Saturday, 20 April 2024

የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን? ነህምያ 4፡2

Posted On %AM, %27 %934 %2017 %00:%May Written by

ከአድካሚ የስራ ቀን በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያዬ እየሔድኩ ሳለሁ በውስጤ ብዙ ሃሳብ  ይመላለስ ነበር። ተስፋ የላቸውም ብዬ የምቆጥራቸው ነገሮች ሲበዙ ከፈረሰው ነገር ባሻገር ማየት አቃተኝና ጥልቅ የሆነ ሃዘን ዉስጥ ገባሁ። ተስፋዬም እያሽቆለቆለ ሲሄድ ድምፅ አልባ በሆነ መቃተት ወደ እግዚአብሔር ተማፀንኩ።

ወዲያውኑም አንድ ቃል ወደ ውስጤ መጣ።  ነህምያ እና ሕዝቡ ኢየሩሳሌምን እንደገና መስራት እንደጀመሩ እነሳናባላጥ በሰሙ ጊዜ እንዲህ ብለዉ ተሳለቁባቸው “እነዚህ ደካማ አይሁድ ምን እያደረጉ ነው? ቅጥራቸውን መልሰው ሊሰሩ ነውን? መስዋዕት ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ጀንበር ሠርተው ሊጨርሱ ነውን? እንደዚያ ተቃጥሎ የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን?” ነህምያ 4፡2። 

በርግጥም ከተማይቱ የፈረሰችበትን መጠን ላየ ሰው ቅጥሩ ሊታደስ ከተማይቱም እንደገና ልትታነፅ ትችላለች ብሎ ማሰብ ዘበት ነበር። በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንዲህ አልነበረም። እግዚያብሔራዊው መልስ ’አዎ ይቻላል‘ ሆነ። ለኔም በጊዜው የመጣልኝ መልስ ‘ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና አዎ ተቃጥሎ የፍርስራሽ ክምር የሆነው ድንጋይ ነፍስ ሊዘራበት ይችላል፣ አዎ ተስፋ የተቆረጠበት ነገር እንደገና ሊታደስ ይችላል’ የሚል ነው።

ዛሬ በሚያጋጥሙን ነገሮች ልባችን ዝሎና ተስፋ ቆርጠን ወደኋላ እንዳንመለስ እግዚአብሔር የገባልንን እንዲህ ያለውን ህያው ተስፋ አጥብቀን እንያዝ። በዙሪያችን ያለው ነገር ሁሉ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም እንኳን ይህ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ በቂ ምክንያት አይደለም። በእውነት እግዚአብሔር ከአእምሮአችን በላይ ትልቅ ነው፣ ለእኛም የገባው ተስፋ በሰው አእምሮ ከመገመትና ከመወሰን ያልፋል። ‘ነፍሴ ሆይ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክሽ ላይ አድርጊ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና’ መዝሙር 42፡5-6።

 

Last modified on %AM, %27 %943 %2017 %00:%May

በርባን እና እኔ

ህዝቡ ሁሉ የኢየሱስን መሰቀል ይጠይቃል። በትረካው ውስጥ ማንን አያችሁ?

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

እግዚአብሔር ተራ በሚባሉ ቀኖቻችሁም ላይ በሥራ ላይ ነው

ሁልጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደማደርገው በሰው ልጆች ታሪክ ሁሉ ውስጥ ከታተሙት መጽሐፍት ታላቅ ከሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ባለኝ አመታዊ የንባብ ጉዞዬ ዘፍጥረት...

Jon Bloom - avatar Jon Bloom

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.