መንፈሳዊ ውልደት እንደተካሄደ የምናውቀው ዳግም በተወለደው ሰው ህይወት ውስጥ በሚኖረው እንቅስቃሴ ነው። ከጨለማ ወደ ብርሃን ፣ ከሱሰኛነት ነፃ ወደመሆን ፣ ከተስፋ ቢስነት ወደ ተስፋ ሙሉነት። መንፈሳዊ ውልደት የሚፈጥረውን ተጽዕኖ እናያለን።
በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ የሚካሄዱ ብዙ ነገሮች አሉ። አሁን ግን ስንጸልይ ምን እንደሚሆን ትኩረት ማድረግ እፈልጋለሁ። ስንጸልይ ምን ይሆናል በሚለው ላይ ትኩረት ስናደርግ እንኳን ብዙ አቅጣጫዎችን ልንመለከት እንችላለን። ዛሬ ግን ትኩረታችን የሚሆነው ስንጸልይ በ መንግሥተ ሰማይ ምን ይሆናል በሚለው ላይ ነው።
በምንጸልይበት ጊዜ በሰማይ ስለሚሆነው ነገር በማወቃችሁ ምክንያት መጸለይ አብልጣችሁ እንድትሹ ጸሎቴ ነው። የመንግሥተ ሰማይን እውነታ ወደሚጨበጠው የህይወታችሁ አውድ አውርዳችሁ በሚታየው ዓለማችሁ ላይ በእግዚአብሔር ብቻ እንጂ በተለመደው መንገድ ሊገለጽ የማይችል እንቅስቃሴ ታዩ ዘንድ ነው።
እስቲ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንመልከትና በምንጸልይበት ጊዜ በሰማይ ምን እንደሚሆን እንይ። ከዚህ አንድ ክፍል ወደ 3 መደምደሚያዎች ልንደርስ እንችላለን።
ራዕይ 8፥4 “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።”
• ጸሎቶቻችን በጥንቃቄ የተጠበቁ ናቸው። ጸሎቶቻችን ከአፋችን ወይንም ከልባችን ወጥተው አየር ላይ የሚቀሩ ከቃላት ያልዘለሉ ተራ ነገሮች እንደሆነ ልናስብ እነንችላለን። ነገር ግን ጸሎቶቻችን በ መላእክት የሚያዙ handled ናቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ጸሎቶቻችን በፊቱ የሚቀርቡት በመላእክት እገዛ ነው። ጸሎታችን የታየበት ያማረ መንገድ አይደለምን? እግዚአብሔር እኛ ላይ ምንም ዕዳ የለበትም። ከእርሱ ጋር በጸሎት ልንገናኝ ጊዜን ስንወስድ እርሱ ደግሞ ጸሎታችንን ሊሰማ ጊዜ ይሰጠናል። ጸሎታችሁን እየሰማ ያለው በዙፋኑ ላይ ያለው የነገስሥታት ንጉሥ ነው። ጸልዩ!
• ጸሎቶቻችን ለእግዚአብሔር መልካም የመዓዛ ሽታ ናቸው። ጣፋጭ ዶሮ ስትበሉ ከመቅረቡ በፊት ቅመማ ቅመሞች ተጨምረውበት በደንብ ሰለበሰለ እንደሆነ ታውቃላችሁ። ጸሎቶቻችንም ከጣፋጭ ቅመሞች ጋር የተዋሀዱ ናቸው። በብሉይ ኪዳን ጊዜ እጣን ማጠን የመስዋዕቱ ሥነ ስርዓት አንድ ክፍል እንዲሆን አግዚአብሔር ተናግሮ ነበር። ጥቃቅኖቹ ነገሮች ሳይቀሩ ለእርሱ አስፈላጊ ስለሆኑ ምን ዓይነት እጣን መጠቀም እንዳለባቸው ተናግሮ ነበር።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ "ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም እጣን ውሰድ የሁሉም መጠን ትክክል ይሁን። በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ፥ በጨው የተቀመመ ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው። ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታልመውማለህ ከዚያም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም የቅዱሳን ቅዱስ ይሁንላችሁ።" ዘጸአት 30፡34-36
የእግዚአብሔር እና አሮን መገናኘት በእነዚህ መልካም መአዛ ባላቸው እጣኖች የታጀበ ነበረ። በኢየሱስ ሞት ጊዜ መጋረጃው ሲቀደድ ፣ እግዚአብሔርን ለማናገር በእኛ ምትክ ካህን ማስፈለጉ ቀረና እጣኑ ወደ ሰማይ ተሸጋገረ። ከእግዚአብሔር ጋር በመገናኛችን ጊዜ እጣኑ ጸሎታችንን ያነጻውና ቅዱስ ያደርገዋል። ጸሎቶቻችን በሰማያዊ ስፍራ ይቀነባበራሉ። በጸሎታችን ጊዜ ይህንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንዴት ድንቅ ነገር ነው! በመአዛው እጅግ ደስተኛ ነው ፤ ስለዚህ ጸልዩ!
• ጸሎቶታችን የሚማለዱት በራሱ በኢየሱስ ነው
"እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።" 1 ጢሞቴዎስ 2:1-5
ይሄ ክፍል ለሁሉም ሰዎች (በተለይ በሥልጣን ላይ ላሉት) መጸለይ እንዳለብን ብቻ አያብራራም፤ ነገር ግን ኢየሱስ እራሱ እንደሚያማልድልን ደግሞ ይናገራል። ምንአልባት ከበላያችን ያሉት ባለሥልጣናት ኃጢያተኞች እንደሆኑና እነእርሱም አዳኝ እንደሚያስፈልጋቸው ረስተን ወደ እግዚአብሔር አቅርበን አስቀምጠናቸው ሊሆን ይችላል። ምንአልባት እኛ የሌለን መብት አላቸው ብለን በማሰብ እንዲጸልዩልን ወደ ሰዎች (ቄስ ሊሆን ይችላል ወይንም ነብይ አልያም ፓስተራችሁ) ቀርበን ሊሆን ይችላል። ይሄ መብት ያለው ግን ኢየሱስ ብቻ ነው ወደ እርሱም እንድንቀርብ እየጠበቀ ነው! ጸሎታችሁን በአብ ዘንድ ሲያቀርብ ስለእናንተ ሊማልድላችሁ ይፈልጋል። ስለዚህ ጸልዩ! ኢየሱስ እየጠበቀ ነው . . .
Translated by Joshua Terefe