"ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻህ ስትሆን ፤ ብቸኛ አይደለህም" የሚለው የታዋቂው ሰባኪ የውድሮው ክሩል አባባል ፍጹም እውነተኛ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ስንሆን ብቸኞች አይደለንም። ያዕቆብ ቤተሰቡን ሁሉ የያቦቅን ወንዝ ካሻገገረ በኋላ "ለብቻው ቀረ" ነገር ግን ብቸኛ አልነበረም። ከእግዚአብሔር ጋር ነበር።
ከሃያ አመት በፊት እግዚአብሔርን በቤቴል ተገናኝቶ ነበር። አሁን ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ሊታገል ነው። "ስምህ ማነው?" የሚለውን ጥያቄ ለመጨረሻ ጊዜ የጠየቀው አባቱ ይስሃቅ ነበር። ነገር ግን ያዕቆብ ለአባቱ ትክክለኛ መልስ አልመሰለሰም ነበር። ከዚያ ይልቅ "የመጀመሪያ ልጅህ ኤሳው ነኝ" ብሎ ነበር የመለሰው (ዘፍጥረት 27:18-19)። አሁን ግን እግዚአብሔር ጋር ሲጠይቀው ሊዋሽ አልቻለም "ያዕቆብ ነኝ" ብሎ መለሰ።
አንዳንድ ጊዜ እንደያእቅብ ለአመታት የዘለቀ የአታላይነት ሕይወት ሊኖረን ይችላል። ያዕቆብ ከወንድሙ ለሁለት አስርት አመታት ተደብቆ እደከረመ እኛም ከሰዎች፣ ከክርስቲያኖች እንዲሁም ከሚያውቁን ሁሉ በስህተታችን ምክንያ እየተደበቅን ከርመን ሊሆን ይችላል። ከዚህም የተነሳ ብቸኝነት ያጠቃን ሰዎች ልንሆን እንችላለን። ያዕቆብ እግዚአብሔር ዳግም ሲያገኘው ብቻውን ነበር!
የያዕቆብ ታሪክ የተቀየረው ፤ አዲስ ጅማሬ የሆነለት ማንነቱን በግልጽ ለእግዚአብሔር በመናገሩ ነው። ምንም እንኳ አባቱን ያታለለ ቢሆንም ለእግአብሔር ግን በግልጽ "ያዕቆብ ነኝ" ብሎ መለሰ። ያዕቆብ ማለት የስሙ ትርጉም "ተረከዝን የሚዝ" ወይም "አታላይ" ማለት ነው። ለእግዚአብሔር በግልጽ ማንነቱን ተናገረ። እግዚአብሔር በግልጽ ለሚናዘዙ ሰዎች የምህረት አምላክ ነውና።
እግዚአብሔር የያዕቆብን ታሪክ ከነስሙ አደሰው "ከእንግዲህ ወዲስ ስምህ እስራኤል ይባላል" (ዘፍጥረት 32:27) ። እስራኤል ማለት "ታግሎ ያሸነፈ" ወይም "ታጋይ" ማለት ነው። ብቻውን እግዚአብሔር ለማግኘት በመፍቀዱ እና ለእግዚአብሔር በግልጽ ማንነቱን በመናገሩ ያዕቆብ በአንድ ጀምበር ከአታላይነት ወደ አሸናፊነት ተሸጋገረ። ዛሬ ከያዕቆብ በመማር እኛም ያለፈው ነገራችንን ሁሉ ተቀይሮ አዲስ ጅማሬ ማድረግ እንችላለን።
Day 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8Day 9
