Monday, 15 July 2024

አንድ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ሊሳደብ ይችላልን?

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ፓስተር ጆን እንደ ጥያቄ ለደረሰው ኢሜል ምላሽ ከሰጠበት ቃለ መጠይቅ በጽሁፍ የተወሰደ።

ሰላም ፓስተር ጆን። ይቅር ስለማይባለው መንፈስ ቅዱስን የመሳደብ ኃጢያት የጻፍከውን ጽሁፍ አንብቤአለሁ። እናም ሁለት ጥያቄዎች አሉኝ:-

1. ደኅንነቱ በክርስቶስ ለዘላለም እርግጥ የሆነ አንድ እውነተኛ አማኝ ከማመኑ በፊት መንፈስ ቅዱስን ለተሳደበበት አሁንም ጥፋተኛ ይባላል?

2. መንፈስ ቅደሱስን መሳደብ እና ማሳዘን አንድ ናቸው?

ስለምን እያወራን እንደሆነ ግልጽ ይሆንልን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ስለሚለው ሀረግ የተወሰኑ ቁልፍ ጥቅሶችን ከፊታችን እናድርግ። በማርቆስ 3፡28-30 ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም። ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉም ነበርና።” በሌላ አገላለጽ የኢየሱስን ሥራ በውስጡ ላለው ለእግዚአብሔር ከመስጠት ይልቅ ለሰይጣን እየሰጡ ነበር።

አንድ ሌላ ተጨማሪ ጥቅስ ደግሞ በ ሉቃስ 12፡10 ላይ ሲናገር “በሰው ልጅም ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሰድብ ግን አይሰረይለትም”። በአገልግሎት ዘመኔ ሁሉ በዛ የሚል ቁጥር ያላቸው ሰዎች (ቁጥሩ አጅግ ብዙ ባይሆንም) በመንፈስ ቅዱስ ላይ ይህን ኃጢያት እንዳደረጉ አምነው ይቅርታ ሊደረግላቸው እንደማይችሉ በማመን በታላቅ ፍርሀት ውስጥ ወድቀው ወደ እኔ መጥተው ያውቃሉ። ብዙዎች ወደ ፊት መውጣት ባይፈልጉም እነዚህ ግን መጥተዋል።

ስለዚህ እንደዚህ የሚሉትን ሰዎች ለመርዳት “መንፈስ ቅዱስን የተሳደበ ኃጢያቱ አይሰረይለትም” ተብሎ ከተቀመጠው ሃሳብ በተጓዳኝ ማንም በኢየሱስ ቢያምን ይድናል የሚሉትን አይነት ጥቅሶች አብረን ማስቀመጥ እንዳለብን ይሰማኛል። አስተውሉ ሌላ ነገሮችን ሳታደርግ ብታምን አይልም። ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ 16፡31 ላይ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት” ይላል። ጳውሎስ የእስር ቤቱን ጠባቂ መንፈስ ቅዱስን ተሳድበህ ታውቃለህ? ብሎ አልጠየቀውም። ያለው እመን ትድናለህ ብቻ ነው። በዮሐንስ 6፡40 ላይ ኢየሱስ “ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ” ብሎ ይናገራል።

ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ስለመሳደብ ሲናገር እንድናውቀው የፈለገው ነገር ንስሀ ለመግባት እና ለማመን እንቢ እስከማለት የኃጢያት ደረጃ ላይ ስለደረሱ ሰዎች ይመስለኛል። ለዚህ ነው አሁን ሁለቱን አንድ ላይ የማደርጋቸው። ዔሳው ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። በዕብራውያን 12፡17 ላይ ሲናገር “ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና” ይላል። ለንስሃ ስፍራ አላገኘም ሲል ሊያደርገው አልቻለም ማለቱ ይመስለኛል። ምንም እንኳ በእንባ ተግቶ ቢፈልገው ለእውነተኛ ንስሃ ግን በልቡ ውስጥ ምንም ስፍራ አላገኘም። 

ስለዚህ ዋናው ነጥብ እዚህ ጋር ዔሳው ንስሀ ገብቶ ይቅር ሊባል አለመቻሉ አይደለም ነገር ግን ለንሰሃ ስፍራ አለማግኘቱ ነው። ብኩርናውን በምስር ወጥ እሲኪለውጥ ድረስ በእግዚአብሔር ላይም ልቡ ወደመደንደን እስኪደረስ ድረስ ለዚህ ዓለም ታላቅ ፍቅር ነበረው። ዓለምን ከመውደዱ ብዛት ዓለምን መውደድ ሊያቆም አልቻለም ነበር። እውነተኛ ንስሀ ማግኘት አልቻለም ነበር። ስለዚህ ጠፋ። ለቅሶው ግን የንስሃ እንባ አልነበረም። ንሰሀ ሊገባ ያለመቻሉ ጸጸት እንባዎች ናቸው።

ሄነሪ አልፎርድ ከሚባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ይቅር ስለማይባለው ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን የመሳደብ ኃጢያት ከጻፈው ውስጥ አንድ ክፍል ላካፍላችሁ። እንደዚህ ነበር ያለው:- 

እዚህ ጋር ፤ ይሄን ኃጢያት አድርጌአለሁ ወይስ አላረደረግሁም?  ማለት እንድንችል አይነት፣ አንድን የተወሰነ ኃጢያት አይደለም እየወቀሰ ያለው። ነገር ግን በመሳደብ ፍሬ ስለሚታየው በራስ ፍቃድ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልን የመቃወም የኃጢያት ደረጃን የሚያሳይ ነው። አዲስ ኪዳን ደጋግሞ ለሚናገረው ነገር ሥጋ የለበሰ ድንጋጌ ነው።


ይሄን ኃጢያት አድርጌአለሁ ወይስ አላረደረግሁም?  ማለት እንድንችል አይነት፣ አንድን የተወሰነ ኃጢያት አይደለም እየወቀሰ ያለው። ነገር ግን በመሳደብ ፍሬ ስለሚታየው በራስ ፍቃድ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልን የመቃወም የኃጢያት ደረጃን የሚያሳይ ነው። አዲስ ኪዳን ደጋግሞ ለሚናገረው ነገር ሥጋ የለበሰ ድንጋጌ ነው።


ዋናው ቁልፍ ሀረግ እዚህ ጋር “በራስ ፍቃድ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልን የመቃወም የኃጢያት ደረጃ” የሚለው ነው። ቀጥሎም እንደ ሌሎቹ የአዲስ ኪዳን ስፍራዎች 1ዮሐንስ 5፡16 ላይ ያለውን “ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም” የሚለውን ክፍል ደግሞ ይሰጠናል። ስለ አንድ ኃጢያት “ሞት የሚገባው አንዲህ ያለ ኃጢያት አለ” ብለን ሳይሆን “ኃጢያት አለ” ብለን እንድንረዳው ነው የሚያስፈልገው። መንፈሱን እና እርሱን እራሱን እግዚአብሔርን በፍቃዱ የሚቃወም ቆራጥ ጠላትነት የሆነ ኃጢያት አይነት አለ።

ስለዚህ ለሁለቱ ጥያቄዎች መልሶቼ እኚህ ናቸው:-

1. ደኅንነቱ በክርስቶስ ለዘላለም እርግጥ የሆነ አንድ እውነተኛ አማኝ በፊት መንፈስ ቅዱስን ለተሳደበበት አሁንም ጥፋተኛ ሊባል ይችላል? አይችልም። ምክንያቱም አልፎርድ እንዳለው እኔም ደግሞ የማምነው መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ማለት መንፈስ ቅዱስ አሁን የሚሰራበትን ኃይል በፍቃድ የመቃወም መነሳሳት ስለሆነ። ክርስቲያኖች ደግሞ እንደዚህ ያለውን ኃጢያት ሊፈጽሙ አይችሉም። ፍቃደኛ ሆነው እግዚአብሔርን በመቃወም ኑሮ ውስጥ ጸንተው ሊኖሩ አይችሉም።

2. መንፈስ ቅዱስን መሳደብ እና ማሳዘን አንድ ናቸው? አይደሉም። ልዩነታቸውን ደግሞ በ ኤፌሶን 4፡29-31 ላይ “ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።” ብሎ ጳውሎስ ከጻፈው ማየት እንችላለን።

እዚህ ጋር ሁለት ነጥቦችን ማንሳት እንችላለን። አንደኛ መንፈስ ቅዱስን ስናሳዝን ጳውሎስ እንደሚለው እያሳዘንን ያለነው ለቤዛ ቀን የታተምንበትን መንፈስ ነው እያሳዘንን ያለነው። ይህም ማለት ልታሳዝኑት ትችላላችሁ ባለበት አንደበት ደኅንነታችሁ ተጠብቋል እያለን ነው። ታትማችኋል። የታተማችሁበትን ማህተም ደግሞ አይከፍተውም። ይዟችሁ ለቤዛነት ቀን እየጠበቃችሁ ነው።

ሌላኛው ደግሞ ልናስተውለው የምንችለው ነገር የሚያሳዝኑት ነገሮች ምን እንደሆኑ ነው። የሚያሳዝኑት ነገሮች በሌሎች ላይ ያለ ቁጣ እና መራርነት ነው። እነዚህን ነገሮች ደግሞ ክርስቲያኖች ያደርጓቸዋል እናም በማድረጋቸውም ደግሞ ይጸጸታሉ።ይህንንም በማድረጋቸው ደግሞ ንሰሃ ሊገቡ እና ይቅርታ ሊጠይቁ ያስፈልጋል። ንስሀ ደግሞ ለቤዛ ቀን ተጠብቀን እንቆይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በምህረቱ የእግዚአብሔርን ልጆች የሚያነቃበት ሥራ ነው።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %897 %2016 %23:%Dec
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ

የሰው ህይወት በምድር ላይ ብዙ ሰልፍ፣ ብዙ መከራ፣ ብዙ ፈተና እንዳለበት የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። የመከራውም ሆነ የፈተናው ዓይነት ብዛቱም ሆነ ዐይነቱ ...

Eyob B Kassa - avatar Eyob B Kassa

ጨርሰው ያንብቡ

ምኞትን ለመዋጋት የሚጠቅሙ ስልቶች

ይህን ስጽፍ ወንዶችንም እና ሴቶችንም በማሰብ ነው። ለወንዶች በእርግጥ ግልጽ ነው። በወሲባዊ ምስሎች የሚመጣ ፈተናን ለማጥፋት የሚደረግ ውጊያ አስፈላጊ ነው። ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.