ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ፊታችሁም አያፍርም።
ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ፊታችሁም አያፍርም።
አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኃልና፤እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።
የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
ልጄ ሆይ፥ ኃጢያተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።
የምወድህ ልጄ አንተ ነህ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።
በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤እርሱም የርስታችን መያዣ ነው።
እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።
የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤የኀጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል።
መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ፀልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ እየሱስ ወደ እናንተ ነውና።
ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።
በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።
አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፣ አንተ ታላቅ ነህ። ስምህ በኃይል ታላቅ ነው።
የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ ብርሃኑ እየጎላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።
እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ።
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፥ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም፤
ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤
ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሱም ዘንድ...
DownloadDaily Injera is a Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible each day.
The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.