Friday, 20 November 2026

ቀን 2 - መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንፈሳዊነት - ክፍል 2

Posted On %AM, %02 %916 %2018 %00:%May Written by

ፋሲካን አስታከን  የሰነበትንበት መንፈስ (የሰሞኑ መስቀል ተኮር ስብከት፤ መዝሙር፤ ጸሎት ምሥጋና፤ ይህ በትንሳኤው ሐይል ላይ የተደገፈ የሰሞኑ መታመናችን፤ ይህ ክርስቶስ ራሱን ለብዙዎች እስኪሰጥ ድረስ የወደደበት መውደድ ላይ የተመሰረተው ፍቅራችን) እንዴት ሳያቋርጥ ይቀጥል የሚለው ጥያቄ መታሰብ ያለበት ነው። መቼም ብዙ የሚያሳስበኝና የምጸልይበት ጉዳይ የዚህ የመንፈሳዊነት ጉዳይ ነው። 

“መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው?” በየግል ሕይወታችን ውስጥ ለሚንጸባረቀው እንዲሁም በህብረት በየአብያተ-ክርስቲያናት በየእሑዱ ለምናካሒደው ስብሰባ ምን ፋይዳ አለው? ይህ ጥያቄ በአንድ ወገን በጣም ቀላል የሆነ፣ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሁሉ የቀመሰው እውነታ ነው። ነገር ግን በዚያው ልክ ጥልቅም ጥያቄ ነው። መንፈሳዊነት ትናንት ወደ መንግሥቱ የተጨመረ ሕጻን ሊዋኝበት የሚችል ገንዳ ነገር ግን ደግሞ ታላላቅ መርከቦችንም የሚያስተናግድ ባሕር ነው። በሕይወታችን የተለማመድነውን በቃላት ማስቀመጥ አንዳንዴ ትልቅ ጥበብን ይጠይቃል። ለምሳሌ ያህል የገላትያ ቤተክርስቲያን “ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ [እንዴት] መንፈስን ተቀበላችሁን? (ገላ 3:2)” ሲል እነዚህ ሰዎች ጥልቅ የወንጌልን እውነት ሳይረዱ እንኳ ሕያው የሆነው መንፈስ ትልቅ መንፈሳዊ ሐይልን እንዲለማመዱ አብቅቷቸዋል። እዚህ ጋር ማብቃት ግን ትልቅ አደጋ ነው። 

ብስለት ባለው በጥበብ ቃል ይህንን ልምምድ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ነገረ-መለኮታዊ በሆነ መንገድ መግለጥ እስካልቻልን ሲወሰድብንም፤ ከዚያም ስተን ስንወጣም (በሌላ መንፈስ) አናውቅም። ስለዚህ "መንፈሳዊነት ምንድር ነው?" የሚለውን አስፍተንና አጥልቀን እንደገና ማሰብ ያለብን ጉዳይ ነው።

 Day 1 Day 2Day 3Day 4Day 5Day 6Day 7Day 8Day 9

 

Samson Tilahun

Samson Tilahun is an Ethiopian theologian currently living in Bronx, New York. He has Masters of Divinity (M.Div.) in Biblical and Theological Studies from the Southern Baptist Theological Seminary, in Louisville KY, and currently working on Th.M. in New Testament.

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.