“መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው?” በየግል ሕይወታችን ውስጥ ለሚንጸባረቀው እንዲሁም በህብረት በየአብያተ-ክርስቲያናት በየእሑዱ ለምናካሒደው ስብሰባ ምን ፋይዳ አለው? ይህ ጥያቄ በአንድ ወገን በጣም ቀላል የሆነ፣ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሁሉ የቀመሰው እውነታ ነው። ነገር ግን በዚያው ልክ ጥልቅም ጥያቄ ነው። መንፈሳዊነት ትናንት ወደ መንግሥቱ የተጨመረ ሕጻን ሊዋኝበት የሚችል ገንዳ ነገር ግን ደግሞ ታላላቅ መርከቦችንም የሚያስተናግድ ባሕር ነው። በሕይወታችን የተለማመድነውን በቃላት ማስቀመጥ አንዳንዴ ትልቅ ጥበብን ይጠይቃል። ለምሳሌ ያህል የገላትያ ቤተክርስቲያን “ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ [እንዴት] መንፈስን ተቀበላችሁን? (ገላ 3:2)” ሲል እነዚህ ሰዎች ጥልቅ የወንጌልን እውነት ሳይረዱ እንኳ ሕያው የሆነው መንፈስ ትልቅ መንፈሳዊ ሐይልን እንዲለማመዱ አብቅቷቸዋል። እዚህ ጋር ማብቃት ግን ትልቅ አደጋ ነው።
ብስለት ባለው በጥበብ ቃል ይህንን ልምምድ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ነገረ-መለኮታዊ በሆነ መንገድ መግለጥ እስካልቻልን ሲወሰድብንም፤ ከዚያም ስተን ስንወጣም (በሌላ መንፈስ) አናውቅም። ስለዚህ "መንፈሳዊነት ምንድር ነው?" የሚለውን አስፍተንና አጥልቀን እንደገና ማሰብ ያለብን ጉዳይ ነው።
Day 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8Day 9
