Friday, 20 November 2026

ቀን 7 - የትንሳዔው ተስፋ- አዲስ ጅማሬ ክፍል 2

Posted On %PM, %02 %834 %2018 %22:%May Written by

"እንግዲህ ወንድሞች ሆይ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት አለን" ዕብራውያን 10:19-20

ይሁዳ ማለት ምስጋና ማለት ነው። የይሁዳ ሕዝብ ግን ሁልጊዜም እንደስሙ የሆነ ሕዝብ አልነበረም። በተደጋጋሚ በእግዚአብሔር ፊት ክፉን ነገር ያደርጉ ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር ከብዙ ማስጠንቀቂያ እና መልዕክት በኋላ ለ 70 አመት ለባቢሎን አገዛዝ አሳልፎ ይሰጣቸዋል (ኤር 29) ። በአንድ ወቅት እነ ዳዊትን፣ ሰለሞንን፣ ኢዮሲያስን በመሰሉ መልካም ነገስታት የተመራው ይህ ሕዝብ በጥፋቱ ምክንያት 70 አመት ለባዕድ ሕዝብ አገዛዝ ተላለፎ ተሰጠ።

አንድ የጎልማሶች ትምህርት ክፍለ ጊዜ ላይ መምህሩ "እስቲ ስህተት ሰርታችሁ የማታውቁ እጃችሁን አውጡ" ብለው ተማሪውን ሲጠይቁ ሁሉም ተማሪ ሲሳሳቅ አንድ እጅ ብቻውን ከፍ ብሎ ወጣ። መምህሩ በመደነቅ እጁን ያወጣውን ተማሪ እንዲናገር ይፈቅዱለታል። እጁን ያወጣው ተማሪ እንዲህ ብሎ ይናጋራል "ይቅርታ መምህር.. እኔ በሕይወቴ ስህተት ሰርቼ አላውቅም"። መምህሩ ስቀው "ይቅርታው ታዲያ ለምንድን ነው?" አሉት ይባላል።

ሁላችንም ስህተት መስራትን ደግሞ ይቅርታ መጠየቅን ልማዳችን አድርገነዋል። ስህተት ሲደራረብ እና ይቅርታ መጠየቅ እና መመለስ ሲጠፋ ግን ለቅጣት እንዳረጋለን። የይሁዳ ሕዝብም ለቅጣት ተዳርጎ ነበር። ስህተት ቅጣትን ትወልዳለችና።

ግን ደግሞ ተስፋ አለ! እግዚአብሔር እንደተናገረው የሰባው አመት ቅጣት በተፈጸመ ጊዜ ይህንን ሕዝብ ጎበኘው (ዕዝራ 1:1) ። እንዲሁ እኛ በተደጋጋሚ ሃጢአት በመውደቅ ከመንገድ ወጥተን ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር አምላክ የቅጣታችን ፍጻሜ የሆነውን አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በመስቀል ላይ ስለ እኛ ሰቅሎታል (ኢሳይያስ 53:8፣ ሮሜ 5:6)። ስለዚህም በክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ እኛ አዲስ መንገድ እንድንጀምር ተመርቆልናል (ዕብራውያን 10:19-20)።

ስለዚህም ያለፈውን ሃጢአታችንን፣ በደላችንና የምንከሰስበትን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ኩነኔ እንደሌለባቸው (ሮሜ 8:1) በማወቅ እና በመረዳት በተመረቀልን አዲስ መንገድ እንጓዝ! 

 Day 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8Day 9

 

Naol Befkadu

Naol Befkadu Kebede (BTh, student of MA in Ministry and Medical Doctorate student at AAU) is the founder and contributor of Lechristian Blog, an online ministry that aims to redeem cultures for the glory of God and to inspire and encourage believers for the completion Great Commission. Naol has authored an Amharic book titled "ተነሺ ፤ አብሪ" (2015) that motivates young believers for a meaningful and radical life. 

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.