Tuesday, 22 October 2024

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናት የምናሳልፈው ጊዜ ውድ እና ያልባከነ ጊዜ ነው። ረጃጅም ክፍሎችን እያጠናችሁ ቢሆን ወይንም ለአንድ ኃጢያት የሚሆን የውጊያ ጥቅስ አሊያም ለመጋቢ አገልግሎትዎ የሚሆኑ ምንባቦች ቢሆኑ በእርግጥም እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት “ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማሉ” (2 ጢሞቴዎስ 3፡16)

መጽሐፍ ቅዱሳችንን ልናነብብ ስንከፍት ለብቻችንን አይደለንም ። መንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ ክብር ሲል ልባችንን ሊያነሳሳ አዕምሮአችንን ሊያበራ ሕይወታችንን ሊቀይስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሰፍፎ አለ (ዮሐንስ 16፡14) ። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ዋነኛው መስፈርት መንፈስ ቅዱስ ነው ። ተራ የሚመስልን ነገር ወደ ኃያል ነገር ይቀይረዋል ። ስለዚህም ለዓይኖቻችን ለአዕምኖአችን እና ለልባችን ሳንጸልይ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ ሞኝነት ይሆንብናል ።

የእያንዳንዱ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ከመነበብ ብዛት ያረጀ፤ በየቦታው የተሰመረበት፤ በተለያዩ ቀለማት የተፃፉ መንፈሳዊ ሃሳቦችን የያዘ ማስታወሻ አብሮት ያለ ደግሞ ይመስለናል። ይህ ግን በአብዛኛው ልክ አይደለም። ብዙ ክርስቲያኖች ዕለታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ልምድ ውስጥ መግባት ይከብዳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የማላነበው:- 

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጠቃሚ እንደሆነ የሚያስረዱ ምክንያቶችን መናገር ላያስፈልጋችሁ ይችላል። ጠቃሚ መሆኑን ግን ጠንቅቃችሁ ታውቃላችሁ። ትንሽ ማበረታቻም ሊያስፈልጋችሁ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ አስደሳች ከሚያደርጉት ነገሮች ዉስጥ አንዱ የንባብ መርሃ ግብር ስልታችንን ማጤን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ የሚረዱ ሁለት ጠቃሚ መንገዶች እነሆ።

ጾም ለጀማሪዎች

ምንአልባት አልፎ አልፎ አልያም ፈጽሞ ከማይጾሙት ብዙኃኑ የክርስቲያን ጎራ ልትሆኑ ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስላላነበብን ወይንም ከአንድ ሊታመን ከሚገባ ...

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

የመንግሥተ ሰማይ ጠረን

የምንኖረው በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ነው። ምንም እንኳን በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እየሆነ ያለውን ነገር በሙሉ ባናይም በሚታየው ዓለም ላይ ባላቸው ተጽዕኖ ግን ...

Michelle Zombos - avatar Michelle Zombos

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.