Monday, 15 July 2024

ጾም ለጀማሪዎች

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ምንአልባት አልፎ አልፎ አልያም ፈጽሞ ከማይጾሙት ብዙኃኑ የክርስቲያን ጎራ ልትሆኑ ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስላላነበብን ወይንም ከአንድ ሊታመን ከሚገባ ስብከት ስላልተማርን ወይንም ስለጾም ሃይል ስላልሰማን አይደለም። እንደእርሱ ቢሆን እራሱ ልናደርገው አንፈልግም። መብላታችንን ዘወር ማድረጉ ከባድ ነገር ይሆንብናል። 

አንዱ ምክንያት ያለንበት ማህበረሰብ ሊሆን ይችላል። ምግብን እንዲሁ ተገናኝቶ ለመብላት እና ግንኙነታችንን ለማሳደግ እንበላለን ወይንም ከኃላፊነት ለመሸሽም እንበላለን።

በእርግጥ ከመጾም የሚከለክለን የራሳችን የድሎት ረሃብ አለን። 

ጾም በፍቃደኝነት ምግብን ወይንም ማንኛውንም ከእግዚአብሔር የተሰጠን የምንደሰትበትን መልካም ስጦታ ለአንድ መንፈሳዊ አላማ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ ማቋረጥ ነው። 

የጠፋውን የጾምን ባህል ለመመለስና በፍሬው ለመደሰት ካለብን ጆሯችንን በወዳጆቻችን ስሜት እና ግንኙነት ላይ ጥለን ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳችንን ከፍተን ነው መሆን ያለበት። እንደዚህ ሲሆን ጥያቄው መጾም አለብን ወይ መሆኑ ይቀርና መቼ እንፁም ይሆናል። ኢየሱስ ተከታዮቹ እንደሚጾሙ ሃሳቡ ነበረው። እውን እንደሚሆንም ቃል ገብቶላቸው ነበር። “ምንአልባት ስትጾሙ” ሳይሆን “ስትጾሙ” ነው ያለው (ማቴዎስ 6፡16)። ደግሞም ተከታዮቼ “ሊጾሙ ይችላሉ” ሳይሆን “ይጾማሉ”ነው ያለው (ማቴዎስ 9፡15)። 


ጾም በፍቃደኝነት ምግብን ወይንም ማንኛውንም ከእግዚአብሔር የተሰጠን የምንደሰትበትን መልካም ስጦታ ለአንድ መንፈሳዊ አላማ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ ማቋረጥ ነው። 


እዚህ ባለው ሕይወታችን የምንጾመው ከዚህ በኋላ ሕይወት አለ ብለን ስለምናምን ነው። በሚመጣው ዘመን ሁሉን እንደምናገኝ ተስፋ ስለተሰጠን እዚህ ሁሉን ማግኘት የለብንም። የማይታየውን እና ወሰን የሌለውን እግዚአብሔር ስላየን እና ስለቀመስን፤ እርሱነቱን የበለጠ ስለምንራብ ልናያቸው እና ልንቀምሳቸው ከምንችላቸው ነገሮች እንጾማለን።

ጊዜያዊ መሣሪያ 

በዙሪያችን ካለው ህመም እና ችግሮች ዘለን ንጹህ አየርን መሳብ እንድንችል ልባችንን የምናሰፋበት ለዚህ ዓለም የተዘጋጀ ነገር ጾም ነው። በውስጣችን ላለው ድካም እና ኃጢያት ጋር ላለ ፍልሚያ የተሰጠ ነው። በኃጢያተኛ ማንነታችን እርካታ እንደሌለን ነገር ግን ለክርስቶስ ፍላጎት እንዳለን የምንገልፅበት መንገድ ነው።

ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ ጾም ያበቃል። በዚህ ላለ ሕይወት እና ዘመን ብቻ የተዘጋጀ በኢየሱስ ላይ ያለንን ደስታ ለማበልጸግ እና ለሚመጣው ሕይወት እንድንዘጋጅ ፊት ለፊት እንድናየው የሚያደርገን ጊዜያዊ መሣሪያ ነው። ተመልሶ ሲመጣ ግብዣን ያዘጋጃል እንጂ ጾምን አያውጅም። የዚያን ጊዜ ቅዱስ የነበሩት መከልከሎቻችን ግባቸውን ስለሚመቱ በሁሉም ዘንድ እንዴት ያለ ድንቅ ስጦታ እንደነበረ ይገለጣል።

እስከዚያ ድረስ ግን እንጾማለን።

ጾምን እንዴት መጀመር እንችላለን

ጾም የሚከብድ ነገር ነው። በተግባር ከሚባለው ይልቅ በሃሳብ ደረጃ ቀላል ይመስላል። አንድ ምግብ ስንዘል የሚሰማን ድካም በእርግጥ የሚያስገርም ነው። ብዙ ጀማሪ ጿሚዎች አንድ ምግብ በመዝለል ለመጀመር ይሞክሩና ነገር ግን ሆዳችን የሚቀጥለው የምግብ ሰዓት ሳይደርስ ጾሙን ትተነው ላለፈውም እንድናካክስ ይገፋፋናል። 

ጾም ቀላል ነገር ቢመስልም ዓለም፣ ስጋችን እና ሰይጣን እንዳንጾም የተለያዪ ውስብስብ ነገሮችን ሊያመጡብን እርስ በእርስ ይመክራሉ። ወደ ጾም መንገድ መግባት እንድትችሉ ሊረዷችሁ የሚችሉ 6 ጠቃሚ ምክሮች እነሆ። እነዚህ ምክሮች ምንአልባት ጥልቅ ያልሆኑ ናቸው ነገር ግን ለጀማሪዎችም ሆነ ሞክረውት ለማያውቁ ሊጠቅሙ ይችላሉ። 


1. በትንሹ መጀመር

በአንድ ጊዜ ሳምቱን ለመጾም አትሞክሩ። አንድ ምግብ በመዝለል ጀምሩ። በሳምንት አንድ ምግብ ለረጅም ሳምንታት በመዝለል ጀምሩ። ከዚያም ሁለት ምግብ መዝለል ሞክሩ። እንደዚህ እያደረጋችሁ ወደ ሙሉ ቀን ጾም አሳድጉት። ከጊዜ በኋላ ደግሞ ፈሳሽ ነገር ብቻ እየወሰዳችሁ ለሁለት ቀን ለመጾም ሞክሩ።

ፈሳሽ ነገር ብቻ ስንል ምግብን እና የለስላሳ መጠጦችን ሳያጠቃልል ውሃ እና ጭማቂዎችን እየወሰድን የምንጾመው ነው። ጭማቂ መውሰድ ስኳር ስላለው ሰውነታችን መስራቱን እንዲቀጥል እያገዘው በተመሳሳይ ጊዜ ጠጣር ምግብ ካለመውሰድ የሚመጣውን ስሜት ግን እንዳለ ይተወዋል። ማንኛውንም አይነት ጊዜ የሚወስድ ጾም ስትጾሙ ያለ ውሃ ማድረግ የሚመከር ነገር አይደለም።


2. በመብላት ምትክ የምታደርጉትን ነገር አቅዱ  

ጾም እራስን መከልከል ብቻ አይለም ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሙሉነት የምንፈልግበት መንፈሳዊ ልምምድ ነው። ይህም ማለት እንመገብበት በነበረው ሰዓት ልናደርጋቸው ለሚገቡ አዎንታዊ መፈለጎች እቅድ ማውጣት አለብን። ከቀናችን ውስጥ ረዘም ያለ ጊዜ ከምግብ ጋር እናሳልፋለን። የጾም ዋነኛው ጥቅም ለመጸለይ እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማሰላሰል ወይንም ለሌሎች ፍቅርን ለማሳየት እንድንችል የሚፈጥረው ጊዜ ነው።

ቀጥታ ወደ ጾም ከመግባታችን በፊት ቀለል ያለች እቅድ አውጡ። ከምትጾሙበት አላማ ጋር አዛምዱት። እያንዳንዱ ጾም መንፈሳዊ አላማ ያስፈልገዋል። ይህ አላማችሁ ምን እንደሆነ ካወቃችሁ በኋላ የመብል ጊዜአችሁን በምን እንደምትለዉጡት አቅዱ። ያለ አላማ እና እቅድ እንዲሁ እየተራብን ነው እንጂ ክርስቲያናዊ ጾም ሊባል አይችልም። 


ቀጥታ ወደ ጾም ከመግባታችን በፊት ቀለል ያለች እቅድ አውጡ። ከምትጾሙበት አላማ ጋር አዛምዱት። እያንዳንዱ ጾም መንፈሳዊ አላማ ያስፈልገዋል። ይህ አላማችሁ ምን እንደሆነ ካወቃችሁ በኋላ የመብል ጊዜአችሁን በምን እንደምትለዉጡት አቅዱ። ያለ አላማ እና እቅድ እንዲሁ እየተራብን ነው እንጂ ክርስቲያናዊ ጾም ሊባል አይችልም። 


3. ሌሎችን እንዴት እንደሚነካ አስቡ

ጾም ሌሎችን ችላ ለማለት ፍቃድ አይሆንም። በእግዚአብሔር ላይ ካለን ታላቅ ትኩረት የተነሳ ለሌሎች አትኩሮት እና እንክብካቤ አለመስጠት አሳዛኝ ነው የሚሆነው። ለእግዚአብሔር እና ለባለንጀሮቻችን ያለን ፍቅር ጎን ለጎን የሚሄድ ነገር ነው። ትክክለኛ ጾም ወደላይ ያለንን አትኩሮት ወደ ጎን ካለን ጋር አጣምሮ ይይዛል። እንደውም በምንጾምበት ጊዜ ሰዎች የበለጠ ፍቅር እና እንክብካቤ እንዲሰማቸው ያስፈልጋል።

ስለዚህ የጾም እቅዳችሁን በምትነድፉበት ጊዜ ሌሎችንም እንዴት እንደሚነካ አስቡ። በመሥሪያ ቤታችሁ ምሳ አብራችሁ የምትበሉ ጓደኞች ካሏችሁ ወይንም ከቤተሰብ ጋር እራት አብራችሁ የምትበሉ ከሆነ፤ መቅረታችሁ እነርሱን እንዴት እንደሚነካቸው አስቡና ሳያሳውቁ ከመቅረት ወይንም የምግብ ጊዜ ሲደርስ አልበላም ከማለት ቀድማችሁ አሳውቋቸው።

ለመጾም የሚያነሳሱ እድሎችንም አስተውሉ። ለምሳሌ አብራችሁ የምትበሉ ጓደኞች ወይንም የቤተሰብ አባላት ውስጥ በጉዞ ወይንም በሥራ ዕረፍት አሊያም ባልታወቁ ምክንያቶች ቢቀሩ ለብቻችሁ ከመብላት ይልቅ ይህን አጋጣሚ ለመጾም ተጠቀሙበት።


4. የተለያዩ የጾም አይነቶች ሞክሩ 

የተለመደው የጾም አይነት ተለይተን በግል የምናደርገው ነው። ነገር ግን የተለያዩ የጾም አይነቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰዋል።  በግል እና በሕብረት፣ በስውር እና በግልፅ፣ ጉባኤ አቀፍ እና ሃገር አቀፍ፣ ጊዜያዊ እና ቋሚ የመሳሰሉት ከተጠቀሱት ውስጥ ናቸው።

ከቤተሰብ፣ ከአነስተኛ ቡድን ወይንም ከቤተክርስቲያን ጋር ለመጸለይ አስቡ። በጋራ የእግዚአብሔር እርዳታ እና ጥበብ የሚያስፈልጋችሁ ሁኔታ ውስጥ አላችሁ? የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ሊያስፈልጋችሁ የሚችልበት የተለየ ጉዳይ በቤተክርስቲያናችሁ ወይንም በማህበረሰባችሁ ውስጥ አለ? ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጥሩ እይታ እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ? እንግዲያውሰ ከሌሎች አማኞች ጋር አንድ በመሆን የእግዚአብሔርን እርዳታ ለምኑ።


5. ከምግብ ውጪ ያሉ ነገሮችንም ጹሙ

ለሁሉም ሰው ከምግብ መጾም አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። አንዳንድ የጤንነት እክሎች ከተለመደው የመጾሚያ ስልት ገሸሽ ሊያደርጉን ይችላሉ። ጾም ከምግብ መቆጠብ ላይ ብቻ አይወሰንም። ማርቲን ሎይድ ጆንስ ሲናገር “ጾም ለአንድ ለተለየ መንፈሳዊ ጥቅም ሊውል በሚችል መልኩ ከማንኛውም አይነት ነገር መቆጠብን ሊያጠቃልል ይገባል።” ይላል

ካላችሁበት የጤንነት ሁኔታ አንጻር ምግብ ማቆም የማይመከር ከሆነ በኢየሱስ ላይ በሙሉ ልባችሁ መደሰት ትችሉ ዘንድ እንደ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒዩተር፣ ማህበራዊ ድሕረ ገፆች እና ከመሳሰሉት መዝናኛዎች ለመጾም አስቡ። ጳውሎስ ለተጋቡ ሰዎች ከግብረ ሥጋ ግንኙነት መጾምን ሳይቀር ይጠቅሳል። “ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለአለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።” (1 ቆሮ 7፡5)


6. አለመብላታችሁን አታስቡ

ሆዳችሁ መግቡኝ እያለ ጥያቄ በሚያሰማበት ጊዜ ምግብ አልበላሁም በሚለው ሃሳብ አዕምሮአችሁን አትያዙ። ለሆዳችሁ እንቢ ማለትን እራሳችሁን ብታስለምዱ ነገር ግን ዓይናችሁን ከምግብ ላይ ማንሳት ካልቻላችሁ ከእግዚአብሔር ይልቅ ስለ ምግብ ያላችሁን ፍቅር ነው የሚያሳየው።

ክርስቲያናዊ ጾም ትኩረትን ሁሉ ወደ ኢየሱስ ወይንም በዚህች ምድር ላይ ወደሚገኝ የተሻለ የክርስቶስ አላማ ያዞራል። ኃጢያትን ለመዋጋት ይሁን ወይንም ስለ አንድ ሰው ደኅንነት ለመለመን፣ ስላልተወለደ አንድ ህፃን ለመጠየቅ ወይንም ኢየሱስን የበለጠ ለመለማመድ ላለ ጥማት ቢሆን፣ ክርስቲያናዊ ጾም የረሃብን ህመም ወስዶ ወደ አንድ ዘላለማዊ አርማ ቁልፍነት ይቀይረዋል።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %847 %2016 %22:%Dec
David Mathis

David Mathis is executive editor for desiringGod.org, pastor at Cities Church in Minneapolis/Saint Paul, and adjunct professor for Bethlehem College & Seminary. He is author of Habits of Grace: Enjoying Jesus through the Spiritual Disciplines.

https://twitter.com/davidcmathis

የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን? ነ…

ከአድካሚ የስራ ቀን በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያዬ እየሔድኩ ሳለሁ በውስጤ ብዙ ሃሳብ  ይመላለስ ነበር። ተስፋ የላቸውም ብዬ የምቆጥራቸው ነገሮች ሲበዙ ከፈረሰው...

Yodit Fantahun - avatar Yodit Fantahun

ጨርሰው ያንብቡ

እግዚአብሔር ተራ በሚባሉ ቀኖቻችሁም ላይ በሥራ ላይ ነው

ሁልጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደማደርገው በሰው ልጆች ታሪክ ሁሉ ውስጥ ከታተሙት መጽሐፍት ታላቅ ከሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ባለኝ አመታዊ የንባብ ጉዞዬ ዘፍጥረት...

Jon Bloom - avatar Jon Bloom

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.