Monday, 01 March 2021

ትዳር በዘላለም እይታ

Posted On %PM, %14 %499 %2016 %13:%Jul Written by

ትዳራችሁ ምን ያህል ሚቆይ ይመስላችኋል? ሌላ ተጨማሪ አምስት አመት ምትቀጥሉ  ይመስላችኋል? አስርስ? ሃምሳ? ከዘላለም ጋር ሲነፃፀር ብዙም እንደማይባል ሁላችንም ምንስማማ ይመስለኛል። ዘላለም ትዳርንም ሆነ በዚህ ዓለም ላይ ያለን ማንኛውንም ነገር የምንደሰትበትን መንገድ ይቀይራል። ዘላለም የፍቅራችንን አቅጣጫ ይቀይራል። ባለቤቴንና ልጆቼን በዚህ ስላለ ህይወት ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ ባደርግ ስለመጪው ግን ባላዘጋጃቸው እየወደድኋቸው አይደለም። አንዳንድ ክርስቲያኖች ትዳር ላይ አብዝተው ከማተኮራቸው የተነሳ የክርስትና ዋና ዓላማ በደስተኛ ትዳር ውስጥ መኖር እንደሆነ ይመስላቸዋል። እግዚአብሔርንም የነገሮች ማግኛ መንገድ አድርገው ያስቡታል። ብዙ ክርስቲያኖች ከመስቀሉ ይልቅ ስለ ትዳራቸው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑት እሰማለሁ። እርግጥ ነው አግዚአብሔር ቤተሰቦቻችንን እንድንወድ ይፈልጋል ነገር ግን ጥንቃቄ ልናደርግ ያሻል።


ብዙ ክርስቲያኖች ከመስቀሉ ይልቅ ስለ ትዳራቸው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑት እሰማለሁ።


ኢየሱስ የትኛውን ጥቅስ ሚጠቅስ ይመስላችኋል?

ልክ ባልሆነ መረዳት አትረዱኝ። በማግባቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ። ከተጋባን ሃያ ዓመታት ሆነውናል። ባለቤቴን ሊሳን ከምንጊዜውም በላይ አብልጬ እወዳታለሁ። ይሁን እንጂ ለስኬታችን ቁልፉ ትዳራችንን በትክክለኛ ቦታው ማስቀመጣችን ነው። አግዚአብሔር ለትዳር ከብር እንድንሰጥ ቢያዘንም ከሚገባው በላይ ግን ዋጋ መስጠት እንደሌለብን ይነግረናል። በዚህ ምድር ላይ ባለችን አጭር ዕድሜ በተልዕኮ ላይ መሆናችን እርግጥ ነው። ለዚህ ነው ጳውሎስ እንዲህ ያለው፡-

በሚስት ታስረህ እንደ ሆንህ መፋታትን አትሻ፤ በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ። ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይሆንባቸዋል፥ እኔም እራራላችሁ ነበር። ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ።” (1 ቆሮንቶስ 7፤27-29)

ኤፌሶን 5ትን የፃፈልን ጳውሎስ 1 ቆሮንቶስ 7ንም ፅፎልናል። “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ” ብሎ የፃፈልን “ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ” ብሎ ደግሞ ይፅፋል። ጤነኛና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ሁለቱንም ልንታዘዝ መፈለግ አለብን። እዚህ ጋር የኢየሱስን ቃሎች መርሳት የለብንም፡- “ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።” ሉቃስ 14፡26

ስለትዳር በምናሰተምርበት ጊዜ ዝንባሌአችን እነዚህን የመሰሉትን ምንባቦች በአንድ ወይንም ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ቋጭተን ወደ ኤፌሶን 5 መሻገር ነው። ይሄ ግን ልክ ነው? ወይስ እግዚአብሔር ሁሉንም ጥቅሶች እኩል የአየር ሰአት አኩል አትኩሮት እንድንሰጣቸው ይፈልጋል? ኢየሱስ በአንድ የጋብቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ቢሰብክ የትኞቹን ጥቅሶች ሚጠቀም ይመስላችኋል?

በአንድ በኩል ኤፌሶን 5 ላይ ብዙ ጊዜ ወስደን ማስተማራችን ተቀባይነት አለው። ምክንያቱም ብዙ ቤተሰብ እየፈራረሰ ነው ያለው። ፍቺዎች በሚያስደነግጥ ፍጥነት እየተከሰቱ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ቀውስ አለ። ባሎች ሚስቶቻቸውን ቸል እያሏቸው ነው። ሚስቶችም ባሎቻቸውን እንዲሁ። በአንድ በኩል ስናየው እንደነዚህ ያሉትን ጥቅሶች ማስተማር አደገኛ ሊመስል ይችላል። ቤተሰብ ከእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ሊያዘናጋን እንደሚችል የሚያስጠነቅቁንን የመጽሐፍ ክፍሎች እንድንዘል የሰው ጥበብ ይነግረናል። ነገር ግን “የእግዚአብሔርን የቃሉን ምክር ሁሉ” መስበክ ቃሉን ማክበር፤ ማመን እንዲሁም ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስን ማስተማር  ነው።

በተቃራኒው አቅጣጫ አንያዝ

ፍቺ በቤተክርስቲያን ሳይቀር ተስፋፍቶ ስላለ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው በላይ ስለትዳር አጽንዖት በመስጠት ለማካካስ ማመዘናችን ትርጉም የሚሰጥ ሊሆን ይችላል። ይህን በማድረጋችን ግን ትዳሮችን ከማደስ ይልቅ ልንጎዳቸው እንችላለን። ባለትዳሮች የወንጌል ተልዕኮ-ተኮር ከመሆን ይልቅ ራስ-ተኮር ይሆናሉ። ላጤ በነበሩባቸው ወቅቶች ኢየሱስን በመስጠት ሲያገለግሉ የነበሩ ሲያገቡ ግን ትዳራቸውን በማሻሻልና በትዳራቸው በመደሰት ብቻ ጊዜአቸውን ያሳልፋሉ። አልያም ደግሞ ያለማቋረጥ በመጨቃጨቅ ጊዜአቸው በምክር አገልግሎትና በሃዘን ያልፋል። በዚህም ሆነ በዚያ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዓላማ ፍሬቢስ ይሆናሉ። ከተጋቡ በኋላ ኢየሱስን በበለጠ ታማኝነት እያገለገሉ ያሉ ጥንዶች ታውቃላችሁ? እንደዚህ መሆን ግን የለበትም። ለዚህ ነው ጳውሎስ በ1 ቆሮንቶስ 7 ላይ ይህን የጻፈው “ይህንም የምለው ለእናንተ የሚበጃችሁን ነገር በማሰብ እንጂ ላስጨንቃችሁ አይደለም ዓላማዬም ልባችሁ ሳይከፈል በጌታ ጸንታችሁ በአግባቡ እንድትኖሩ ነው።” (1 ቆሮንቶስ 7፤35) ዓላማው “ልባችሁ ሳይከፈል. . . በአግባቡ እንድትኖሩ” ነው። እነዚህን ቃላት አስቡ። አስተውሉ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር እንጂ ስለትዳር የተጻፈ መጽሐፍ አይደለም። ባለችን አጭር ሕይወት ልናደርገው የምንችለው የተሻለ ነገር ለእርሱና ለተልዕኮው መሰጠት ነው። ይህ ነው ዓላማው። ጋብቻም ይህንን ዓላማ እንድንጨብጥ ሊያግዘን ይችላል። ለዚህ ነው ጳውሎስ ሰዎች በምኞት ከሚቃጠሉ እንዲያገቡ ሚመክረው። ጤነኛ ትዳር ውጤታማነታችንን የሚያጠፉ ፈተናዎችን እንድንከላከል ይረዳናል። ግን አስታውሱ ይህ ግብ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ መሆን አለበት። ትዳር ለኢየሱስ ያለንን መሰጠት ማሻሻያ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን በተቃራኒው አቅጣጫ ይዘን የትዳራችን ማሻሻያ መንገድ አናድርገው።


አስተውሉ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር እንጂ ስለትዳር የተጻፈ መጽሐፍ አይደለም።


ባለቤቴ ሊሳ ትዳራችንን ረጅም ምዕራፍ ያሉትን “The Amazing Race” (የሚደንቅ ውድድር እንደማለት ነው) የተባለውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ይመስላል ስትል ገለፀችው። ይህን ፕሮግራም አይታችሁት አታውቁ እንደሁ በዚህ ፕሮግራም ላይ አንድ ሰው አንድ አጋር ይመርጥና በዓለም ዙሪያ እየሄዱ ከሌላ ጥንዶች ጋር ይወዳደራል። የባለቤቴ ሃሳብ እኔና እርሷም ሕይወታችንን ልክ በፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት ተወዳዳሪዎች እንደምናየው ነው። ልክ እንደ ጳውሎስ አኛም በምድር ላይ ያለውን ሕይወታችንን እንደ እሽቅድምድም ነው ምናየው። (1 ቆሮንቶስ 9፤24-27) የምንጣላበትም ሆነ በትንሹ ነገር ተደላድለን የምንኖርበት ጊዜ የለንም። ሩጫችን ሽልማትን ለመቀበል ነው። የሚቻለንን ያህል ቁጥርም ሆነ ጥልቀት ያላቸው ደቀመዝሙሮች ለማፍራት እየሰራን ነው (ማቴዎስ 28፡18-20)። መጨረሻውን መስመር ካለፍን በኋላ ስኬታችንን ለማክበር በቂ ጊዜ ይኖረናል። ለአሁን ግን ሩጫችንን እንቀጥላለን።

ወደ ውጊያው ሜዳ አብራችሁ ግቡ

መጽሐፍ ቅዱስ ከእውነተኛ ጠላት ጋር በ እውነተኛ ጦርነት ውስጥ እንዳለን ያስተምራል (2 ቆሮንቶስ 10፡3-4፤ ኤፌሶን 6፡10-20) ። “በሌላ ሥራ ራሳችንን እንዳናጠላልፍ” (2 ጢሞቴዎስ 2፡3-4) እግዚአብሔር ተልዕኮ ሰጥቶናል። እስቲ በምናባችሁ ይህን አስቡ በሚያምር ቤት ውስጥ ከደስተኛ ቤተሰባችሁ ጋር አብራችሁ አላችሁ። እናም ካላችሁበት ቤት ትንሽ ራቅ ብሎ የለየለት ጦርነት ተከፍቷል። እናንተ ጓዳችሁን ስታስተካክሉ አዲስ የገዛችሁትን ቴሌቪዥን ለመስቀል ስትጣጣሩ ጓደኞቻችሁ እና ጎረቤቶቻችሁ ሕይወታቸውን ለማትረፍ እየተዋጉ ነው። ሠራተኛ ቀጥራችሁ ደግሞ ከውጪ ድምጽ የማያስገባ መስኮት ታስገጥማላችሁ።

በቂ ያልሆነ ምስል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ለብዙ ክርስቲያን ጥንዶች ሰለሚቀርብ ሕይወት ጥሩ ንጽጽር ነው። ብዙዎች በዚህ ያላቸውን ሕይወት ለመደሰት ሲሉ የኢየሱስን ተልዕኮ ችላ እያሉት ነው። ነገር ግን አትሸወዱ። እውነተኛው ሕይወት ያለው በጦርነቱ ውስጥ ነው። ብዙ ወንድምና እህቶቻችን በአሁኑ ጊዜ ስለ እምነታቸው መከራ እየደረሰባቸው ነው። ወደዚህ ውጊያ እኛም እንድንገባ በእነርሱ ምሳሌ ልንበረታታ ለእነርሱም ልንጸልይላቸው ይገባል።

በውጊያው ውስጥ አብረን መሆናችን ምናልባትም እርስ በእርሳችን ጥል እንዳይኖር የሚጠብቀን ነው።ትዳራችሁ ላይ ለመስራት ውጊያውን ቸል ከማለት ይልቅ ወደ ውጊያው አብሮ መግባት ምናልባት ለትዳራችሁ የተሻለ ይሆናል።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %831 %2016 %21:%Dec
Francis Chan

Francis Chan Francis is a pastor in San Francisco and is actively planting churches in the Bay Area.

francischan.org

ወደ እግዚአብሔር መቅረብ (ክፍል 1)

ወደ አንድ ሰው ቤት ወይንም የሥራ ቦታ ሄዳችሁ ያንን ሰው ቀርቦ መገኛኘት አስጨንቋችሁ ያውቃል? የምትገናኙበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ ልትነግሩት ያሰባችሁት ሁሉ ስት...

Michelle Zombos - avatar Michelle Zombos

ጨርሰው ያንብቡ

አስታውሱ ፤ ይወድዳችኋል

“እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን ...

Joseph Tenney - avatar Joseph Tenney

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.