Sunday, 28 April 2024

አሮጌው እኔ አዲስ ሲሆን

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። (መዝሙር 51፡10-12)

በመጀመሪያ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሰምተን ስንቀበል ኃጢያታችን ይቅር መባሉ ሀፍረታችንም መወገዱ ያረካናል። ሃያል እና ሁሉን አዋቂ የሆነን አምላክ መበደል ያለውን ችግር ስለምንረዳ ካጠፋነው ጥፋት ብዛት የከበደ ሸክማችን ሲነሳልን ይሰማናል። በአንድ በኩል አሁንም በውስጣችን የሚመላለስ የቀረ ኃጢያት፤ የቀረ ሥራ እንዳለ እናውቃለን። ነገር ግን ይቅር እንደተባልን ማወቁ በራሱ የበለጠ ሃይል አለው። 

ኢየሱስ ከኃጢያት ይቅርታ በላይ ከሆነ የሞተው?

የወንጌሉ የምስራች በይቅርታ ብቻ አያቆምም። ጸጋን ላጠፋነው ማንኛውም ስህተት ማጥፊያ የሚሆን የእግዚአብሔር ትልቅ ላጲስ አድርገን እናስበዋለን። ነገር ግን እግዚአብሔር ገጹን ንጹህ አድርጎ ብቻ ሊተወው አይደለም ሃሳቡ። ነገር ግን አላማው በኃጢያት ምትክ ቀድሞ ተሰብሮ፣ ተበላሽቶ እና ሞቶ የነበረውን በፍቅር በታማኝነትና በሕይወት ቀይሮ ሊጽፈው ነው።

ወንጌል ከሲዖል ማስመለጥ ብቻ አይደለም የሚሰራው፤ አዲስም ደግሞ ያደርገናል። ጸጋ የሚረዳን ያለፈውን ኃጢያታችንን እንድናስወግድ ብቻ አይደለም  ነገር ግን አዲስ እንደሆንን እና አዲሰ ሆነን እንድንኖር ይረዳናል።

ከምናስበው በላይ ኃጢያተኞች ነን 

ዳዊት ሲናገር “እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና” ይላል (መዝሙር 51፡3)። በሰገነቱ ላይ ሆኖ አንዲት ያገባች ሴት ስትታጠብ ያያል (2 ሳሙኤል 11፡2) ተመኛት ወደ እርሱም አስገባት አብሯትም ተኛ (11፡4) ሴቲቱም አረገዘች (11፡5)። ኃጢያቱንም ለመሸፈን ባሏን ከጦር ሜዳ አስመጥቶ እንዲተኙ አሰበ (11፡9-13)። ይህ አልሆንለት ሲለው ባሏ በጦርነት መሃል እንዲሞት መከረ (11፡5) ጥፋቱን ለመሸፈን ሲል ንጹህ ሰው ገደለ።

ናታንም ስለዚህ ነገር ፊት ለፊት ተቃወመው (12፡1-14)። ዳዊት ይህንን መዝሙር በሚጽፍበት ጊዜ ስላጠፋው ኃጢያት ሁሉ ስለልቡ ኃጢያት እና አመጻ ያውቃል።

ወይስ በእርግጥ ያውቅ ነበር? “እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” (መዝሙር 51፡5)። መዘሞቱ፣ መዋሸቱ እና ማስገደሉ ሁሉ የሌላ ጥልቅ የሆነ ትልቅ ችግር ምልክቶች ናቸው። ዳዊት ከስሩ ኃጢያተኛ ነው። ከልጅነቱም ብቻ ሳይሆን ከዛም በፊት ኃጢያተኛ ነበር። ኃጢያት ልናውቅ እና ልናምን ከምንችለው በላይ በክሎን ሽባ አድርጎናል።

ከኃጢያታችን ሁሉ የሚበልጥ ጸጋ

ዳዊት ኃጢያት ትልቅ ነገር እንደሆነ ያውቃል። ነገር ግን ከኃጢያቶቹ ሁሉ የሚበልጥ ነገር ያውቃል። “አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ" ይላል። (መዝሙር 51፡1) ኃጢያተኞች በፊቱ ያለ ፍርሃት በድፍረት መሆን የሚችሉበትን ነገር እግዚአብሔር ስለራሱ ገልጾአል። ዳዊት በአስከፊ ነፍስ የመግደል ኃጢያት ውስጥ አንደወደቀ ያውቃል። ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ፊት ይቅርታ ለመጠየቅና ለመንፃት በድፍረት ይቀርባል። ከዚያ በፊት ነገሮችን ለማስተካከል ሞክሮ እንደሚያውቀው ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር ብዛት ይቅርታን ይጠይቃል ይማጸናልም።

ፀሎቱ በይቅርታ ሳይሆን የሚያልቀው (መዝሙር 51፡1) በመታደስ ነው። ከይቅርታ አልፎ የሚበልጥን ነገር ይጠይቃል። “በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ.  . . አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” (መዝሙር 51፡7፤ 10) እያለ ይጸልያል። እግዚአብሔር ሆይ መለወጥ እሻለሁ። መልካም እና ጥሩ የሆነውን መውደድ እፈልጋለሁ። ከእዚህ በተለየ መልኩ መኖር እፈልጋለሁ። አንተ በምትወድበት አይነት ፍቅር መውደድ እፈልጋለሁ። ከሲዖል ውስጥ ባወጣኸኝ ተመሳሳይ ጸጋህ እባክህ አዲስ አድርገኝ። 

የዳነ ሕይወት አላማው ዳግም ሲታደስ

በመዝሙር 51 ንድፍ ውስጥ ይቅር የሚል ደግሞም የሚለውጠው ይህ ጸጋ በመላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ በተደጋጋሚ ይታያል። 

ለምሳሌ ፊሊጵስዩሰ ክርስቶስ እራሱን እስከ መስቀል ሞት ድረስ እንዳዋረደ ይናገራል (ፊሊጵስዩሰ 2፡8) ። በእኛ ምትክ ሞታችንን ሞተልን። “ስለዚህ” ይላል ጳውሎስ ሲጽፍ “ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ” (ፊሊጵስዩሰ 2፡12)። ግን እንዴት? ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። በሃይሉ ያዳነን እግዚአብሔር እርሱን የበለጠ በመምሰል እንድንኖር ደግሞ ያስችለናል።

ወይንም ደግሞ ጴጥሮስ በመጀመሪያ መልዕክቱ በደኅንነታችን ላይ እግዚአብሔር ስላለው ክብር በተደጋጋሚ ሲገልጽ የሞተውን ነፍሳችንን በአዲስ ሕይወት አስነስቶ እምነታችንን እና ደስታችንን ለዘለአለም እንደተጠበቀልን ይናገራል (1 ጴጥሮስ 1፡3-6)። እንግዲህ በዚህ ሕይወት የቀረልን ምን ሥራ የለም? ጴጥሮስ ቀጥሎ ሲጽፍ “እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።ዳሩ ግን፤ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ (1 ጴጥሮስ 1፡14-15) ይላል። እግዚአብሔር ባዳናቸው ውስጥ የእርሱ ቅድስና ይታያል። ልክ እንደእርሱ ያለ አዲስን ልብ በውስጣቸው ያኖራል።

እግዚአብሔር በልባችሁ ውስጥ ያለውን አስቀያሚነት ባሳያችሁ ቁጥር ይቅር እንዲላችሁ ነገር ግን አዲስ እንዲያረጋችሁም ደግሞ ጠይቁት። በይቅርታ ውስጥ የሚሰጠው ጸጋ ከምናስበው በላይ ታላቅ ቢሆንም ከዛ በላይ ጸጋ ግን ሊሰጠን የተስፋ ቃሉን ሰጥቶናል። አዳኛችን የሆነውን ታላቁን መዝገባችንን ስንመለከት “እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን” (2 ቆሮንቶስ 3፡18) ። ይሄ ነው አሮጌው እኔ አዲስ ሲሆን። 

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %850 %2016 %22:%Dec
Marshall Segal

Marshall Segal is a writer and managing editor at desiringGod.org. He’s the author of Not Yet Married: The Pursuit of Joy in Singleness & Dating (2017). He graduated from Bethlehem College & Seminary. He and his wife Faye have a son and live in Minneapolis.

twitter.com/marshallsegal

ጳውሎስ ነፍሰ ገዳይ እንዲሆን እግዚአብሔር ለምን ፈቀደለት

ጳውሎስ ገና ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔር ለሐዋርያነት እንደለየው እናውቃለን። “ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

ዓለም ሊነገራት የሚያስፈልገው ነገር

ቻርልስ ስፐርጅን:-  ማለት የምፈልገው ነገር ሁሉ ሲጨመቅ ይህ ነው:- ወንድሜ ክርስቶስን ሁልጊዜ ስበክ ። እርሱ ሙሉው ወንጌል ነው ። ማንነቱ ፣ ሹመቱ እና...

Jonathan Parnell - avatar Jonathan Parnell

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.