Monday, 15 July 2024

በጌታ እንዴት መበርታት ይቻላል?

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

1. “የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነው” (ነህምያ 8፡10)

ደስታን የኃይል ምንጭ ከሚያደርግ አምላክ ጋር መሆን መልካም አይደለምን? ሰይጣን ጨፍጋጋ አምላክ ነው። ኢየሱስ ግን ሲናገር “እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም” (ሉቃስ 6፡23)። ሰይጣን የቅዱሳንን መዝሙር ሊቋቋመው አይችልም። (ይህንንም በማወቅ የደስተኛ ሰዎች የልብ መዝሙር ሳይሆን ሰላም የሌላችው ሰዎች ማጉረምረም እና ጩኸት የሆነ ሙዚቃዊ ተለዋጭ ፈበረከ)። ተስፋን በተሞሉ ክርስቲያኖች በሚዘመር መዝሙር ሰይጣን ሲወጣ አይቼ አውቃለሁ። በሕይወቴም እንደተማርኩት ሩጫውን ለመጨረስ እርምጃው የእግዚአብሔርን ደስታ ዕለት ተዕለት ማደስ እንደሆነ ነው። ደስታ ታላቅ ኃይል ነው። 

2. “የእግዚአብሔርንም ክብርም ተስፋ በማድረግ ሐሴት እናደርጋለን” (ሮሜ 5፡2)።

አንዳንድ ደስታዎቻችን አሁን ባሉን እንደ ኃጢያት ይቅርታ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት፣ አላማ ያለው ሕይወት ፣ አምልኮ ፣ ሕብረት ፣ የፀሀይ መግባት እና መውጣት፣ ድንቅ ጓደኞች እና ቤተሰቦች ወዘተ ምክንያት ይመጣሉ። ነገር ግን ቀላል የሆነ ግን የሚያም እውነታ “የውጭው ሰውነታችን እየጠፋ” (2 ቆሮንቶስ 4፡16) መሆኑ ነው። “በሁሉ እንገፋለን… እናመነታለን … እንሰደዳለን …እንወድቃለን …” (2 ቆሮንቶስ 4፡8-9) ፤ እርሱም ብቻ አይደለም “የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን” (ሮሜ 8፡23)። ስለዚህ እዚህ ባለ ሕይወታችን የማይናወጥ ደስታ እንዲኖረን ካስፈለገ “ተስፋ” በምናደርግበት ነገር ላይ መሆን አለበት። “በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። (ሮሜ 8፡24-25)። ስለዚህ “በተስፋ ደስ ይበላችሁ” (ሮሜ 12፡12)

3. "እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ…ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር" (ራዕይ 21፡4፤3)።

ተስፋችን ይህ ነው። የእግዚአብሔር ክብር አንድ ቀን በአዲስ ፍጥረት ፊት መካከል ይቆምና እንባን ሁሉ፣ ህመምን ሁሉ፣ ሀዘንን ሁሉ፣ ስብራትን ሁሉ ፍርሀትን እና ወቀሳን ሁሉ ያስወግዳል። ለእያንዳንዱ ታማኝነት እና ታዛዥነት ዋጋ ይሰጠዋል። እያንዳንዱ ራስን መካድ እና ስለ እምነት የሆነ መከራ ሁሉ 100 እጥፍ ካሳ ይቀበላል። "ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር ይሰጠናል" (ሮሜ 8፡32)። እግዚአብሔር ያለው ሁሉ ለልጆቹ ደስታ የዘለአለም ርስት ይሆናል።

4. "ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም፤ የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው” (ኤፌሶን 1፡16-18)

ትልቁ ፈተና አሁን የተስፋችንን ታላቅነት ማወቁ ላይ ነው። በአዕምሮአችን ማየት ብቻ ሳይሆን በልቦናችን ዓይኖች ማየቱ ላይ ነው። ይሄ ታላቁ መንፈሳዊ ውጊያ ነው። ቴሌቪዥናችንን አጥፍተን በቃሉ ላይ እና በጉልበቶቻችን በመሆን የምንዋጋው ነው። “እያዩ አለማየትን እየሰሙ አለመስማትን እግዚአብሔር ከእኛ ያርቅ”። “በልባችን ውስጥ የበራ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር”. . . “በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ” (2 ቆሮንቶስ 4፡6) እንጸልይ።

ማጠቃለያ

ለዓይኖቻችሁ ጸልዩ “የእግዚአብሔርን ክብርም እዩ”፤ በዚያ ክብር ተስፋ አድርጉ፤ “በተስፋ ደስ ይበላችሁ”፤ በደስታ በርቱ።

ከእናንተ ጋር ወደ እግዚአብሔር ለመዘርጋት አብሬአችሁ ነኝ።

ፓስተር ጆን

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %904 %2016 %23:%Dec
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

አሮጌው እኔ አዲስ ሲሆን

አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእ...

Marshall Segal - avatar Marshall Segal

ጨርሰው ያንብቡ

የእግዚአብሔር ጸጋ ከአዕምሮ በላይ ነው

መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቸር አምላክ እንደሆነ ይናገራል። ብዙ ሰዎች ግን ይህንን ለማመን ይቸገራሉ። አንዳንዶች ጸጋ ምን እንደሚመስል ሲያስቡ ይገረማሉ። የእ...

Phillip Holmes - avatar Phillip Holmes

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.