Monday, 15 July 2024

ከሮሜ 8:35 ውስጥ ልንማራቸው የምንችለው ሦስት ነገሮች

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? (ሮሜ 8፡35)

በቁጥር 35 ላይ ሦስት ነገሮችን አስተውሉ።

1. ክርስቶስ አሁን እየወደደን ነው

ሚስት ስለሞተ ባሏ ከእርሱ ፍቅር ማንም አይለየኝም ልትል ትችላለች ። የፍቅሩ ትውስታ በሕይወቷ ሁሉ ጣፋጭ እና ኃይለኛ እንደሆነ ለመግለጽ ሊሆን ይችላል ። ጳውሎስ ግን እዚህ ጋር እያለ ያለው ይህን አይደለም ። በሮሜ 8፡34 ላይ በግልጽ ሲናገር “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል ። ጳውሎስ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ማለት የሚችለው ክርስቶስ በሕይወት ስላለ እና አሁንም ስለሚወድደን ነው ። በእግዚአብሔር ቀኝ ስላለ ስለእኛ እየገዛ ነው ። ደግሞም እየማለደልን ነው ። ማለትም የመዋጀቱ ያለቀ ሥራ እንደሚያድነን እና ወደ ዘላለም ደስታ እንደሚያመጣን እርግጥ እያደረገ ነው ። ፍቅሩ ትውስታ አይደለም ። ወደ ዘላለማዊ ደስታ እንዲያመጣን ሁሉን በሚችለው በሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚደረግ ድርጊት ነው።

2. የክርስቶስ ፍቅር ከመለየት ሊጠብቀን ስለሚቻለው ይህ ፍቅር ለአለም ሁሉ የሆነ ፍቅር አይደለም ነገር ግን በሮሜ 8:28 መሠረት እግዚአብሔርን ለሚወድዱት እንደ ሀሳቡም ለተጠሩት ለህዝቦቹ የተለየ ፍቅር ነው ።

ይሄ በኤፌሶን 5፡25 ላይ ያለው ፍቅር ነው:- “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ” ይሄ ክርስቶስ ሙሽራው ለሆነችው ለቤተክርስትያን ያለው ፍቅር ነው ። ክርስቶስ ለሁሉም ፍቅር አለው ደግሞም የሚያድን እና የሚጠብቅ ፍቅር ደግሞ ለሙሽራው አለው ። በክርስቶስ ካመናችሁ የዚህ ሙሽራ አካል እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ ። በክርስቶስ የሚያምን ማንኛውም ሰው ሁሉ ያለ ምንም መለያያት እኔ የሙሽራው ፣ የቤተክርስትያኑ እናም ቁጥር 35 ምንም ቢሆን ለዘላለም የተጠበቁት የተጠሩት እና የተመረጡት የሚላቸው ውስጥ አንድ አካል ነኝ ማለት ይችላል ።

3. ይሄ ሁሉን ቻይ እና የሚጠብቅ ፍቅር በሕይወት የሚደርሱ አደጋዎች እንዳይደርሱብን አያደርግም ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ወዳለ ዘላለማዊ ደስታ ሊያደርሰን ይችላል ። 

ሞት ሊደርስብን ይችላል ግን አይለየንም። ስለዚህ ጳውሎስ በ ቁጥር 35 ላይ “ሰይፍ” ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን አይችልም ሲል ብንሞት እንኳን ከክርስቶስ ፍቅር ልንለይ አንችልም ማለቱ ነው ። 

ስለዚህ በቁጥር 35 ላይ ያለው ሀሳብ ሲጠቃለል:- ክርስቶስ ኢየሱስ ህዝቡን በሚያስደንቅ ሁሉን ቻይ እና በሁሉም ጊዜ በሚገለጥ ነገር ግን ከአደጋ ሁሉ ነፃ በማያደርግ ይሁን እንጂ በመገኘቱ ሆኖ በሚገጥሙን መከራዎች እና ሞት ውስጥ ለዘላለም ደስታ በሚጠብቅ ፍቅሩ እየወደደን ነው።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %881 %2016 %23:%Dec
Jonathan Parnell

Jonathan Parnell is the lead pastor of Cities Church in Minneapolis/St. Paul, where he lives with his wife, Melissa, and their five children. He is co-editor of Designed for Joy: How the Gospel Impacts Men and Women, Identity and Practice.

https://twitter.com/jonathanparnell

አንቀፅ 17፣ ነፃነት/ባርነት — ከአድዋ - ጎልጎታ

ይህ ታሪክ ከተፈፀመ እነሆ በዛሬዉ 122ኛ ዓመቱን ይዟል። ይህ ቀን ለአሁኗ ኢትዮጵያ ማንነቷን ያስጠበቀችበት፣ ከባርነት ራሷን ነፃ ያደረገችበት ቀን ነው። ከመ...

Misgana Kibret - avatar Misgana Kibret

ጨርሰው ያንብቡ

የምንሰራበት ዋነኛው ምክንያት

ማብሰል ስላልፈለጋችሁ ውጪ ወጥቶ መብላት ይሁን ወይንም የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያለማቋረጥ ማየት ቢሆን፣ ወይንም ሥራ ትቶ የማሕበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ማፍጠጥ፤ አ...

Phillip Holmes - avatar Phillip Holmes

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.