Tuesday, 22 October 2024

ቀን 7 - "የእኔም ወንጌል ይኸው ነው፤ ለዚህም እንደ ወንጀለኛ እስከመታሰር ድረስ መከራን እየተቀበልሁ ነው" 2ኛ ጢሞቴዎስ 2:9

Posted On %PM, %09 %838 %2018 %22:%Jun Written by

ኢቫንጀሊዮን (eu)agge/lion) የሚለው የጥንታዊ ግሪክ ቃል ትርጉሙ የምስራች ማለት ነው። ቃሉ በብዛት በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ ኪዳን ውጭ በሌሎች የጥንት የግሪክ ሁለት ጽሁፎች ላይ ብቻ ሰፍሮ ይገኛል። ኢቫንጀሊዮን በአማርኛው መጸሐፍ ቅዱስ “ወንጌል” ተብሎ ተተርጉሟል። ወንጌል ማለት ምስራች ወይም መልካም ዜና ማለት ነው።

ስለ መልካም ዜና ሳስብ ሶስት ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዬ ይመጣሉ። 

1ኛ መልካም ዜና ለምን ያህል ጊዜ ነው ትኩስ ዜና ሆኖ የሚቆየው? 

2ኛ መልካም ዜና ለምን ያህል ጊዜስ ነው መልካም ሆኖ የሚቆየው? 

3ኛ መልካም ዜና ሲነገር መልካም ውጤት ብቻ ነው የሚገኘውን? 

የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው። የሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻ ቀናት ጽናቱን ከፈተኑት ነገሮች እነዚህ ጥያቄዎች እንደሚኖሩ አልጠራጠርም። የሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌል ወይም መልካም ዜና ከላይ ያሉትን ሶስት ጥያቄዎች መመለስ ነበረበት። ሐዋርያው ራሱ እንደሚናገረው የእርሱ ወንጌል ከዳዊት ዘር የሆነው ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (2ኛ ጢሞቴዎስ 2:8) ። የጳውሎስ መልካም ዜና ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ነው! ይህን ዜና ከላይ ባሉት ሶስት ጥያቄዎች ብንፈትነው። ጳወሎስ ሶስቱንም ጥያቄዎች እንዲህ ይመልስልናል።

1ኛ ይህ መልካም ዜና ለምን ያህል ጊዜ ነው ዜና ሆኖ የሚቆየው? ለዘላለም! ወንጌል የዘላለም ጉዳይ ነው! (2ኛ ጢሞቴዎስ 1:9)

2ኛ ይህ መልካም ዜና ለምን ያህል ጊዜስ ነው መልካም ሆኖ የሚቀጥለው? ለዘላለም! ወንጌል አሁንም የዘላለም ጉዳይ ነው! (2ኛ ጢሞቴዎስ 2:10)

3ኛ ይህ መልካም ዜና ሲሰበክ መልካም ውጤት ብቻ ነው የሚገኘውን? አይደለም1 መከራም አለ! (2ኛ ጢሞቴዎስ 2:9)

ለሐዋርያው ጳውሎስ በመጨረሻዎቹ ቀናት እንኳን ወንጌል በጊዜ ሂደት የሚለወጥ ነገር አልነበረም። ሐዋርያው ከምንም በላይ ወንጌል መከራን ይዞ ሊመጣ እንደሚችልም ያውቃል። ስለዚህ ወንጌልን እየሰበከ መከራን በጽናት ለማለፍ ቆረጠ ሰው ነበር!

ዛሬ እንደ ሐዋርያው ‹የእኔ› ምንለው ወንጌል ከዳዊት ዘር የሆነው ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሆነ የሚገጥመን መልካም ውጤት ብቻ ሳይሆን መከራም ከፊት ለፊታችን እንዳለ ማወቅ አለብን። ‹መከራ የለም! › የሚሉ ሰዎች ወንጌላቸው እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌል ስላልሆነ ብቻ ነው። አንደ ሐዋርያው ጳውሎስ እውነትን የሰበከ ግን መከራ ማየቱ አይቀሬ ነው።

ታዲያ ለሁላችን የሚቀረው ጥያቄ የዘላለም ጉዳይ ለሆነው ለዚህ ወንጌል መከራን እንኳ ለመቀበል ጽኑ ነን ወይ? የሚለው ነው!

ጳውሎስን ከጎኑ ቆሞ ያበረታ እና ያጸና አምላክ (የሐዋርያት ሥራ 23፡11) እኛንም ያበርታን ደግሞም ያጽናን! አሜን!

 

 IntroductionDay 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8

 

Subscribe to get our devotionals to your email, everyday!

ድክመታችሁን ለእግዚአብሔር ስጡት

እንደምን አላችሁ? ጥፋተኛ ብሆንም እነዚህ ቃላት እንደ ጥያቄ ሳይሆን እንደ ሠላምታ ሲቀርቡልኝ ትንሽ ይረብሸኛል። ተጨባጭ መልስ ሳንፈልግ “እንዴት ናችሁ?” ...

Steven Lee - avatar Steven Lee

ጨርሰው ያንብቡ

ሃሳባችሁን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት…

አንዳንድ ጊዜ ሃሳባችንን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት ውስጥ ልንጨምር ያስፈልገናል። ወደ ውስጥ በሰመጥን ቁጥር ክብደቱ ሊሰማን ይገባል...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.