Monday, 15 July 2024

የሚያበረቱ 10 የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

Posted On %AM, %16 %041 %2017 %03:%Feb Written by

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናት የምናሳልፈው ጊዜ ውድ እና ያልባከነ ጊዜ ነው። ረጃጅም ክፍሎችን እያጠናችሁ ቢሆን ወይንም ለአንድ ኃጢያት የሚሆን የውጊያ ጥቅስ አሊያም ለመጋቢ አገልግሎትዎ የሚሆኑ ምንባቦች ቢሆኑ በእርግጥም እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት “ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማሉ” (2 ጢሞቴዎስ 3፡16)

በተለይ ደግሞ አንድ መስመር “የወንጌል ጥቅሶች” እጅግ ጠቃሚዎች ናቸው።

ወንጌልን የሚገልጹ ጥቅሶችን በቃላችሁ ስታጠኑ ደግሞም አጥብቃችሁ ስትይዙት በልባችሁ የሰወራችሁት የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን ያልተሳሳተ በሰው ልጆች ቋንቋ የተገለጸ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የታሪክን ሙሉ ገጽታ ነው። በውስጣችሁ የያዛችሁት ጠንካራ የሆነውን የመንፈስን  ሰይፍ ነው። አንድ መስመር የወንጌል ጠቅላላ ፍሬ ሃሳብ መንፈሳዊ የጀርባ አጥንታችንን አጠንክሮ የእኛን ፍሬ ነገራችንን ተጨባጭ በማድረግ በእግዚአብሔር ጥልቅ ልብ ውስጥ እና በፈጠረው ዓለም ውስጥ እየተከለን የእኛም ይሁን የሌሎችን አለማመን እንድንዋጋ ወደ ውጊያ እንድንሄድ ያደርገናል። የወንጌል ጥቅሶች በወንጌል ሥርጭት ሆነ በደቀ መዝሙርነት ዋጋቸው እጅግ የላቀ ነው።

ስለዚህ ከሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናታችሁ በተጨማሪ ሙሉ ክምችታችሁን ሊመሩላችሁ ሊቀርጹላችሁ እና ቃናውን ሊቀይሩ የሚችሉትን “የወንጌል ጥቅሶች” ጨምሩባቸው። የወንጌል ጥቅሶች ስንል እንደ ዮሐንስ 3፡16 ያሉትን ኢየሱስ ኃጢያተኞችን እንደሚያድን በግልጽ የሚናገሩ ጥቅሶችን ነው። 

ለመጀመር ያህል አስር ዝርዝሮች እነሆ። እግረ መንገዳችሁን ሌሎችን መጨምር እንድትችሉ ዓይኖቻችሁን ክፍት አድርጉ። ከሮሜ መጽሐፍ ብዙ ብታገኙ እንዳትደነቁ።

(ማርቆስ 10፡45) “እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”

(ሮሜ 5፡8) “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”

(ሮሜ 6፡23) “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”

(ሮሜ 8፡1) “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።”

(ሮሜ 8፡32) "ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?"

(2 ቆሮንቶስ 5፡21) “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።”

(2 ቆሮንቶስ) “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።”

(1 ጢሞቴዎስ) “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ ።”

(1 ዮሐንስ 4፡10) “ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”

(ራዕይ 5፡9) “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ . . .”

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %17 %781 %2017 %20:%Feb
David Mathis

David Mathis is executive editor for desiringGod.org, pastor at Cities Church in Minneapolis/Saint Paul, and adjunct professor for Bethlehem College & Seminary. He is author of Habits of Grace: Enjoying Jesus through the Spiritual Disciplines.

https://twitter.com/davidcmathis

ፖርኖግራፊ ምንድን ነው?

ከፓርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል! ክፍል አንድ - ፖርኖግራፊ ምንድን ነው?  በአንድ ወቅት ‘ጉግል’ አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈል...

Ermias Kiros - avatar Ermias Kiros

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.