የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።
የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።
ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥
አንተ ረዳቴና መጠጊያዬ ነህ፥ በቃልህም ተማመንሁ።
ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ።
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።
እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ።
ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።
በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።
እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንፅና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ።
በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።
በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢፀልዩ፣ ፊቴንም ቢፈልጉ፣ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም ፈውሳለሁ።
ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።
አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።
ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።
የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ ብርሃኑ እየጎላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።
ሳታቋርጡ ጸልዩ።
Daily Injera is a Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible each day.
The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.