በሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻ ቀናት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጋንግሪን ገብቶ ነበር። ይህ ጋንግሪን የሀሰት ትምህርት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን የሐሰት ትምህርት የገለጸበት መንገድ "እንደማይሽር ቁስል" ወይም በእንግሊዘኛው “Gangrene” (ጋግሪን) በሚል መግለጫ ነው። የሐዋርያውን ጽናት ሊገዳደር ብቻ ሳይሆን ጽናቱን ሊያጠፋ የሚችል ጋንግሪን - የሀሰት ትምህርት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየገባ ነበር።
ይህ የሐሰት ትምህርት ‹ትንሳኤ ከአሁን በፊት ሆኖአል› የሚል እንደነበር እናነባለን (2ኛ ጢሞቴዎስ 2:18) ። ይህንን የሃሰት ትምህርት ከሚያባዙት ሰዎች መካከልም ሄሜኔዎስ እና ፊሊጦስ ይገኙበታል (ቁ 17)። የዚህ ስህተት ትምህርት አደጋው ደግሞ የክርስቲያኖች ተስፋ የሆነውን ትንሳኤን ማብቃቱን እና ማለፉን ማስተማሩ ነው። በሌላ አነጋገር ክርስቲያኖች "ተስፋ የላችሁም! ሞት ማብቂያችሁ ነው" እየተባሉ ነው። ታዲያ ይህ አስተምህሮ ስርጭቱ እንደ ጋንግሪን ነው (ቁ 18) ። ከታች ጀምሮ ወደ ላይ መንፈሳዊነትን እየገደለ ምድራዊነትን እያስፋፋ የሚሄድ የሃሰት አስተምህሮ ነበር።
ከምንም በላይ ጳውሎስ የታገለለትንና መከራ የተቀበለለትን ጉዳይ ገደል የሚከት አስተምህሮ ነበር። ሐዋርያው የሰበከው እና የኖረው ስለ ሰማያዊ ምስጢርና ስለሙታን ትንሳኤ ነው። ታዲያ በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደ ጋንግሪን እየሰፋ የተነሳው አስተምህሮ ጽናቱን ያሳጣው ይሆን? በፍጹም! ሐዋርያው በእምነቱ ጽኑ ነበር! እንደውም ወደ ፊት የድልን አክሊል እንደሚቀበል ይናገራል (2ና ጢሞቴዎስ 4:8) ። ይህም የሚሆነው በቅዱሳን ትንሳኤ ነው! (የዮሐንስ ራዕይ 19:6)
በዚህ ዘመን እንደ ጋንግሪን እየተዛመቱ ያሉ የሀሰት ትምህቶች እና አስተሳሰቦች አሉ። "እግዚአብሔር የለም" ፣ "ከሞት በኋላ ሕይወት የለም" ፣ "ክርስቶስ አልሞተም" ፣ "ክርስቶስ ከሞት አልተነሳም"… ወዘተ ይገኙበታል። በእነዚህ የሃሰት አስተምህሮዎች እና አስተሳሰቦች ፊት ቆመን በጽናት የክርስቶስን ወንጌል እናውጃለን? ሐዋርያው ጸንቶ በማለፉ ከእርሱ ከምዕተ አመት በኋለ "የሐዋርያት እምነት መግለጫ" ተብሎ በሚጠራው የክርስቲያኖች የቆየ ውስጥ "በሙታን ትንሳኤ አምናለሁ" የሚል አረፍተ ነገር አለበት! የጽናት ውጤት!
ጳውሎስን ከጎኑ ቆሞ ያበረታ እና ያጸና አምላክ (የሐዋርያት ሥራ 23፡11) እኛንም ያበርታን ደግሞም ያጽናን! አሜን!
IntroductionDay 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8