Tuesday, 19 March 2024

የመንግሥተ ሰማይ ጠረን

Posted On %PM, %07 %845 %2016 %22:%Dec Written by

የምንኖረው በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ነው። ምንም እንኳን በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እየሆነ ያለውን ነገር በሙሉ ባናይም በሚታየው ዓለም ላይ ባላቸው ተጽዕኖ ግን እንዳሉ እናውቃለን። ከዚህም ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዳግም ስንወለድ ስለሚሆነው መንፈሳዊ ውልደት ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ነግሮት ነበር። በዮሐንስ 3፡8 ላይ ሲናገር “ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው” አለ።

መንፈሳዊ ውልደት እንደተካሄደ የምናውቀው ዳግም በተወለደው ሰው ህይወት ውስጥ በሚኖረው እንቅስቃሴ ነው። ከጨለማ ወደ ብርሃን ፣ ከሱሰኛነት ነፃ ወደመሆን ፣ ከተስፋ ቢስነት ወደ ተስፋ ሙሉነት። መንፈሳዊ ውልደት የሚፈጥረውን ተጽዕኖ እናያለን።

በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ የሚካሄዱ ብዙ ነገሮች አሉ። አሁን ግን ስንጸልይ ምን እንደሚሆን ትኩረት ማድረግ እፈልጋለሁ። ስንጸልይ ምን ይሆናል በሚለው ላይ ትኩረት ስናደርግ እንኳን ብዙ አቅጣጫዎችን ልንመለከት እንችላለን። ዛሬ ግን ትኩረታችን የሚሆነው ስንጸልይ በ መንግሥተ ሰማይ ምን ይሆናል በሚለው ላይ ነው።

በምንጸልይበት ጊዜ በሰማይ ስለሚሆነው ነገር በማወቃችሁ ምክንያት መጸለይ አብልጣችሁ እንድትሹ ጸሎቴ ነው። የመንግሥተ ሰማይን እውነታ ወደሚጨበጠው የህይወታችሁ አውድ አውርዳችሁ በሚታየው ዓለማችሁ ላይ በእግዚአብሔር ብቻ እንጂ በተለመደው መንገድ ሊገለጽ የማይችል እንቅስቃሴ ታዩ ዘንድ ነው።

እስቲ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንመልከትና በምንጸልይበት ጊዜ በሰማይ ምን እንደሚሆን እንይ። ከዚህ አንድ ክፍል ወደ 3 መደምደሚያዎች ልንደርስ እንችላለን።

ራዕይ 8፥4 “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።

ጸሎቶቻችን በጥንቃቄ የተጠበቁ ናቸው። ጸሎቶቻችን ከአፋችን ወይንም ከልባችን ወጥተው አየር ላይ የሚቀሩ ከቃላት ያልዘለሉ ተራ ነገሮች እንደሆነ ልናስብ እነንችላለን። ነገር ግን ጸሎቶቻችን በ መላእክት የሚያዙ handled ናቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ጸሎቶቻችን በፊቱ የሚቀርቡት በመላእክት እገዛ ነው። ጸሎታችን የታየበት ያማረ መንገድ አይደለምን? እግዚአብሔር እኛ ላይ ምንም ዕዳ የለበትም። ከእርሱ ጋር በጸሎት ልንገናኝ ጊዜን ስንወስድ እርሱ ደግሞ ጸሎታችንን ሊሰማ ጊዜ ይሰጠናል። ጸሎታችሁን እየሰማ ያለው በዙፋኑ ላይ ያለው የነገስሥታት ንጉሥ ነው። ጸልዩ!

ጸሎቶቻችን ለእግዚአብሔር መልካም የመዓዛ ሽታ ናቸው። ጣፋጭ ዶሮ ስትበሉ ከመቅረቡ በፊት ቅመማ ቅመሞች ተጨምረውበት በደንብ ሰለበሰለ እንደሆነ ታውቃላችሁ። ጸሎቶቻችንም ከጣፋጭ ቅመሞች ጋር የተዋሀዱ ናቸው። በብሉይ ኪዳን ጊዜ እጣን ማጠን የመስዋዕቱ ሥነ ስርዓት አንድ ክፍል እንዲሆን አግዚአብሔር ተናግሮ ነበር። ጥቃቅኖቹ ነገሮች ሳይቀሩ ለእርሱ አስፈላጊ ስለሆኑ ምን ዓይነት እጣን መጠቀም እንዳለባቸው ተናግሮ ነበር።

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ "ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም እጣን ውሰድ የሁሉም መጠን ትክክል ይሁን። በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ፥ በጨው የተቀመመ ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው። ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታልመውማለህ ከዚያም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም የቅዱሳን ቅዱስ ይሁንላችሁ።" ዘጸአት 30፡34-36

የእግዚአብሔር እና አሮን መገናኘት በእነዚህ መልካም መአዛ ባላቸው እጣኖች የታጀበ ነበረ። በኢየሱስ ሞት ጊዜ መጋረጃው ሲቀደድ ፣ እግዚአብሔርን ለማናገር በእኛ ምትክ ካህን ማስፈለጉ ቀረና እጣኑ ወደ ሰማይ ተሸጋገረ። ከእግዚአብሔር ጋር በመገናኛችን ጊዜ እጣኑ ጸሎታችንን ያነጻውና ቅዱስ ያደርገዋል። ጸሎቶቻችን በሰማያዊ ስፍራ ይቀነባበራሉ። በጸሎታችን ጊዜ ይህንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንዴት ድንቅ ነገር ነው! በመአዛው እጅግ ደስተኛ ነው ፤ ስለዚህ ጸልዩ!

ጸሎቶታችን የሚማለዱት በራሱ በኢየሱስ ነው

"እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።" 1 ጢሞቴዎስ 2:1-5

 ይሄ ክፍል ለሁሉም ሰዎች (በተለይ በሥልጣን ላይ ላሉት) መጸለይ እንዳለብን ብቻ አያብራራም፤ ነገር ግን ኢየሱስ እራሱ እንደሚያማልድልን ደግሞ ይናገራል። ምንአልባት ከበላያችን ያሉት ባለሥልጣናት ኃጢያተኞች እንደሆኑና እነእርሱም አዳኝ እንደሚያስፈልጋቸው ረስተን ወደ እግዚአብሔር አቅርበን አስቀምጠናቸው ሊሆን ይችላል። ምንአልባት እኛ የሌለን መብት አላቸው ብለን በማሰብ እንዲጸልዩልን ወደ ሰዎች (ቄስ ሊሆን ይችላል ወይንም ነብይ አልያም ፓስተራችሁ) ቀርበን ሊሆን ይችላል። ይሄ መብት ያለው ግን ኢየሱስ ብቻ ነው ወደ እርሱም እንድንቀርብ እየጠበቀ ነው! ጸሎታችሁን በአብ ዘንድ ሲያቀርብ ስለእናንተ ሊማልድላችሁ ይፈልጋል። ስለዚህ ጸልዩ! ኢየሱስ እየጠበቀ ነው . . .

 

Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %795 %2016 %21:%Dec
Michelle Zombos

Born in Auckland, New Zealand to migrant parents from Western Samoa and Australia/Greece, Michelle declared at the age of six that one day she would be a “missionary” to Ethiopia. After giving her life to Jesus as a 19-year-old mother and wife, she started to serve in ministry in South Auckland’s urban community. After having her five children and graduating from Bible College, she eventually came to Ethiopia with her family where she has served a local Ethiopian Evangelical Mekane Yesus Church in Debre Zeit and Addis Ababa. She is passionate about the word of God and sharing it with those who long to connect with their Creator.

aheartforethiopia.blogspot.com/

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ

የሰው ህይወት በምድር ላይ ብዙ ሰልፍ፣ ብዙ መከራ፣ ብዙ ፈተና እንዳለበት የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። የመከራውም ሆነ የፈተናው ዓይነት ብዛቱም ሆነ ዐይነቱ ...

Eyob B Kassa - avatar Eyob B Kassa

ጨርሰው ያንብቡ

ምስጋና ለመስጠት 32 ምክንያቶች

እንግሊዛዊው ፓስተር እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ማቲው ሄነሪ (1662-1714) ከመሞቱ 2 ዓመት በፊት ስለ ጸሎት መጽሐፍ ጽፎ ነበር። ለጸሎት የሚሆን መንገድ...

Donny Friederichsen - avatar Donny Friederichsen

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.