዲሁም በእናንተ ውስጥ እንዲኖር ነው (ሮሜ 5፡5፤ ዮሐንስ 14፡17)። መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ የመራችኋል፣ ቃሌን እንድትጠብቁ ያግዛችኋል እናም ሥራዬን እንድትሰሩ ያስታጥቃችኋል (ዮሐንስ 16፡7፤ 13፤ የሐዋርያት ሥራ 1፡8፤ ገላትያ 5፡16)

ትለወጣላችሁ

ክብሬን በፈለጋችሁና ባያችሁ ቁጥር ወደልጄ መልክ እየለወጥኋችሁ ነው(2 ቆሮንቶስ 3፡18፤ ዘጸአት 33፡18)። አንድ ቀን የኋለኛው መለከት ሲነፋ በቅጽበተ አይን ትለወጣላችሁ (1 ቆሮንቶስ 15፡52)። እርሱ እንዳለ ስለምታዩት ኢየሱስ ሲገለጥ እሱን ትመስላላችሁ (1 ዮሐንስ 3፡2፤ ሮሜ 8፡29)

በኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ የሞት ሥጋችሁ ትድናላችሁ መኖሪያ ስፍራችሁም ከእኔ ጋር ይሆናል (ሮሜ 7፡24-25፤ ዮሐንስ 14፡3)። እንባችሁንም ሁሉ ከዓይኖቻችሁ አብሳለሁ፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም (ራዕይ 21፡3-4)

ያለክፍያ ከሕይወት ውሃ ምንጭ ትጠጣላችሁ እኔ እራሴም የሰባ ግብዣ ያረጀ ወይን አዘጋጅላችኋለሁ (ራዕይ 21፡6፤ ኢሳያስ 25፡6)። ወደ እረፍቴ ትገባላችሁ፤ ያዘጋጀሁላችሁን መንግስት ትውርሳላችሁ፤ ወደ ሙሉ ደስታ እና ዘላለማዊ ፍሥሐ ትገባላችሁ።(ዕብራውያን 4፡9-11፤ ማቴዎስ 16፡11)

ከሁሉም በላይ ግን ፊቴን ታያላችሁ እኔም ባለሁበት ትኖራላችሁ። (ራዕይ 22፡4፤ ዮሐንስ 14፡3)

ተወካዮቼ ናችሁ

ስለዚህ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ተመላለሱ (ኤፌሶን 4፡1)። ከእንግዲህ ወዲህ በልጄ ብርሃን ናችሁ እንጂ ጨለማ አይደላችሁም። እንደ ብርሃን ልጆች ኑሩ (ኤፌሶን 5፡8)። እናንተ የዓለም ብርሃን በተራራ ላይ ያለች ከተማ ናችሁ (ማቴዎስ 5፡14)። ጠርቼአችኋለሁ (2 ጴጥሮስ 1፡3)። መርጬአችኋለሁ (ራዕይ 17፡14)። አሁን ቅዱስ፣ አገልጋይ፣ ደቀመዝሙር እና ወታደር ናችሁ (ሮሜ 1፡7፤ የሐዋርያት ሥራ 26፡16፤ 1 ጴጥሮስ 4፡10፤ 2 ጢሞቲዎስ 2፡3)። ምስክሮች እና ሠራተኞች ናችሁ (የሐዋርያት ሥራ 1፡8፤ ኤፌሶን 2፡10)። በኢየሱስ አሸናፊዎች ናችሁ (1 ቆሮንቶስ 15፡57)። የሚደንቅ የወደፊት ኑሮ አላችሁ (ሮሜ 8፡18)። የሰማይ ሃገር ዜጋ ናችሁ። (ፊሊጵስዩስ 3፡20)። የልጄ መልዕክተኞች ናችሁ (2 ቆሮንቶስ 5፡20)።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %875 %2016 %23:%Dec
Jonathan Parnell

Jonathan Parnell is the lead pastor of Cities Church in Minneapolis/St. Paul, where he lives with his wife, Melissa, and their five children. He is co-editor of Designed for Joy: How the Gospel Impacts Men and Women, Identity and Practice.

https://twitter.com/jonathanparnell

እግዚአብሔር ተራ በሚባሉ ቀኖቻችሁም ላይ በሥራ ላይ ነው

ሁልጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደማደርገው በሰው ልጆች ታሪክ ሁሉ ውስጥ ከታተሙት መጽሐፍት ታላቅ ከሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ባለኝ አመታዊ የንባብ ጉዞዬ ዘፍጥረት...

Jon Bloom - avatar Jon Bloom

ጨርሰው ያንብቡ

የመንግሥተ ሰማይ ጠረን

የምንኖረው በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ነው። ምንም እንኳን በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እየሆነ ያለውን ነገር በሙሉ ባናይም በሚታየው ዓለም ላይ ባላቸው ተጽዕኖ ግን ...

Michelle Zombos - avatar Michelle Zombos

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.