Monday, 15 July 2024

ከአዕምሮ እውቀት ወደ ልብ ትግበራ መሄጃ 5 መንገዶች

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

አንዳንድ ጊዜ ለሰዎች ከዛ በፊት ሰምተውት የማያውቁትን አዲስ ሃሳብ ታካፍሏቸዋላችሁ። ከዛም ይህ ሃሳብ ስለራሳቸው ወይንም ስለሌሎች ምናልባትም ስለ እግዚአብሔር ያላቸውን አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ሲቀይር ታያላችሁ። ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ገብቷቸው ስታዩ በጣም የሚያስደስት ነገር ነው። በሕይወታቸው ውስጥ ፍሬውን ማየት አጅግ የሚያረካ ነገር ነው። ይሁን እንጂ ብዙ ጊዜ ደግሞ አይመጣም። ብዙውን ጊዜ ለሰዎች የላቀ የመረዳት ምክር ሳይሆን የሚያስፈልጋቸው የሚያውቁትን ነገር መተግበር የሚችሉበትን ብልሃት መስጠት ነው።   

ታዲያ እንዴት ነው “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ” (ምሳሌ 3፡5) ከሚለው ትዕዛዝ “እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ። በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል? (መዝሙር 56፡3-4) ወደሚለው የግል እምነት የምንሻገረው? በሌላ አነጋገር እንዴት ነው የአዕምሮን እውቀት ወደ ልባችን ልናወርደው የምንችለው? አምስት መንገዶች ይኸውላችሁ፡-

1. በክርስትና ሕይወት ውስጥ መከራ እና አገልግሎት እንደሚኖር እውነተኛ ምስል ይኑራችሁ

ትክክለኛዎቹ የእግዚአብሔር ተስፋዎች ህመምን ፣ ፍርኃትን እና ሃዘንን አያስወግዱም። እርግጥ ነው ወንጌል ከዚህ ከተበላሸ ዓለም እፎይታን ይሰጠናል (ሮሜ 8) ነገር ግን መከራ በእግዚአብሔር አላማ ውስጥ አንድ ክፍል ሆኖ እንጂ ከዛ ውጪ ሳይሆን ይገኛል (ሮሜ 5፡3-5)። ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔርን ተስፋዎች ካሉብን ጉዳቶች ሁሉ በአንድ ጊዜ እንዲገላግለን አይነት ልንጠቀማቸው እንሞክራለን። ይሄ አካሄዳችንም አልሰራ ሲል እራሳችንን የእግዚአብሔር መልካምነት አይገባኝም እያልን እንወቅሳለን ወይንም እግዚአብሔርን መልካም አይደለም እያልን እንወቅሳለን አሊያም ሁለታችንንም እንወቅሳለን።  

ይሁን እንጂ ጳውሎስ በ ሮሜ 5 እና 1 ተሰሎንቄ 4 በግልጽ ሲናገር የእግዚአብሄር ተስፋዎች ከህመም አይጋርዱንም ነገር ግን ያድኑናል። ወንጌል ህመማችንን በተስፋ ይነካውና ልንቆጣጠረው የምንችል አላማ ያለው ያደርገዋል እንጂ አያጠፋውም። 

2. በመጀመሪያም በሙሉ ልባችሁ ባይሰማችሁም የየዕለት ፀሎት እና መጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፈፅሙ። በየሳምንቱም በጋራ የአምልኮ ስብሰባዎች ላይ ተሳተፉ

በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ባልኖርን ቁጥር ልንተገብረው የማንችል ይመስለናል። ይህ እውነት በጣም ቀላል ለማሰብ የማይከብድ ይመስለናል ነገር ግን እንደ ብዙ ፍላጎቶቻችን (ምግብ ፣ እንቅልፍ ፣ መዝናናት) መንፈሳዊ ፍላጎታችንም በሚገጥሙን ችግሮች በቀላሉ ሊቃወስ ይችላል። በሚገጥሙን መከራዎች መሀል “እግዚአብሔር የዚህን ጊዜ ወዴት አለ?” ብለን ለመጠየቅ እንቃጣለን። ነገር ግን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ “አምልኮዬ ወዴት አለ?” ብለን ነው። ለእግዚአብሔር ነገር ፍላጎታችን ሞቶ የእግዚአብሔር መገኘት ማይሰማን ከሆነ ልንደነቅ አይገባንም። በየጊዜው መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና አምልኮ ልክ እንደ እንቅልፍ ፣ እንቅስቃሴ እና ምግብ ወሳኝ ነገር ናቸው (ማቴዎስ 4፡4)


በሚገጥሙን መከራዎች መሀል “እግዚአብሔር የዚህን ጊዜ ወዴት አለ?” ብለን ለመጠየቅ እንቃጣለን። ነገር ግን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ “አምልኮዬ ወዴት አለ?” ብለን ነው። ለእግዚአብሔር ነገር ፍላጎታችን ሞቶ የእግዚአብሔር መገኘት ማይሰማን ከሆነ ልንደነቅ አይገባንም። በየጊዜው መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና አምልኮ ልክ እንደ እንቅልፍ ፣ እንቅስቃሴ እና ምግብ ወሳኝ ነገር ናቸው (ማቴዎስ 4፡4)


3. አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ወስዳችሁ በቃላችሁ ለመሸምደድ እና ለማሰላሰል ሞክሩ። ከዚያ ክፍል ልታወጡ የምትችሉትን ያህል ነገር ያገኛችሁ ሲመስላችሁ ወደሌላ ጥቅስ ደግሞ ተሻገሩ

የቃል ጥናት ጥቅስ ወሳኝ ነገር ነው። በዚህ ዘመን የተረሳ ድንቅ ጥበብ ነው። ከአጠቃላይ የእግዚአብሔር እውነቶች ይልቅ እንድ ወይንም  ከዚያ በላይ የሆኑ ልከኛ የእግዚአብሔር ተስፋዎችን ማወቅ አስፈላጊ ነው። የእግዚአብሔርን እውነት በቅፅበት ለመተግበር አቅም ሲኖረን ስሜቶቻችንን ወደ ዓለም ከማጠፍ ይልቅ ከመስቀሉ ቅርፅ ጋር እንድናስማማ ይረዳናል።

4. የእግዚአብሔርን እውነት ማስተጋባት እና በትክክል መግለፅ የሚችሉ መዝሙሮችን ፈልጉ። አብራችሁ መዘመር እስክትችሉ ድረስ አጫውቱት።

ሙዚቃ ስሜቶቻንን ለመቆጣጠር የሚረዳን የሚያስደንቅ ነገር ነው። በ2013 በተደረገ ጥናት ተመራማሪዎች እንደገለፁት ሙዚቃ ልንሰማ ስንጀምር የምንጠቀመው የአንጎላችን ክፍል ለሥነ አመክንዮ የምንጠቀምበትን ተመሳሳይ ክፍል እንደሆነ ነው። ይሄ ግን ማለት ልቅ የሆኑ ነገሮችን ስንሰማ እንድንፈጽማቸው ያስገድደናል ማለት አይደለም። ለምንሰማቸው ሙዚቃዎች ባሪያዎች አይደለንም። ይሁን እንጂ ልባችንን ከምንሰማው ነገሮቸ ጋር ደግሞ በቅርበት እንዲጣጣሙ ሊያደርግን እና ተቀባይነት ያላቸው ሊያስመስላቸው ይችላል።

ተቃራኒውም እውነታ አለው። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚያጠናክሩ መዝሙሮችን የምንሰማ እና አብረን መዘመር የምንችል ከሆነ በአስቸጋሪ ጊዜያት ጠንካራ እንድንሆን እራሳችንን ልናገኝ እንችላለን የእግዚአብሔርም ተስፋዎች ለተሰበረው ልባችን ጠቃሚ መስለው እንዲሰሙን ያደርጋል። ለዚህም ሊሆን ይችላል የመጽሐፍ ቅዱሳችን ትልቁ መጽሐፍ (መዝሙረ ዳዊት) የመዝሙር መጽሐፍ የሆነው። እግዚአብሔር አንጎላችሁ እንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ ምንም አይነት መሳሪያ መጠቀም አያስፈልገውም። 


የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚያጠናክሩ መዝሙሮችን የምንሰማ እና አብረን መዘመር የምንችል ከሆነ በአስቸጋሪ ጊዜያት ጠንካራ እንድንሆን እራሳችንን ልናገኝ እንችላለን የእግዚአብሔርም ተስፋዎች ለተሰበረው ልባችን ጠቃሚ መስለው እንዲሰሙን ያደርጋል። ለዚህም ሊሆን ይችላል የመጽሐፍ ቅዱሳችን ትልቁ መጽሐፍ (መዝሙረ ዳዊት) የመዝሙር መጽሐፍ የሆነው። 


5. ለእግዚአብሔር ክብር ማገልገል የምትችሉበትን ቦታ አግኝታችሁ ግቡ።

ሲ. ኤስ. ሉዊስ አንድ ጊዜ እንዳለው እንደ ክርስቲያን ስለራሳችን ትንሽ ነገር እንድናስብ ሳይሆን ስለራሳችን ትንሽ ብቻ እንድናስብ ነው የተጠራነው። ክርስቶስ ተመሳሳይ ነገር በ ማቴዎስ 20 ላይ ይናገራል። ከራሳችን በላይ ሌሎችን ስናስቀድም ከተያዝንበት የእራስ ሃዘኔታ (Self Pity) አረንቋ ወጥተን በዚህ መከራ ውስጥ ለብቻችንን እንዳልሆንን ማየት እንችላለን። ደግሞም ሌሎችን በእግዚአብሔር ተስፋዎች ከፍ ልናደርግ ስንጥር እራሳችንን ተደላድለን ስንቆም እናገኘዋለን። ስለዚህ በአላማ ስናገለግል ካገለገልናቸው ሰዎች ይልቅ ለእራሳችን ታላቅ አገልግሎት ሆኖ እናገኘዋለን።

የእግዚአብሔርን የጸጋ ተስፋዎች እና መፅናናቶች በ ተጎዳ ፣ ፍርኃት በያዘው ቁጡ ላባችን ላይ ተግባራዊ ማድረግ ብዙ ክርስቲያኖች ወደ ሥራ ሊገቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ምንም እነዚህ 5 ምክሮች በአንድ ሌሊት ከፅኑ ሀዘን ወደ መረጋጋት ላይቀይሯችሁ ቢችሉም የእግዚአብሔርን ተስፋ እና የጥበቃውን ቅርበት ግን እንዲሰማችሁ ሊረዷችሁ ይችላሉ።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %852 %2016 %22:%Dec
Josh Squires

Josh Squires Josh Squires (@jsquires12) has degrees in counseling and divinity. He currently serves as the pastor of counseling and congregational care at First Presbyterian Church in Columbia, SC where he lives with his wife Melanie and their five children.

twitter.com/jsquires12

አስታውሱ ፤ ይወድዳችኋል

“እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን ...

Joseph Tenney - avatar Joseph Tenney

ጨርሰው ያንብቡ

የጋብቻዎን ቀን ያለ ድንግልና ማሳለፍ

አንድ ወጣት የሚከተለዉን ጥያቄ አስተላልፎልናል፡- ፓስተር ጆን፣ የሴት ጓደኛዬን እንድታገባኝ ልጠይቃት እፈልጋለሁ። ለትዳርም በምዘጋጅበት ጊዜ የቀደሙት ስህተ...

Tony Reinke - avatar Tony Reinke

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.