ተከተሉኝ (Follow Me) በሚለው መጽሐፉ ፕላት የእግዚአብሔርን ፍቃድ የመፈለጋችን ስር መሠረቱ ምን እንደሆነ ይናገራል። እጣ መጣል ቢሆን ወይንም እንደ ኤሊያስ ዝግተኛዋን ትንሽ ድምጽ መስማት አሊያም በሩ በፊታችን አውቆ እንዲከፈቱ መጠበቅ አይነት ወዳሉ ብዙ መንገዶችን ተስበናል። ነገር ግን ፕላት ይህን ያህል ከባድ ነው? ይለናል።
እግዚአብሔር ልጁን የላከው እርሱ በሰማይ ቁጭ ብሎ “አይ እንደሱ አይደለም. . . አሁን ልክ ነህ . . . አሁን ልክ ነው” ሊለን ባይሆንስ? የእግዚአብሔርን ፍቃድ በዚህ መልኩ መፈለግ ሙሉ በሙሉ የክርስቶስ ደቀመዝሙር የሚለውን ሀሳብ የሳተ ቢሆንስ? (ገጽ 127-128)
ክርስቲያናዊ ደቀ መዝሙርነት አላመው ፍቃዳችንን መቀየር ነው። አማኞች በክርስቶስ አዲስ ሲሆኑ የሆነው ይህ ነው። “እንደ ኢየሱስ ተከታዮች ሕይወታችን በሕይወቱ ውስጥ የተካተተ ነው። መንገዳችንም ለፍቃዱ ሙሉ በሙሉ የተገዛ ነው” (ገጽ 128)። በክርስቶስ መሆን ማለት “ከእንግዲህ ወዲህ ስለ እኛ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳችን አንኖርም” (2 ቆሮንቶስ 5፡15) ማለት ነው።
እግዚአብሔር ልጁን የላከው እርሱ በሰማይ ቁጭ ብሎ “አይ እንደሱ አይደለም. . . አሁን ልክ ነህ . . . አሁን ልክ ነው” ሊለን ባይሆንስ? የእግዚአብሔርን ፍቃድ በዚህ መልኩ መፈለግ ሙሉ በሙሉ የክርስቶስ ደቀመዝሙር የሚለውን ሀሳብ የሳተ ቢሆንስ?
እንደዚህ ከሆነ ታዲያ እጆቻችንን አጣምረን በተቆጣ ፊት ወደ እግዚአብሔር መመልከት ትንሽ እንግዳ ነገር አይሆንም? እኛ የእራሳችን አይደለንም ነገር ግን “ማንኛውም ነገር ይሁን ጌታ ሆይ ከእነዚህ ምርጫዎች ውጪ ማንኛውም ነገር ይሁን" እንላለንን? ከክርስቶስ ጋር ስላለን ሕብረት በማስተዋል እየኖርን ከሆነ “ወደምትመራኝ ሁሉ እሄዳለሁ ከእኔ የምትጠይቀውን ሁሉ እሰጣለሁ” ከማለት የተለየ ነገር ለእግዚአብሔር ልንናገር እንችላለን? ፕላት ሲጽፍ “በክርስቶስ ውስጥ የእራሳችንን ሕይወት አጥተነዋል፣ በደስታ ፍቃዳችንን ለእርሱ እናሰገዛለን። ይህ በምንጠመቅበት ጊዜ የታወጀ እና የተደነገገ ደቀ መዝሙር የመሆን ትርጉም ነው” (ገጽ 130)።
ስለዚህ ለሕይወታችን የእግዚአብሔርን ፍቃድ ስንፈልግ የመጀመሪያው ነገር ፍቃዳችን በክርስቶስ ውስጥ እንደ አዲስ እንደተመሠረተ ማወቅ ነው። በዚህ ሴሚስተር ምን ማድረግ እንዳለብን ወይንም ከቀረቡልን የሥራ ምርጫዎች ውስጥ አንዱን መምረጥ ወይንም ሀገር ስለመቀየር ቢሆን በእግዚአብሔር ሀሳብ ውስጥ ምንም አቋራጭ መንገድ የለም። ፕላት ይሄ የእግዚአብሔር ሀሳብ እንዳልሆነ ያስታውሰናል።
ስለዚህ ለሕይወታችን የእግዚአብሔርን ፍቃድ ስንፈልግ የመጀመሪያው ነገር ፍቃዳችን በክርስቶስ ውስጥ እንደ አዲስ እንደተመሠረተ ማወቅ ነው።
እግዚአብሔር የሚያሳስበው እናንተን ከነጥብ ሀ ወደ ለ ፈጣን ፣ ቀላል ፣ የማያስቸግር በጣም ግልጽ በሆነው መንገድ ማድረስ አይደለም። ነገር ግን የሚያሳስበው እኔ እና እናንተ በእርሱ ሙሉ በሙሉ በታመንን ጊዜ እርሱን በጥልቅ ማወቃችን ነው። (ገጽ 131)
አያችሁ የተጠራነው ከኢየሱስ ጋር ሕብረት እንድናደርግ ነው። የተጠራነው ወደ እራሱ አንጂ ወደ መመሪያዎች አይደለም። ፕላት ሲጽፍ “ስለዚህ የኢየሱስ ደቀ መዝሙርነት አላማው ‘ለሕይወቴ የእግዚአብሔር አላማ ምንድን ነው?’ የሚለውን መመለስ ሳይሆን ቀን በቀን በእያንዳንዷ አፍታ በእግዚአብሔር ፍቃድ ውስጥ መራመድ ነው” (ገጽ 133)። ዋናው ነገር ከኢየሱስ ጋር መራመድ ነው። ከእርሱ ጋር የምንራመድ ከሆነ ሕይወታችን በእርሱ ሕይወት የተዋጠ ከሆነ በትክክለኛው መንገድ እንጓዛለን።
እግዚአብሔር የሚያሳስበው እናንተን ከነጥብ ሀ ወደ ለ ፈጣን ፣ ቀላል ፣ የማያስቸግር በጣም ግልጽ በሆነው መንገድ ማድረስ አይደለም። ነገር ግን የሚያሳስበው እኔ እና እናንተ በእርሱ ሙሉ በሙሉ በታመንን ጊዜ እርሱን በጥልቅ ማወቃችን ነው።
Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe