Tuesday, 19 March 2024

ብዙ ክርስቲያኖች ደስተኛ ያልሆኑት ለምንድን ነው?

Posted On %PM, %10 %844 %2016 %22:%Dec Written by

ለምንድን ነው ብዙ ክርስቲያኖች ደስተኛ ያልሆኑት?

ደስታ የደህንነት ስሜት ነው። “. . .  የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል” (1 ጴጥሮስ 1፡8-9) ። ክርስቲያን ከሆናችሁ መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ እንድትደሰቱ ያደርጋችኋል። ውበቱ እና ታላቅነቱ ነፍሳችሁን ያስደንቃታል። 

ነገር ግን በጣም ጥቂት ክርስቲያኖች ብቻ ደስታን ለመለማመድ ይሞክራሉ። ይህ ለምን ይሆን?

አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮአቸው ወደ ሀዘን ያደላሉና ደስታ ቋሚ ፈተና ይሆንባቸዋል። የማርቲን ሎይድን አንድ የቆየ “መንፈሳዊ ቁዘማ” (Spritual Depression) የሚል መጽሃፍ ሳነብ ባህሪን እና ስብዕናን ዋነኛ ምክንያቶች አድርጎ ስላቀረባቸው ስደነቅ ነበር። ልክ ነው ብዬ አስባለሁ።

ይሁን እንጂ ሌላም ምክኒያቶች አሉ። ወጣት እናቶች በቀላሉ በመድከማቸው እና እንቅልፍ በማጣታቸው ደስታን ለማግኘት ትግል ይሆንባቸዋል። በሀዘን ወይንም በመከራ ውስጥ ካላችሁ እግዚአብሔር ባላችሁበት ሁኔታ ውስጥ ደስታ እንዳዘጋጀላችሁ ላታውቁ ትችላላችሁ። ጠላታችን እንደሚጠላንና ከደስታችን የሚቻለውን ያህል አሟጦ እንደሚሰርቅብን ማስታወስ አለባችሁ።

በጣም አሳዛኝ ክርስቲያኖችን ያየሁት ግን በሁለቱም ዓለማት ውስጥ የሚኖሩትን ነው።

አንድ አይናቸውን ሰማይ ላይ አንድ አይናቸውን ደግሞ ምድር ላይ ይተክላሉ። የክርስቶስን ስም ይጠራሉ ጥበቃን፣ እርካታን፣ ደስታን መሳካትን ደግሞ ከምድር ላይ ይሻሉ። አቋም ስለሌላቸው ደስተኞች አይደሉም። 

ይሄ እናንተ ናችሁን? ብቸኛው ደስታን ማግኛ መንገድ ለእግዚአብሔር ሙሉ እሺታን መስጠት ነው። ይህም ማለት ለዓለም እንቢ ስንል ነው። 

ትልቁ እሺታ

እያንዳንዱ ክርስቲያን እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ ማወቅ አለበት። እግዚአብሔር ብቻ መልካም ነው ከዚህ በላይ ምን አለ?

እግዚአብሔር ብቻ መልካም እንደሆነ ካላወቅን ደስታን እንደሚሰጡ ቃል ገብተው ግን ምሬትን ብቻ ለሚሰጡ ለሌላ አማልክት እንቢ ማለት አንችልም። ከእግዚአብሔር ውጪ የሆነ ቁራጭ እንኳን መልካም አለ ብለን ልናስብ መድፈር የለብንም።

መዝሙረ ዳዊት ይህንን እውነታ ይናገራል። 

እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም ። (መዝሙር 16፡2)

እንደገናም፡- 

በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? (መዝሙር 73፡25)

አሁንም እንደገና፡-

አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ። አንተ ተስፋዬ ነህ፥ በሕያዋንም ምድር አንተ እድል ፈንታዬ ነህ አልሁ። (መዝሙር 142፡5)

በአዲስ ኪዳንም ያዕቆብ ሲጽፍ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። (ያዕቆብ 1፡16-17)

እያንዳንዱ በዚህ ምድር ላይ ያለ መልካም ነገር የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው። ከእግዚአብሔር ካልመጣ ምንም ነገር መልካም ሊሆን አይችልም። ደስተኛ ክርስቲያን ይህን እውነት ያምናል። ህይወቱን እና ደስታውን በዚህ ላይ ያኖራል። 

ካልቪን እንደዚህ ይላል፡-


የእውነት ሁሉ ምንጭ እንደሆነ ካላመንን እና ከእርሱ ውጪ ምንም ላለመፈለግ ካልወሰንን ሁሉም ክብር ሊሰጠው የሚገባ አንድ እንዳለ ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም። ሰዎች ነገራቸው ሁሉ ከእግዚአብሔር የመጣ እንደሆነ ካላመኑ፣ በአባትነቱ እንክብካቤ እስካልረሰረሱ፣ የመልካም ነገር ሁሉ ጸሐፊ እርሱ እንደሆነ እስካላመኑ፣ ከእርሱ ውጪ ሌላ ነገርን መፈለግ እስካላቆሙ ድረስ ለፍቃዱ ተገዢ አይሆኑም። ሙሉ ደስታቸውን በእርሱ ላይ እስካልመሰረቱ ድረስ ሙሉ በሙሉ ሁለንተናቸውን የእውነት ሊሰጡት አየይችሉም። (ኢንስቲትዩትስ 1፣2፣1)


እግዚአብሔር መልካም ነው። እግዚአብሔር ብቻ መልካም ነው። ሁሉም መልካም ነገር የሚመጣው ከእርሱ ነው።

ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር እራሱን ሰጥቶናል። እርሱ ደስታችን ነው፤ ሊገለጽ የማይችል የልባችን ደስታ። ዳዊት ሲናገር

“የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ”። (መዝሙር 16፡11)

ትልቁ እንቢታ

ሰይጣን ከእግዚአብሔር ውጪ ደስታን እና እርካታን ልናገኝ እንችላለን ብለን እንድናስብ ይፈትነናል። እኛ ግን ከእግዚአብሔር ውጪ መልካም ነገርን ቃል ለሚገቡልን ነገሮች በሙሉ ጠንካራ እንቢታ ልንሰጥ ይገባናል። ይህ “እንቢታ” የክርስትና ደስታ ሥሩ ነው።

የኃጢያት መሰረቱ ከእግዚአብሔር እና ከፍቃዱ ውጪ መልካምን ነገር መፈለግ ነው። እናታችን ሄዋንም የተታለለችው እንዲሁ ነው።

ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች ከፍሬውም ወሰደችና  በላች ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። (ዘፍጥረት 3፡6)

እኛም ልክ እንደእርሷ በተመሳሳይ መንገድ እንሰናከላለን። ከእያንዳንዱ ኃጢያቴ ጀርባ ምን እንዳለ ስፈልግ የማገኘው ምክንያት ከእግዚአብሔር እና ከመንገዱ ውጪ መልካምነት እየፈለግሁ ስላለው ነው። ይህ ምፈልገው መልካም ነገር ደስታ፣ ጥበቃ፣ ተቀባይነት፣ እርካታ፣ ፍትህ፣ ንብረት፣ ድሎት፣ ቁሳዊ ፍላጎት ወዘተ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ላገኝ የጣርኩት ከእግዚአብሔር ውጪ ነው።

ሲጠቀለል ይሄ ጣዖት አምልኮ ነው። ከእግዚአብሔር ውጪ ፍላጎቶቼን ሊያሟሉልኝ እና መሻቶቼን ሊያረኩልኝ የሚችሉ ነገሮች እየፈለግሁ ነውና። እነዚህ ጣዖቶች ደስታን እንደሚያመጡ ተስፋ ቢሰጡም መጨረሻቸው ግን ምሬት ነው። 

ለዚህ ነው ግማሽ ልብ ያለው ክርስቲያን በክርስቶስ ላይ የሚቀጥል ደስታ ሊኖረው የማይችለው። ዳዊት ሲናገር 

“ወደ ሌላ ለሚፋጠኑት መከራቸው ይበዛል የቍርባናቸውን ደም እኔ አላፈስሰውም፥ ስማቸውንም በከንፈሬ አልጠራም” (መዝሙር 16፡4) ይላል።

ደግሞም ሲናገር 

ሕይወቴ በኅዘን አልቃለችና፥ ዓመታቴም በልቅሶ ጩኸት ኃይሌ በችግር ደከመ፥ አጥንቶቼም ተነዋወጡ (መዝሙር 30፡10) ይላል።

ወደሌላ አማልክት ደስታን ፍለጋ እንሮጣለን የምናገኘው ግን መራራ ሃዘን ነው።

አንዲት ወጣት ሴት ክርስቲያን ያልሆነ ወንድ ማግባት እንደሌለባት ታውቃለች። ነገር ግን እግዚአብሔር ባይኖርበትም በዚህ ግንኙነት ውስጥ ፍቅር እና ጥበቃ እንደምታገኝ ታስባለች። መልካምን ነገር ትፈልጋለች። ነገር ግን እንዲያሟላላት ወደ ሌላ አምላክ ስለምትዞር ሃዘንዋ ይበዛል። 

አንድ ወንድ በፖርኖግራፊ (ራቁት ምስል ፊልም) ውስጥ የመሟላት ስሜትን ሚያገኝ ይመስለዋል። በእግዚአብሔር መንገድ ሲሆን ወሲባዊ ደስታ መልካም ነገር ነው። ይሁን እንጂ ይህ ሰው ደስታውን ለማግኘት ወደ ሌላ አምላክ እየተመለከተ ነው። አነዚህ ለሰከንዶች የሚቆዩ ደስታዎች በፊቱ ወደምንምነት ይቀየራሉ።

አንድ ሴት በሃሜት ተቀባይነትን ለማግኘት ትሞክራለች። ሌሎች ሰዎች ስለሚያደርጉት ነገር ስታወራ ተፈላጊነት ስሜት ይሰማታል። በክርስቶስ ያላትን ዋጋ እየፈለገች አይደለም። ዋጋዋን ለማግኘት ወደ ሌላ አምላክ እየሮጠች ነው።

ይቅርታ የማያደርግ ሰው ቂም ይይዛል። ነገሮችን ማስተካከል የእርሱ ኃላፊነት ይመስለዋል። ፍትህ መልካም ነገር ሆኖ ሳለ በምድር ሁሉ ላይ ፈራጅ ወደሆነው ሳሆን ወደሌላ አምላክ እየሮጠ ነው።

ስለዚህ ዛሬ የምታመልኩትን ምረጡ። በሕይወታችሁ ለሚሆን ለማንኛውም ነገር ወደ እግዚአብሔር እና ወደ መንገዱ ተመልከቱ። ከመዝሙረኛው ጋር አብራችሁ “እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ” (መዝሙር 16፡5) በሉ።

ግማሽ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ደስተኛ ክርስቲያኖች አይደሉም። በእግዚአብሔር ታመኑ ወደ ሌላ አማልክትም አትሂዱ። ይህ ነው የደስታ መንገድ።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %30 %785 %2017 %20:%Jan
Jim Johnston

Jim Johnston Jim Johnston is senior pastor of Tulsa Bible Church in Tulsa, Oklahoma, and the author of The Psalms: Rejoice, the Lord Is King (Crossway, 2015). He and his wife, Lisa, have four teenage children.

የ"ዋቄፈና" እምነት ምንድን ነው? የዋቄፈና እም…

"ይሄ ደሞ ምንድን ነው?" አልኩት በእጄ የሆራ አርሰዲ ዙሪያ ረግረጉን ይዞ የበቀለውን ሳር ቀንጥሼ ውሃው ውስጥ እየነከርኩ። ስለማደርገው ነገር ምንም አልገባኝ...

Naol Befkadu - avatar Naol Befkadu

ጨርሰው ያንብቡ

ታላቅ ሽልማት

በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ከሚያስቸግረኝ ነገር ውስጥ በክርስትና ሕይወት ውስጥ መሠረታዊ በሚባለው የግል የጥሞና ጊዜ ውስጥ ነፃነት ማግኘት ነው። በእርግጥ አላደርጋቸ...

Tim Challies - avatar Tim Challies

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.