ከመቀየሩ በፊት ክርስቲያኖችን የሚጠላ (የሐዋርያት ሥራ 9፡1) ክርስቶስን የሚያሳድድ (የሐዋርያት ሥራ 9፡5) በቅንዓት የተሞላ (ፊሊጲስዩስ 3፡6 ፤ ገላትያ 1፡14) እንደነበር እናውቃለን። በእነዚህ ክፉ ቀኖች ምክንያት እራሱን “የ ኃጢያተኞች ዋነኛ” እያለ ይጠራ ነበር (1 ጢሞቴዎስ 1፡15፤ 1 ቆሮንቶስ 15፡9)።
ደግሞም ወደ እምነት ያመጣው ዘንድ እግዚአብሔር ወደ ጳውሎስ ሕይወት በአስደናቂ እና ሥልጣን ባለው መንገድ ዘልቆ እንደገባ እናውቃለን (የሐዋርያት ሥራ 9፡3-19)። ይህም ማለት በደማስቆው መንገድ ላይ የተፈጠረውን ጳውሎስን ያገኘበትን ክስተት፤ ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ከማሰሩ እና ከመግደሉ በፊት ሊያደርገው ይችል ነበር። ግን አላደረገም።
ስለዚህ ዓላማው ጳውሎስ “የኃጢያተኞች ዋና” እንዲሆን መፍቀድ ነበር። ከዚያም ሊያድነው እና 13 የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትን የሚጽፍ ሐዋርያ ማድረግ ነበር።
ለምን? ለምን በዚህ መንገድ ያደርገዋል? ለምን ከመወለዱ በፊት ሐዋርያ እንዲሆን መርጦት ነገር ግን አስከፊ እና ጠንካራ የክርስቶስ ተቃዋሚ እንዲሆን ይፈቅድለታል? ከዚያም ደግሞ በደማስቆ መንገድ ላይ በአስደናቂ እና ሥልጣን በተሞላ መንገድ ያድነዋል፤ ለምን?
ቀጥሎ 6 ምክንያቶች አሉ። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በግልጽ የተጻፉ ናቸው። የመጨረሻዎቹ አራቱ ደግሞ ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ምክንያቶች ልንረዳቸው የምችላቸው ናቸው። እግዚአብሔር እንደዚህ ነው ያደረገው. . .
1. ፍጹም የሆነውን የክርስቶስን ትዕግስት ያሳይ ዘነድ።
“ስለዚህ ግን፥ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ።” (1 ጢሞቴዎስ 1፡16)
2. እጅግ ኃጢያተኛ ስለሆንኩ ተስፋ የለኝም ብለው የሚያስቡትን ለማጽናናት።
“ስለዚህ ግን፥ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ።” (1 ጢሞቴዎስ 1፡16)
3. ክርስቲያኖችን የገደሉትን ልበ ደንዳና የክርስቶስ ጠላቶችን እንኳን ሳይቀር እግዚአብሔር እንደሚያድን ለማሳየት።
4. እግዚአብሔር አብልጦ የሚወደውን ምርጡን አስከፊ ኃጢያት ውስጥ እንዲሰምጥ መፍቀዱን ለማሳየት።
5. እግዚአብሔር የኃጢያተኞች ዋነኛን የአገልጋዮች ዋነኛ ሊያደርገው እንደሚችል ለማሳየት።
6. አቅም የሌላት፣ በስደት ላይ ያለች የተጠላችዋ ቤተክርስቲያን፣ በ ኃይለኛው ጠላታቸው መለኮታዊ ላውጥ ድል ልትነሳ እንደምትችል ለማሳየት።
Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe