Friday, 20 November 2026

ቀን 6 - የትንሳዔው ተስፋ- አዲስ ጅማሬ ክፍል 1

Posted On %PM, %06 %821 %2018 %21:%May Written by

"ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ እድፈትም ለሌለበት ለማያልፍም ርስት እንደምህረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ" 1ኛ ጴጥሮስ 1፡3

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማግስት ጀርመን እጅገ ፈራርሳ ልክ ከአሁኗ ሶርያ ጋር ተመሳሳይ ገጽታ ይዛ ነበር። መንገዶቿ እና ሕንጻዎቿ ፈራርሰው ለማየት የምትቀፍፍ ነበረች። በዚሁ ወቅት ወጣቱ ወ/ዊ ቢሊ ግራሃም ወደ ጀርምን አምርቶ በጊዜው ከነበሩት የጀርመን ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንራድ አዴናውር ጋር በ ፈራረሰው ቤተ መንግስት ተቀምጠው ያወራሉ። በንግግራቸው መሃል ጠ/ሚ አዴናውር ከመቀመጫ ቸው ብድግ ብለው በመስኮቱ አሻግረው የፈራረሰውን የሃገራቸውን ገጽታ በትካዜ ይመለከታሉ። በዚህ መሃል ወደ ወጣቱ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ዘወር አሉና " ወ/ዊ ቢሊ ግርሃም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ታምናለህ?" ብለው ይጠይቁታል። ወ/ዊ ቢሊ ግራሃምም "የወንጌል ሰባኪ እንደመሆኔ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት አምናለሁ" ብሎ ይመልስላቸዋል። በዚህ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ለሰው ልጆች ብቸኛ ተስፋ ነው!" አሉት።

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በእርግጥም ለሰው ልጆች ብቸኛ ተስፋ ነው። ሞት እንደሚሸነፍ እና የአማኞች መጨረሻ እንዳይደለ ትንሳኤው አረጋግጦልናል። ከዚህም በላይ "ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ ለሕያው ተስፋ… " ዳግም ተወልደናል። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ተስፋን ያገኘንበት ክስተት ነው። ዛሬ ምን ይሆን ተስፋ የሚያስቆርጠን? ምን ይሆን በመስኮት አሻግረን ስንመለከት በትካዜ የሚሞላን? በእርግጥም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ዛሬም ተስፋ እንዳለ ያሳየናል።

ስለዚህም በዚህ ክርስቲያኖች በመስኮት አሻግረን ከምንመለከተው ፍርስራሽ በተቃራኒ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን እናምናለን። ከምናየው ከሁኔታችን በላይ ላየነውን ትንሳኤውን በዕምነት አይን እንመለከታለን። የኑሯችን፣ የትዳራችን፣ የሃገራችን ጉዳይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆን እንኳ እኛ ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ ትንሳኤውን እናያለን። በትንሳኤው አዲስ መንገድ፣ አዲስ ሕይወት፣ አዲስ ተስፋን እናገኛለን።

 Day 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8Day 9

 

Naol Befkadu

Naol Befkadu Kebede (BTh, student of MA in Ministry and Medical Doctorate student at AAU) is the founder and contributor of Lechristian Blog, an online ministry that aims to redeem cultures for the glory of God and to inspire and encourage believers for the completion Great Commission. Naol has authored an Amharic book titled "ተነሺ ፤ አብሪ" (2015) that motivates young believers for a meaningful and radical life. 

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.