Tuesday, 19 March 2024

ቀን 6 - "ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው" 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:16

Posted On %PM, %08 %838 %2018 %22:%Jun Written by

በዩክሬን በኮሚዩኒዝሙ ዘመን መጸሐፍ ቅዱስ መያዝ የተከለከለ ነበር። ከመጸሐፍ ቅዱስ ጋር የተገኘ ማንም ሰው እስር እና ገንዘብ ቅጣት ይጠብቀው ነበር። ኮሚዩኒዝም ከዩክሬን ካበቃ በኋላ ታዲያ ነጻነት ሲመጣ አንድ ሰው ከጎረቤት ሃገር አንድ ሺህ ስድስት መቶ መጸሐፍ ቅዱሶችን በመኪናው ጭኖ ወደ ሃገሩ ዩክሬን ሲገባ የዩክሬን የድንበር ላይ ፈታሽ ፖሊሶች አስቁመው "ምንድነው በመኪናህ የጫንከው?" ብለው ይጠይቁታል። ይህ ግለሰብም ሃገሪቱ በቅርቡ ያገኘችውን ነጻነት ተማምኖ በኩራት "አንድ ሺህ ስድስት መቶ መጸሐፍ ቅዱሶች ነው የጫንኩት!" ብሎ ይመልስላቸዋል። በዚህ ጊዜ ፖሊሶቹ "መግባት አትችልም!" ይሉታል። በሁኔታው የተደናገጠው ግለሰብ "ምን አጠፋሁ?" በጥያቄ ይመልስላቸዋል። እነርሱም "ለምን አንድ ሺህ ስድስት መቶ መጸሐፍ ቅዱስ ብቻ ይዘህ መጣህ? ለሃገራችን እጅግ ብዙ መጸሐፍ ቅዱሰ ነው የሚያስፈልጋት!" አሉት ይባላል።

መጽሐፍ ቅዱስ በአለማችን ታሪክ በንባብም ሆነ በሽያጭ እንዲሁም በሕትመት ተወዳዳሪ የማይገኝለት ተጽዕኖ ፈጣሪ መጽሐፍ ነው። እንዲህ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነውም በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በጽናት የጻፉ እና በጽናት ያነበቡ የእግዚአብሔር ሰዎች ውጤት ስለሆነ ነው። ከእነርሱ መካከል ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ ይገኝበታል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ከሃያ ሰባቱ የአዲስ ኪዳን መጸሐፍቶች አስራ ሶስቱን የጻፈ ሰው ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሐዋርያ በመጨረሻዎቹ ቀናት ከገጠሙት ተግዳሮቶች መካከል አንዱ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያጣምሙ እና የሚያቀሉ ሰዎች መነሳታቸው ነው። ከዚያ ይልቅ ተረት ተረት እንዲወራ የሚፈልጉ ሰዎች በዚያ ጊዜ ነበሩ። ሐዋርያው ጳውሎስ ግን "ቃሉ ይሰበክ!" (2ኛ ጢሞቴዎስ 4:2) የሚል ቁርጥ አቋም ነበረው።

ይህ ብቻም አይደለም ሐዋርያው የእግዚአብሔር ቃል ሰባኪ ብቻ ሳይሆን አንባቢም ነበር። በዕድሜው የመጨረሻዎቹ ቀናት ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን "ስትመጣ … ጥቅልል መጸሐፍቱን በተለይም የብራና መጸሐፍቱን አምጣልኝ" (2ኛ ጢሞቴዎስ 4:13) ብሎት ነበር። በእድሜው የመጨረሻ ቀናት እንኳን ለእግዚአብሔር ቃል ፍጹም ፍቅር እና ፍላጎት ነበረው! የእግዚአብሔር ቃል እውነትን በተመለከተም ፍጹም ጽናትን አሳይቷል!

ዛሬ ዛሬ በእኛው ዘመን የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መጸሐፍ ቅዱስን እያቃለሉ እና እያብጠለጠሉ ማውራት የስልጣኔ ምልክት ተደርጎ መቆጠር ተጀምሯል። ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ሰዎች ለተረት ተረት እና ለፊልም ቦታ መስጠት ቀጥለዋል። በዚህ ዘመን የእግዚአብሔርን ቃል ይዘን እንጸና ይሆን?

በቅርቡ አንድ የሃገራችን ሰባኪ "የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መጸሐፍ ቅዱስን ይዤ ተሰድጃለሁ፣ ተከራክሬአለሁ ፣ ፍርድ ቤት ቀርቤአለሁ ፣ ሰብክያለሁ ፣ አስተምሬአለሁ። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ደግሞ እኖርለታለሁ።" ሲሉ ሰማኋቸው። ይህ የጳውሎስም አቋም እንደነበር አልጠራጠርም!

የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መጸሐፍ ቅዱስ ይዘን በዚህ አስቸጋሪ ዘመን በጽናት እንድንራመድ የሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻ ቀናት ያስተምሩናል። 

ጳውሎስን ከጎኑ ቆሞ ያበረታ እና ያጸና አምላክ (የሐዋርያት ሥራ 23፡11) እኛንም ያበርታን ደግሞም ያጽናን! አሜን!

 

 IntroductionDay 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8

 

Subscribe to get our devotionals to your email, everyday!

ድክመታችሁን ለእግዚአብሔር ስጡት

እንደምን አላችሁ? ጥፋተኛ ብሆንም እነዚህ ቃላት እንደ ጥያቄ ሳይሆን እንደ ሠላምታ ሲቀርቡልኝ ትንሽ ይረብሸኛል። ተጨባጭ መልስ ሳንፈልግ “እንዴት ናችሁ?” ...

Steven Lee - avatar Steven Lee

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.