የሰማይና የምድር ገዢ የሆነው እግዚአብሔር ማንነቱንና ዓላማውን፣ እንዲሁም ለሰው ልጆች ሕይወት ያለውን ዕቅድ የገለጠልን (divine disclosure) “ሰማያዊው ንጽረተ-ዓለም በዚያ በጥንታዊው ንጽረተ ዓለም” ውስጥ በነበረው «ንኪኪ» ውስጥ ነው። በዚህ ንኪኪ ውስጥ ዘመን መጠቅ የሆነው ነገረ-መለኮታዊው እውነት ተሠጠን (timeless biblical/theological truth)። ስለዚህ ዘመን መጠቅ እና ድንበር ዘለል የሆነው እውነት ለማግኘት የመጀመሪያይቱን ቤተክርስቲያን አንገባጋቢና ወቅታቂ ጉዳይ ማተት ይኖርብናል። ጥያቄዋ እና የተሰጣት መልስ ሲገባን፤ የክርስቶስ ሐሳብ ይገባናል። ይህ የመጀመሪያ ተግዳሮት ነው። ይህ የማይለወጠው አምላክ ፈቃድ በእኛም ዘመን እንዲገለጥ ከዘመናችንም ጋር «ንኪኪ» ልንፈጥር ይገባናል። ለዚህም በዙሪያችን ያለውን አንገብጋቢ ጉዳይ በእኩል አጽኖት ጠንቅቆ መረዳት ያስፈልጋል። ምክኒያቱም ሕይወታችን የምትኖረው በዚህ ዓውድ ውስጥ ስለሆነ። የአማኞችን ልብ ያንጠለጠለው ጉዳይ ምንድር ነው? በውጪ ያለው ፈተና ምንድ ነው? ጣኦት የሆነብን ነገር ምንድር ነው? ሕይወትን አንቆ የሚይዝ ስጋት ምንድር ነው? የግጭታችን መንስኤ ምንድ ነው? ወዘተ....እነዚህ የቅዱስ ቃሉ ጥያቄዎች ሳይሆኑ የዘመናችን ጥያቄዎች ናቸው። ይህ ካልሆነ እንዴት አገልጋይ ህዝቡን ያክማል። ሐኪም ዝም ብሎ መድሃኒት አያዝም፤ በመጀምሪያ ምርመራ ያካሒዳል፤ ከዚያ በሽታው ከታወቀ በኋላ ነው መድሃኒት የሚታዘዘው። በሽታው ሳይታወቅ መድኃኒት ማዘዝ በራሱ በሽታ ነው። በበሽታውና በምርመራው ላይ አተኩሮ መድሐኒቱን ግን አለማወቅ እንዲሁ በራሱ በሽታ ነው። ስለዚህ ሁለቱንም በአንድ ላይ የማገናዘብ ጥበብ በተለይ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሊካኑ የሚገባው ጥበብ ነው። ይህ ጥበብ ደግሞ በብዙዎች ምክር የሚጸና እንጂ በአንድ ሰው አስተያየት ላይ የተመሰረተ ሊሆን አይገባም።
ስለዚህ ክርስቶስን ያማከል፤ መስቀልና ትንሳኤውን ጅምሩና ግቡ በማድረግ ለሰመረ መንፈሳዊ ህይወት የሚከተሉት በአጣዳፊ ተደራርበን ልናክማቸው የሚገቡ ሕመማችን ናቸው።
- የመሪ ያለ፤ የእረኛ ያለ (1 ጴጥሮስ 5:1-4 ) ብቃት ያላቸው መሪዎች፤ ለጠብና ለግጭት የማይቸኩሉ፤ ከራሳቸውና ከእኔነታቸው በላይ ለመንጋው ፍቅር ያላቸው “የሚጤሰውን ጧፍ የማያጠፉና የተቀጠቀጠውን ሸንበቆ የማይሰብሩ" ብድራታቸውን የእረኞች አለቃ ሲመለስ ያደረጉ።
- የጸሎት ያለ፤ የሕብረት ያለ (ሮሜ 15:1-7) በክርስቶስ የመስቀል ፍቅር መዋቅር ላይ የተመሰረተ የጉባኤ ሕይወት። የክርስቶስን አርዓያነት ያነገበ መተሳሰብ እና ርህራሄ።
- የስብከት ያለ፤ የትምህርት ያለ (ሐዋርያት 20፡ 25-32) መጽሐፍ ቅዱን በመተንተን ላይ ያተኮረ፤ ክርስቶስን ያማከለ፤ ሙሉውን የእግዚአብሔር ምክር ያካተተ። ስንት አብያተ ክርስቲያናት በ10 ዓመት ቆይታዋ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን (ምንም እንኳ ጥቅስ በጥቅስ ባይሆንም ግን እያንዳንዱን መጽሐፍ ምእራፍ ጭብጥ ሐሳብ) ለምእመኗ ‘በስልታዊ መንገድ አስተምሬያለሁ’ ትል ይሆን? ይህ ካልሆነ እንዴት እንደ ጉባኤ መንፈሳዊ ህይወትን መመስረት እንችላለን?
Day 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8Day 9
