Tuesday, 19 March 2024

መልካምነቱን ማስታወስ — መንፈሳዊ የመርሳት ችግርን ለመፋለም 6 መንገዶች

Posted On %AM, %12 %041 %2016 %03:%Oct Written by

አልዛይመር በሚባል በሽታ ለብዙ ዓመት ስትሰቃይ ከቆየች በኋላ አያቴ በ2002 ዓ.ም.  ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። የቀሩ ትውስታዎች ቢኖሯትም አብዛኛዎቹ የማስታወስ አቅሟ ግን ደክሞ ነበር። 

ከአስርት ዓመታት በፊት ለእናቷ ሕይወት ማስታወሻ ጽፋ ነበር። ከእናቷ ጋር ዘወትር አርብ በስልክ ታወራለች። ከዛም በእራሷ እጅ ጽሁፍ የእናቷን ታሪክ ጻፈች። ቤተሰቦቿን እንዴት በልጅነቷ እንዳጣች ፣ በጀርመናዊ ቤተሰቦች ጉዲፈቻ እንደተደረገች ፣ እናም ወደ አሜሪካ ተመልሳ ቤንጃሚን ግራፊን የተባለ ሰውን እንዳገባች ጻፈች።

በመጨረሻዎቹ ዓመታት እና ወራት አክስቴ ካሮል ይህን ማስታወሻ ለአያቴ ታነብላት ነበር። ብዙ ትውስታዎቿ ደብዝዘው እና ጠፍተው ነበር ነገር ግን እነዚያ ማስታወሻዎች ሲነበቡላት የሆነ ነገር ፊቷ ላይ ይፈነጥቅ ነበር።

የሰው ልጆች የማስታወስ ችሎታ እንዴት እንደሚሰራ (እንዲሁም እንዴት እንደማይሰራ) ሚስጥር የሆነ ነገር ነው።

አታስታውሱምን?

የእግዚአብሔርን ታማኝነት ወደማስታወሱ ስንመጣ ዝንጉዎች ልንሆን እንችላለን። አንድ የሚያስደንቅ ምሳሌ በዘጸአት 14 እና 16 ላይ እናገኛለን። በትንሽ ምዕራፎች ልዩነት እስራኤላውያን ከባርነት ነፃ ወጥተው በቀይ ባህር ሲያልፉ ቀጥሎ ግን ምግብ የለንም ብለው ሲያጉረመርሙ እናያለን።

“እግዚአብሔር ምን እንዳደረገላችሁ አታስታውሱምን?” ውሃው እንደግድግዳ ቆሞ በቀይ ባህር ውስጥ በደረቅ መሬት ተሻገራችሁ! እና ይህንን ያደረገ እግዚአብሔር ምግብ ለእናንተ ማዘጋጀት የሚችል አይመስላችሁምን? እመኑት! ልንላቸው እንፈልጋለን።

ይሁን እንጂ እኛም እንደዚህ ያሉ ነገሮችን እንደምናደርግ እናስታውሳለን። እግዚአብሔር ከፈተናዎች ውስጥ ያወጣናል ፣ ጸሎታችንን ይመልስልናል ይሁን እንጂ በጥቂት ቀናት ውስጥ ፈጽሞ እንረሳዋለን። ገና ይሄ እየሆነ ስለሚቀጥለው ትግላችን እያሰብን ለማጉረምረም ምክንያቶችን እንፈልጋለን።

የእግዚአብሔርን መልካምነት የምናስታውስበት መንገድ መፈለግ አለብን።

የእግዚአብሔር መልካም መታሰቢያዎች

በኢያሱ መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ላይ እግዚአብሔር ለህዝቡ ያደረገላቸውን አስደናቂ ታዕምራት እናነባለን። የዮርዳኖስ ወንዝን በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ ወንዙን እንዳይፈስ አስቆመው። እግዚአብሔር 12 ድንጋዮችን ከ ዮርዳኖስ ወስደው እንደመታሰቢያ እንደሚያቆሙ በኢያሱ በኩል ተናገራቸው። ከእያንዳንዱም ነገድ አንድ ሰው ከወንዙ ዳር ድንጋይ እንዲያመጣ ተመረጠ።  እግዚአብሔር በዛ ቀን ለህዝቡ ላደረገላቸው ነገር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ድንጋዮቹን ኢያሱ ደረደረ።


እግዚአብሔር ለእኛ መልካም ነው። መንፈሳዊ የመርሳት በሽታ እንዳለብን ያውቃል። ዝንጉዎች እንደሆንን ያውቃል። ስለዚህም መታሰቢያዎችን ሰጥቶናል። 


እግዚአብሔር ለእኛ መልካም ነው። መንፈሳዊ የመርሳት በሽታ እንዳለብን ያውቃል። ዝንጉዎች እንደሆንን ያውቃል። ስለዚህም መታሰቢያዎችን ሰጥቶናል። እንደ ማስታወሻ የሚያገለግሉ ነገሮችን እንድናደርግ አዝዞናል። መንፈሳዊ የመርሳት በሽታን ልንዋጋባቸው የምንችላቸው 6 ተግባራዊ መንገዶች እኚሁላችሁ።

1. አስቡ

ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ እንደ ድንጋዮቹ ልታዩአቸው የምትችሏቸው እግዚአብሔር ግልፅ በሆነ መልኩ እየመራችሁ ፣ ጸሎታችሁን እየመለሰ ፣ ተስፋውንም እየፈጸመ ኃይሉን በሕይወታችሁ ያሳየባቸው ክስተቶች የትኞቹ ናቸው? “በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ በሥራህም እጫወታለሁ” (መዝሙር 77፡12)

2. አመስግኑ 

ላደረገላችሁ ነገሮች ልባችሁን በምስጋና ጥመዱ። “አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ” (መዝሙር 9፡1)።

3. ተናገሩ

እግዚአብሔር ስላደረገልን ታላላቅ ነገሮች ነገር ለማሰብ እና ለማመስገን ጊዜ ከወሰድን በኋላ የእነዚያ ትውስታዎች ደስታ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር ስናወራ ሞልተው ይትረፈረፋሉ። በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 4 ልጆችን የሚመለከት አንድ ተዕዛዝ እናገኛለን:- “ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ አባቶቻቸውን። እነዚህ ድንጋዮች ምንድር ናቸው? ብለው ሲጠይቁ፥ ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ። እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ” (ኢያሱ 4፡21-22)።

4. ባህል/ልምዶች

የዓመት በአልን እና የልደት በአላት ባህሎችን ስታስቡ የእግዚአብሔርን መልካምነት ልትናገሩ የምትችሉባቸውን መንገዶች እንዴት እንደምታጠቃልሉበት አስቡ።

5. ጻፉ 

ማስታወሻ መጽሐፍ ይኑራችሁ። የፀሎት ጥያቄያችሁን ጻፉበት ከዛም እግዚአብሔር እንዴት እነዚህን ጸሎቶች እንደመለሰላችሁ ጻፉ። ተስፋ በምትቆርጡባቸው ጊዜያት መለስ ብላችሁ የእግዚአብሔርን መልካምነት እንድታዩ ወደ እነዚህ ጽሁፎች ተመልከቱ።

6. ቅመሱ እዩም

የጌታ እራት እና ጥምቀት ድንጋጌዎች ክርስቶስ ያደረገውን ነገር የምናስብበት እና የምናውጅበት ጥልቅ መንገዶች ናቸው። እግዚአብሔር በመልካምቱ ግልጽ የሆኑ ስሜቶቻችንን የሚያጠቃልሉ መታሰቢያዎችን ሰጥቶናል። 

የጌታ እራት ስንወስድ በእጆቻችን ኅብስቱን እና ፅዋውን እንይዛለን። የመዳሰሻ ፣ የሽታ እና የመቅመሻ የስሜት ህዋሶቻችን ክርስቶስ በእኛ ምትክ ስለሞተው ሞት ምሳሌ የሆነውን ማዕድ  ስንካፈል ይሳተፋሉ። ለሚጠመቀው ደግሞ በውሀ ውስጥ ሲነከር የሚደንቅ ትውስታን ይፈጥራል። ሌሎቻችን ግን በቦታው በመገኘት የተሳተፍን አይኖቻችን የሞትን የመቀበርን ደግሞም ከሞት የመነሳትን ምሳሌ ያያሉ።

አንርሳ። መንፈሳዊ የመርሳት በሽታን እግዚአብሔር በሰጡን መታሰቢያዎች የምንዋጋ ሕዝብ ያድርገን።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %905 %2016 %23:%Dec
Ben Reaoch

Ben Reaoch is the pastor of Three Rivers Grace Church in Pittsburgh and the author of Women, Slaves, and the Gender Debate (P&R, 2012).

https://twitter.com/BenReaoch

የምንሰራበት ዋነኛው ምክንያት

ማብሰል ስላልፈለጋችሁ ውጪ ወጥቶ መብላት ይሁን ወይንም የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያለማቋረጥ ማየት ቢሆን፣ ወይንም ሥራ ትቶ የማሕበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ማፍጠጥ፤ አ...

Phillip Holmes - avatar Phillip Holmes

ጨርሰው ያንብቡ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች እና ሥነ መለኮታዊ ትምህርቶችን የማስተማ…

ለመኖር ብቸኛው ምክንያት ትልቅ ስፍራ የሰጣችሁትን ነገር ማሳካት ነው። ማንኛውም ሰው ትልቅ ዋጋ ባለው ነገር ፈንታ ላነሰ ነገር ሲል መቼም ቢሆን ዋጋ መክፈል ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.