Friday, 29 March 2024

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና”። (ኤፌሶን 2፡4-5)

ነገር ግን እግዚአብሔር” የሚሉት እኚህ 3 ቃላት በወንጌል የተትረፈረፉ ናቸው። እንደኔና እንደእናንተ ላሉት ጠፍተው ለነበሩ፤ እራሳቸውን ከእግዚአብሔር ላይ ከተደቀነ አመፃ ሊያድኑ የማይችሉ ኃጢያተኞች ከእነዚህ የዘለሉ ሌላ ሦስት የተስፋ ቃላት ላይኖሩን ይችላል። 

አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። (መዝሙር 51፡10-12)

ያጣችሁት ነገር ላይ ዓይንን እንደመጣል እምነትን የሚያደክም ነገር የለም። 

እንደተረዳሁት ከሆነ ዓይኖቼን በቁሳዊ ማጣቶቼ ላይ ፣ በሌሉኝ ጥንካሬዎች እና በሌሉኝ ድክመቶች ላይ ባደረግሁ ጊዜ ያለማመን ሸክም ይከብድብኝና ሩጫዬን ከባድ ያደርግብኛል (ዕብራዊያን 12፡1)። 

መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቸር አምላክ እንደሆነ ይናገራል። ብዙ ሰዎች ግን ይህንን ለማመን ይቸገራሉ። አንዳንዶች ጸጋ ምን እንደሚመስል ሲያስቡ ይገረማሉ። የእግዚአብሔርን ጽድቅና የእኛን የየዕለት አስከፊ ኃጢያት በጥልቀት ብናስብ እግዚአብሔርን “አሁንም ትወደኛለህ ወይ?” ወይንም “ለምንድን ነው እንደዚህ የታገስከኝ?” ወይንም “ስላደረግሁት ነገር ስለምን አልገደልከኝም?” ብለን  ስንጠይቅ እራሳችንን ልናገኘው እንችላለን።

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንደሆነ መቶ በመቶ ብታምኑ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? እንደተቀበላችሁ ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ማንነት እና ሥራ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እንደተቀበላችሁ ብታምኑ? ታላቅ የምትሉት ስኬታችሁ የተለየ ወደ እርሱ እንደማያቀርባችሁ ወይንም የመጨረሻው ውድቀታችሁ የቱንም ከእናንተ እንደማይወስድ ብታምኑስ? ይህን ብታምኑ ፤ በእርግጥ ብታምኑ በሕይወታችሁ ውስጥ ለደስታ ያላችሁን ፍለጋ ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል።

በርባን እና እኔ

ህዝቡ ሁሉ የኢየሱስን መሰቀል ይጠይቃል። በትረካው ውስጥ ማንን አያችሁ?

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

አንቀፅ 17፣ ነፃነት/ባርነት — ከአድዋ - ጎልጎታ

ይህ ታሪክ ከተፈፀመ እነሆ በዛሬዉ 122ኛ ዓመቱን ይዟል። ይህ ቀን ለአሁኗ ኢትዮጵያ ማንነቷን ያስጠበቀችበት፣ ከባርነት ራሷን ነፃ ያደረገችበት ቀን ነው። ከመ...

Misgana Kibret - avatar Misgana Kibret

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.