“የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሺታ መንፈስም ደግፈኝ” (መዝሙር 51፡12) ።
ይሄ ክፍል በቃል ለመያዝ ቀላል ከመሆኑ በላይ ነፍሴ ድክም ስትል ጸሎቴን ትኩረት እንድሰጠው ያደርገኛል ። የጸሎቱ መዋቅር በየዕለቱ የሚያስፈልጉኝ የሦስት ነገሮች ልመና ነው ።
ደስታዬን አድስ፡- እግዚአብሔር ሆይ ኃጢያተኛ ነፍሴን ለማዳን የወሰድከውን ርቀት አስታውሰኝ ። ባዳነኝ ጣፋጭ ምህረት እደሰት ዘንድ እባክህ ይገባኝ የነበረውን ቅዱሱን ቁጣህን ዳግም አስታውሰኝ ። ይህ ደስታ አሁን የሚሰማኝን መድከም እንዲሸፍን አድርግ ።
ታማኝነቴን መልስ፡- እግዚአብሔር ሆይ ልቤ የዛለው ታማኝነቴ ልክ ስላልሆነ ነው ። ልቤን ባዶ የሚያደርጉትን ቀለል ያሉ ነገሮችን ፤ ድሎትን እና የሰው ምስጋናን ፈልጌአለሁ ። ኃጢያቴን አምናለሁ እባክህን ታማኝነቴን ከስምህ ጋር አንድ ላይ አስሂድ ። ለክብርህም መልሼ መሰጠት እንድችል አድርግ ። "የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ" (መዝሙር 51፡10)
የእሽታ ታዛዥነትን ስጠኝ፡- እግዚአብሔር ሆይ በግዴታዎች ተነሳስቼ ሳይሆን ውስጤ ባለው በሚያስችለው መንፈስህ ዛሬ እንድታዘዝህ እርዳኝ ። ልታዘዝህ እና የመታዘዝን የደስታ ፍሬ መቅመስ ከልቤ እፈልጋለሁ ። ነፃ የሆነ እሺ የሚል መንፈስ ያስፈልገኛል ። የአንተን ነፃ እና እሺ የሚል መንፈስ እሻለሁ። በእዚህ እንድትደግፈኝ እጸልያለሁ።
በእራሴ ቋንቋ፡- እግዚአብሔር ሆይ ደስታዬን አድስ ፣ ታማኝነቴን መልስ እናም ዛሬ አንተን እንድታዘዝ ነፃነትን ስጠኝ ።
ደብዛዛ በሆኑ ቀኖቼ ዞር ብዬ የማያቸው በጣም አጭር ጸሎቶቼ እነዚህ ናቸው ።
Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe