Monday, 15 July 2024

መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ የሚረዱ ሁለት ጠቃሚ መንገዶች

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጠቃሚ እንደሆነ የሚያስረዱ ምክንያቶችን መናገር ላያስፈልጋችሁ ይችላል። ጠቃሚ መሆኑን ግን ጠንቅቃችሁ ታውቃላችሁ። ትንሽ ማበረታቻም ሊያስፈልጋችሁ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ አስደሳች ከሚያደርጉት ነገሮች ዉስጥ አንዱ የንባብ መርሃ ግብር ስልታችንን ማጤን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ የሚረዱ ሁለት ጠቃሚ መንገዶች እነሆ።

ጠቃሚ መንገድ 1፡ በድምጽ የተቀዳ መጽሐፍ ቅዱስን ማዳመጥ

በድምጽ የተቀዳ መጽሐፍ ቅዱስን በምናዳምጥበት ወቅት ምን ያህል የመጽሐፍ ክፍሎችን “እንዳነበባችሁ” ጊዜውም ምንያህል እንደሄደ ስታስቡ ትገረማለቸሁ። ብዙውን ጊዜ መኪና ስነዳ ወይም ሳፀዳ አሊያም በምሮጥበት ጊዜ በድምጽ የተቀረፁ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን አዳምጣለሁ። ይሁን እንጂ ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ወይንም በዋናው ቅጂ በማነብበት ጊዜ ማዳመጥ የበለጠ ትርፋማ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እያነበባችሁት ካለው ትርጉም ውጪ ሌላ ትርጉም ማዳመጥ በጉጉት እንድታነቡ ይረዳችኋል እግረ መንገዳችሁንም  የተለያዩ ትርጉሞችንም ትመለከታላችሁ። ንባባችሁ ፈጣን ስለሚሆን የተደበቁ ጥቃቅን ሃሳቦችን ላታስተውሉ ትችላላችሁ። ይሁን እንጂ ጠቃሚ የሆነ አጠቃላይ ዕይታ ይሰጣችኋል። በድምጽ የተቀዱ መጽሐፍ ቅዱሶችን ለአብዛኛው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ላሉ የሥነ-ጽሁፍ ዘዬዎች መጠቀም የሚቻል ቢሆንም፣ ለታሪክ ጽሁፎች መጠቀም ከምሳሌ መጽሐፍም ሆነ ከመልዕክት መጽሐፎች የተሻለ ውጤት አለው። ለዚህም ማስረጃ ደግሞ በድራማዊ በልኩ የተሰሩ ትረካ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦችን ስናደምጥ ያለውን ውጤት ማስተዋል በቂ ነው። ጳውሎስ ይጽፍላቸው የነበሩት ሰዎች ልክ እንደኛ የጽሁፉ ቅጂ እንዳልነበራቸው ነገር ግን ጽሁፉ በሕብረት ሳሉ ይነበብላችው እንደነበረ ማስታወስ አስፈላጊ ነው።

እናንተም በድምጽ የተቀዳ መጽሐፍ ቅዱስን ማዳመጥ መጀመር አለባችሁ። 

ጠቃሚ መንገድ 2፡ አንድ ሙሉ መጽሐፍን በአንድ ቁጭታ ማነበብ

ከአራት የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በአንድ ጊዜ አንድን ምዕራፍ ለማንበብ የንባብ መርሃ ግብራችንን ማስኬድ ጠቃሚነት ያለው ነገር ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን የምናነብበት ብቸኛው መንገድ እንደሱ ብቻ ከሆነ ሥነ ጽሁፋዊ ገፅታውን ብሎም የሙሉ መጽሐፉን ሥነ መለኮታዊ መልዕክት እናጣዋለን። የማቴዎስ ወንጌልን በአንድ ቁጭታ አንብባችሁት ታውቃላችሁ? የሮሜ መልዕክትንስ? መጽሐፈ ኢዮብን ወይ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍንስ? እንደሱ አድርጋችሁ ማታውቁ ከሆነ በብዙ እያጣችሁ ነው። የተጻፉት በዛ መንገድ እንዲነበቡ ነው። እንደ ነህምያ ያሉ መጽሐፍት ግፋ ቢል አንድ ሰዓት ነው ሚወስዱት። የኤፌሶን መልዕክት ደግሞ 20 ደቂቃ ይወስዳል። ከዚህ በታች እያንዳንዱ መጽሐፍ ሊወስድ የሚችለው ሰዓት ተቀምጧል።

ይህንን የማደርግበት ጊዜ የለኝም የሚል ምክንያት ልናነሳ እንችላለን ነገር ግን ጊዜ ወስዳችሁ የምታከናውኗቸው ሌላ እንቅስቃሴዎች የሏችሁም? ሌላ መጽሐፍትን በቀን ለተወሰነ ጊዜ አታነቡም? አንድ እና ሁለት ሰዓት የቴሌቪዥን ፕሮግራም ወይንም ፊልም ወይንም ኳስ ጨዋታ ስታዩ አታሳልፉም? ታዲያስ ሕይወትን ለሚሰጥ ለእግዚአብሔር ቃል ያልተከፋፈለ ረጅምን ጊዜ ለምን አንሰጥም?

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %14 %489 %2017 %13:%Jan
Andy Naselli

Andy Naselli @AndyNaselli is assistant professor of New Testament and biblical theology at Bethlehem College & Seminary and an elder of Bethlehem Baptist Church. He is the author of the new book Conscience: What It Is, How to Train It, and Loving Those Who Differ. He also writes regularly at andynaselli.com. Andy and his wife, Jenni, have three daughters.

andynaselli.com/

መልካምነቱን ማስታወስ — መንፈሳዊ የመርሳት ችግርን ለመፋለም 6…

አልዛይመር በሚባል በሽታ ለብዙ ዓመት ስትሰቃይ ከቆየች በኋላ አያቴ በ2002 ዓ.ም.  ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። የቀሩ ትውስታዎች ቢኖሯትም አብዛኛዎቹ የማስ...

Ben Reaoch - avatar Ben Reaoch

ጨርሰው ያንብቡ

ከሮሜ 8:35 ውስጥ ልንማራቸው የምንችለው ሦስት ነገሮች

ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? (ሮሜ 8፡35) ...

Jonathan Parnell - avatar Jonathan Parnell

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.