Thursday, 25 April 2024

ደስታችሁ ያረፈው በክርስቶስ ጽድቅ ላይ ነው

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንደሆነ መቶ በመቶ ብታምኑ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? እንደተቀበላችሁ ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ማንነት እና ሥራ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እንደተቀበላችሁ ብታምኑ? ታላቅ የምትሉት ስኬታችሁ የተለየ ወደ እርሱ እንደማያቀርባችሁ ወይንም የመጨረሻው ውድቀታችሁ የቱንም ከእናንተ እንደማይወስድ ብታምኑስ? ይህን ብታምኑ ፤ በእርግጥ ብታምኑ በሕይወታችሁ ውስጥ ለደስታ ያላችሁን ፍለጋ ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል።

እግዚአብሔር ከእራሱ ጋር ወደ ጤነኛ ግንኙነት እንደተቀበለን የሚናገር የክርስትና አስተምህሮ መጽደቅ ይባላል። ይህ መጽደቅ የምንለው ነገር በእራሳችን እየፈለግነው ካለው ደስታ ከሚባለው ነገር ጋር ታላቅ ቁርኝት አለው። 

ጽድቅ በእምነት ብቻ

መጽደቅ ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት መታረቅ እንደምንችል ይናገራል። ፍርድ ቤት ውስጥ ነን ብላችሁ አስቡ። ተከሳሽ (እናንተ) አላችሁ ከዛም ደግሞ ዳኛው (እግዚአብሔር) አለ። እናም ሁላችንም ላጠፋነው ጥፋት ተከሰናል፤ መተላለፋችንም በእራሱ በዳኛው ላይ የፈጸምነው ታላቅ ክህደት ነው።

መጽደቅ ማለት ዳኛው ጥፋተኛ ብሎ ከመደንገግ ይልቅ ነጻ ሲላችሁ ነው። ከማንኛውም ስህተት ጽዱ መደረግ ነው። በጣም የሚገርመው የክርስቲያን ወንጌል ይህ ነው ምንም ኃጢያተኛ ብንሆን እንኳን በእምነት እግዚአብሔር ኃጢያተኛውን አጸደቀ (ሮሜ 4፡5) ።

ነገር ግን በምን መስፈርት ነው እግዚአብሔር ጻድቅ ያደረገን?  500 ለሚሆኑ ዓመታት ይህ ነገር አጨቃጫቂ ነበር። አንዳንዶች በእግዚአብሔር ፊት ያለን ሙሉ ተቀባይነት ከእኛ ውጪ በሆነው የክርስቶስ ሥራ ላይ ብቻ ሳይሆን የሚወሰነው በእኛ ውስጥ በሚሰራ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው ይላሉ። እግዚአብሔር ጽድቅን ጨምሮብን (Infuses) ጻድቆች ብሎ ደንግጎናል ሲሉ ሌሎች ደግሞ ከአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ጋር በሚጣጣም መልኩ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ የተቀበለን የሌላን ጽድቅ ማለትም የኢየሱስ ክርስቶስን ጽድቅ በመቁጠር ነው (። ዮሐንስ 2፡።)። ጻድቆች ተብለን የተደነገግነው እና በእግዚአብሔር ዘንድ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነትን ያገኘነው በእኛ ውስጥ ባለ ጽድቅ ሳይሆን ከእራሳችን ውጪ በመመልከት በእኛ ሥራ ያልሆነ ነገር ግን ጽድቃችን ከሆነው ክርስቶስ ጋር በእምነት የምንጣበቅበት ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 1:30፣ ሮሜ 5፡9፤10፡4፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡2)።  

መጽደቅ በእምነት ብቻ የሚለው ሃሳብ የወንጌል መሠረት ነው። ማርቲን ሉተር ቤተክርስቲያን የምትወድቅበት ወይንም ጸንታ የምትቆምበት አስተምህሮ ነው ይለዋል። መጽደቅ በ እምነት ብቻ ነው የሚለውን አስተምህሮ ደግሞ አጥብቀው የሚይዙ ሰዎች ጥልቅ የሆነ ታላቅ የደስታ አቅም ስላገኙ ዋነኞቹ ነፃ ፣ በእውነት የሚወድዱ እና በሥራ የሚገለጡ ሰዎች ናቸው።

የእርሱ ጽድቅ መደሰቻችን

መጽደቅ በእምነት ብቻ መሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ላለን ደስታ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በፊሊጵስዩስ 3፡1 እና ቀጥሎ ባለው ቁጥር ላይ ተጽፎ እናገኛለን።

በምዕራፍ ሁለት ላይ ጳውሎስ በአገልግሎቱ እንዲጸና የሚያደርገው ደስታ እንደሆነ አጥብቆ ይናገራል ይህም ደስታ ደግሞ የፊሊጲስዩስ ሰዎችን አንድነትን እና ትህትናን እንዲፈልጉ እንደሚያበረታታቸው ተስፋ ያደርጋል። ቤተክርስቲያንን ወደ ጠላትዋ ማዘንበልዋን ለማሳሰብ ደስታ ወደሚለው ሃሳቡ መልሶ ይወስዳቸዋል።

በጌታ ደስ ይበላችሁ” (ፊሊጽስዩስ 3፡1) ሲል እስካሁን ሲጽፍ ከመጣበት ሃሳብ ጋር ብቻ የሚዛመድ ሳይሆን ቀጥሎም ካለውም ላይ ጎልቶ የሚታይ ነጥብ ነው። ለመሸጋገሪያነት ብሎ የተቀመጠ አይደለም። ነገር ግን እውነተኛ ክርስቲያኖችን ከአስመሳይ ኃይማኖተኞች የሚለይ መስመር ነው። ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን አንድ ስለሚያደርጋት ነገር አጽንዖት እየሰጠ በመከራ መሃል ጸንተው ለመቆም የሚችሉበት ኃይል በኢየሱስ ላይ ያላቸው ደስታ እንደሆነ ይነግራቸዋል። በጌታ ደስ ይበላችሁ።

ጳውሎስ በዚህ ስፍራ በቤተክርስቲያን እና በተቃዋሚዎቿ መኃከል ያለው ልዩነት የሚመኩበት ነገር ምንጭ እንደሆነ ይናገራል።የተቃዋሚዎቿ በእግዚአብሔር ፊት የመቆማቸው ድፍረት የራሳቸው ሥራ ሲሆን የእግዚአብሔር እውነተኛ ሕዝቦች ግን “በሥጋ አይታመኑም” (ፊሊጲስዩስ 3፡3). ጥቂት በሥጋ ላይ አለመመካት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በሥጋ አለመመካት። በሌላ አገላለጽ ጽድቅ በእምነት ብቻ እንደሆነ ነው የሚያምኑት። በእራሳቸው ላይ ሊመኩበት የሚችሉት ነገር እንኳን ቢኖር “በክርስቶስ ላይ ይመኩ ዘንድ” ፊሊጵስዩስ 3፡3) ወደጎን ጥለውታል። እግዚአብሔር እነ እርሱን የተቀበለበት መሠረት ክርስቶስ ብቻ ነው።

እግዚአብሔር እኛን የተቀበለበት መሠረቱ ክርስቶስ ካልሆነ መቼም ቢሆን ደስተኞች ልንሆን አንችልም።

ከዘር ግንዳችሁ ወይን ስኬታችሁ ውጪ የሆነ

ጳውሎስ ይህን እውነታ በትህትና እንዲሁም በድፍረት ተቀብሎት ነበር። ጳውሎስ በዘር አመጣጡ ላይ ወይንም በእራሱ ስኬት ላይ ለመደገፍ ቢያስብ ሁሉንም ይበልጥ ነበር(ፊሊጵስዩስ 3፡4-6)። ነገር ግን በእራሱ ስኬት ላይ ከመደገፍ ይልቅ ጳውሎስ ከልክ በላይ የሆነን ደስታ ይፈልግ ዘንድ በወንጌል ሕይወትን እና ነፃነትን አግኝቷል። ሁሉንም ስኬቶቹን እንደ ጉድፍ ቆጠራቸው።

"አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ" (ፊሊጵስዩስ 3፡8-9)

ስለዚህ በእግዚአብሔር ያለን ደስታ በማይነጣጠል መልኩ ጽድቅን በእምነት ብቻ ከማግኘት ጋር ይቆራኛል። “ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት” የሚለውን ንግግር ከክርስቶስ ጋር በእምነት ተጣብቆ ከእኛ ጽድቅ ጋር በማይወዳደር መልኩ የሚልቀውን የእርሱን ጽድቅ በማግኘትና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን በማግኘት ካልሆነ በቀር ማጣጣም አንችልም። ደስተኛ ለሆነ የክርስትና ሕይወት ጽድቅ በእምነት ብቻ እንደሚገኝ አጥብቆ መያዝ አስፈላጊ ነው።

እግዚአብሔር እኛን የሚቀበልበት መንገድ በእኛ ሥራ ላይ ተመሥርቶ ነው ባልንበት ልክ ደስታችን እናጣለን።

“አሁን በእርግጥ የግር ብረቴ ከላዬ ወደቀ”

ሰማዕት የሆነው እና “የመናኙ ጉዞ” (The Pilgrim’s Progress) የሚለውን መጽሐፍ የጻፈው መጥምቃዊው ፓስተር ጆን በኒያን (1628-1688) በአንድ ሜዳ ላይ እየተራመደ ሳለ መንፈስ ቅዱስ እምነት በጽድቅ ብቻ እንደሚገኝ እንዳበራለት እና በእዚህም ደስታን የማግኛ ምኝጭ እንዴት እንደተነደለለት ያስታውሳል። ከብዙ የልብ ጭንቀት እና መከራ በኋላ በመጨረሻ እንዴት እንዳየ ሲናገር "ለካስ ጽድቄን መልካም ያደረገው የልቤ መልካም ገጽታ መሆን አልነበረም። ሲቀጥል የልቤ መጥፎ ገጽታው ደግሞ ጽድቄን አስቀያሚ የሚያደርገው ነገር አልነበረም ምክንያቱም ጽድቄ “ትላንትም ዛሬም እስከለዘላለም ያው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ” (ዕብራዊያን ።3፡8) እራሱ ስለሆነ። አሁን በእርግጥ የግር ብረቴ ከላዬ ወደቀ . . . ስለ እግዚአብሔር ጸጋ እና ፍቅር እየተደሰትኩም ወደቤቴ ሄድኩ"

በሞቱትም ሆነ አሁን በሕይወት ካሉት ውስጥ ይህ የብዙዎች ምስክርነት ነው። ጆን ፓይፐር እንደጻፈው

"ስለደስታችን ባለን ውጊያ በጣም ጠቃሚው፣ የወንጌል ጦር ዕቃችን በማመናችን ምክንያት ጻድቆች ተብለን መቆጠራችን ነው። ይህ የወንጌል የጦር ዕቃ  ግን ስኬታማ የሚሆነው የጽድቃችንን መሠረት ከእኛ ሥራ ነጻ አድርገን ስናየው ብቻ ነው። እግዚአብሔር የተቀበለን በእኛ ሳይሆን በክርስቶስ ጽድቅ ላይ በመመሥረት ብቻ ነው። በጨለመው አለመብቃታችን ውስጥ የክርስቶስ ጽድቅ የሆነ ፍጹም ጽድቅ እንዳለን እርግጠኞች መሆን አቤት እንዴት ያለ ለውጥን ያመጣል! (When I Don’t Desire God, 85)" 


ስለደስታችን ባለን ውጊያ በጣም ጠቃሚው፣ የወንጌል ጦር ዕቃችን በማመናችን ምክንያት ጻድቆች ተብለን መቆጠራችን ነው።


በንያን እና ፓይፐር እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተለማመዱት በ ክርስቶስ ጽድቅ በማመን ብቻ በእግዚአብሔር ተቀባይነትን ማግኘት ሸክም አልባ ለሆነው የደስታ ፍለጋችን ወሳኝነት አለው።  

በእርሱ የመቀበላችን የመሆን ደስታ

መጽደቅ በእምነት ብቻ እንደሆነ በማመናችሁ ምክንያት በጨለመ ልባችሁ ላይ የሚበራው ብርሃን የሚያመጣውን ደስታ ቀምሳችኋል? ለብዙ ክርስቲያኖች ደስታ አልባ መሆን የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ከሚረሱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ስለመጽደቃችን ደካማዎች ከሆንን ደስታችንም ደካማ እንደሚሆን ነው።

እውነተኛ ክርስቲያናዊ ደስታ መጽደቅ በእምነት መሆኑን ከሚያቃልል ማንኛውም አስተምህሮ ጋር ይጋጫል። ክርስቲያኖች ገና የሚጠብቁት ውሳኔ ወይንም የወደፊት ድንጋጌ እንደሌለ እና በእግዚአብሔር ዘንድ አሁን ሙሉ ተቀባይነት እንዳገኙ ካላመኑ በእግዚአብሔር ውስጥ የሚፈልጉት ደስታ ይገታል። 

በማመን ስለሚመጣ ጽድቃቸው ጠንካራ የሆኑ ሰዎች ደስታን ለመፈለግ በሚኖራቸው ኑሮ ነፃ የሆኑ ሰዎች ይሆናሉ። 

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %910 %2016 %23:%Dec
David Mathis

David Mathis is executive editor for desiringGod.org, pastor at Cities Church in Minneapolis/Saint Paul, and adjunct professor for Bethlehem College & Seminary. He is author of Habits of Grace: Enjoying Jesus through the Spiritual Disciplines.

https://twitter.com/davidcmathis

ጾም ለጀማሪዎች

ምንአልባት አልፎ አልፎ አልያም ፈጽሞ ከማይጾሙት ብዙኃኑ የክርስቲያን ጎራ ልትሆኑ ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስላላነበብን ወይንም ከአንድ ሊታመን ከሚገባ ...

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

የተስፋ ነፀብራቆች ሁኑ

“ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው” (1 ተሰሎንቄ 5፡11)። “ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ ...

Jon Bloom - avatar Jon Bloom

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.