Monday, 15 July 2024

ኃጢያትን ለመግደል 13 ተግባራዊ መንገዶች

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by
ኃጢያትን ለመግደል 13 ተግባራዊ መንገዶች Genaye Eshetu

ሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች በምድር ሳሉ በሥጋቸው ውስጥ ቀሪ ኃጢያት እንዳለባቸው ማወቅ እረፍት የሚሰጥ ደግሞም ልብ የሚሰብር ጉዳይ ነው።ታላቁ ሐዋርያ ሲጽፍ “አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ።” (ፊልጵስዩስ 3:12) በሌላ ቦታ ሲናገር “ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ” (ሮሜ 7፡23) ይላል። ኢየሱስም በየዕለቱ ስንጸልይ “በደላችንን ይቅር በለን” (ማቴዎስ 6፡12) እንድንል ያስተምረናል።

ነገር ግን ከኃጢያት ጋር ተደላድለን እንኑር ማለት አይደለም። ነገር ግን በየዕለቱ ልንዋጋው ያስፈልገናል። በሕይወታችን ውስጥ የቀረውን ኃጢያት በቋሚነት እንድናስወግደው ታዝዘናል። “እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ. . . . እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ።” (ሮሜ 8፡13 ፣ቆላስይስ 3፡5) ይሄ አማራጭ ያለው ጉዳይ አይደለም። ይህ የሞት ሽረት ፍልሚያ ነው። ኃጢያትን እንገለዋለን ወይ ኃጢያት ይገለናል። እዚህ ባለ ሕይወታችን ፍፁማን እንሆናለን ማለት ባይሆንም ነገር ግን ዕለት ከዕለት የሚያጠቁንን ኃጢያቶች ግን እንዋጋቸዋለን። ከኃጢያት ጋር ተስማምተን አንኖርም። ተዋግተን እንገድለዋለን።

ኃጢያትን ታዲያ እንዴት ነው የምንገድለው? ለዚህ ውጊያ የሚሆኑ 13 ስልታዊ መንገዶች እንካችሁ፡-

1. አሮጌው ኃጢያተኛ ማንነታችሁ የሞተ እንደሆነ ይህን እውነት በልባችሁ አጥብቃችሁ ያዙ።

(ሮሜ 6፡6፣ ቆላስይስ3፡3፣ 2 ቆሮንቶስ 5፡14) "የእርሱ ሞት ሞታችን እንዲሆን በእምነት ከክርስቶስ ጋር ተባብረናል።" (ሮሜ 6፡5፣ 2 ቆሮንቶስ 5፡14) ይህ ማለት 

ሀ) የአሮጌው ሥጋችን የሞት መውጊያችን አሁን ተወግዷል  

ለ) አሮጌው ሰው በእኛ ላይ አለቃ የመሆን ሥልጣን የለውም ሐ) ሙሉ በሙሉ እንደሚጠፋ እርግጥ ነው ።

2. አሮጌው ሰው እንደሞተ አስቡ።

ይህም ማለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ አሮጌው ሰው በክርስቶስ ውስጥ እንደሞተ ስለሚናገራቸው እውነቶች አምናችሁ በዚህ ነፃነት ውስጥ ለመኖር ፈልጉ። (ሮሜ 6፡11) የሆናችሁትን እውነት መኖራችሁ ያንን እውነት ለመሆናችሁ ማረጋገጫ ነው። የሆናችሁትን እውነት ስለመሆን የሚገልጽ አንድ ክፍል በ 1 ቆሮንቶስ 5፡7 ለይ በግልጽ ተጽፏል። እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ትንሽ ግር የሚል ሃሳብ ነው። ነገር ግን ደኅንነት ግር የሚል ግን ደግሞ የሚደንቅ ነገር ነው። የኃጢያት እርሾ ስለተወገደላችሁ የኃጢያትን እርሾ አስወግዱ። ይህንን እውነት ወስዳችሁ ኃጢያቴ አንዴ ስለነጻልኝ ኃጢያትን መዋጋት የለብኝም የሚል አመክንዮአዊ ጨዋታ ብትጫወቱ ከነጹት ወገን እንዳልሆናችሁ ብቻ ነው ማረጋገጫ የሚሆነው። 

3. ከኃጢያት ጋር ያላችሁን ጠላትነት አስወግዱ! ወዳጃችሁን አትገድሉም

(ሮሜ 8፡13) የምትገድሉት ጠላትን ነው። ኃጢያት ጓደኛችሁን ኢየሱስን እንዴት እንደገደለው አስቡ፣ አባትህን እንዴት እንደማያስከብር አስብ፤ እናም እንዴት ለዘላለም ሊያጠፋህ እንደሚችል አስብ።

4. በኃጢያት አመፃ ላይ አምፁ። በኃጢያት ውሸት እና ማጭበርበሮች ላለመሸበር እንቢ በሉ።

"እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ።" (ሮሜ 6፡12) የኃጢያት ፈተና ግማሽ እውነት ግማሽ ውሸት ነው። ጳውሎስ ፍሬአቸውን የሚያታልል ምኞት ይለዋል (ኤፌሶን 4፡22)

5. በሌላ እጅ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፍጹም ታማኝነትን አውጁ። ሙሉ አዕምሮአችሁን ልባችሁን እና ሥጋችሁን ለጽድቅ እና ንፅህና ታቀርቡ ዘንድ አስቡ።

ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። (ሮሜ 6፡13)

6. ለኃጢያት በር ሊከፍት የሚችል ማንኛውንም ነገር አታቅዱ።

ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ (ሮሜ 13፡14) ንጽህናችሁን በመፈተን ለማረጋገጥ አትሞክሩ።

7. የዘመኑን መንፈስ ለይታችሁ እወቁ፤ እናም እርሱን ላለመምሰል ተቃወሙት (ሮሜ 12፡2)።

ዲ. ኤል. ሙዲ እንደሚለው፣ መርከብ ቦታው በ ውሃው አለም ነው፤ ነገር ግን ውሃው ወደ ውስጡ ከገባ ይሰጥማል።

8. እግዚአብሔር-ተኮር ወደመሆን የሚያመጡ የልብ መታደስ ልምምዶችን አሳድጉ

(ሮሜ 12፡2፤ 2 ቆሮንቶስ 4፡16)። በየዕለቱ በላይ ላለው (ቆላስይስ 3፡2) የመንፈስ ፍቃድ (ሮሜ 8፡5) ላይ ትኩረታችሁን አድርጉ። ልባችሁ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን (ፊሊጲስዩስ 4፡8) እነዚህን ያስብ።

9. በየቀኑ ኃጢያታችሁን አምናችሁ ተናዘዙ

(1 ዮሐንስ 1፡9) እግዚአብሔርም ይቅር እንዲላችሁ ይቅርታ ጠይቁት (ማቴዎስ 6፡12)

10. በዚህ ሁሉ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን እርዳታና ሃይል ጠይቁ።

በመንፈስ የሥጋን ስራ ግደሉ (ሮሜ 8፡13)። በውስጣችን ያለ ማንኛውም መልካም ነገር የመንፈስ ፍሬ ነው (ገላትያ 5፡22)። እንደሚገባን እንድንሄድ የሚያደርገን እርሱ ነው (ሕዝቅኤል 36፡27፤ ኢሳያስ 26፡12)

11. የኃጢያትን ሽንገላ እንድትጠነቀቁ የሚያሳስቧችሁ ትልቅ እና አናሳ ሕብረቶች ውስጥ ተቀላቀሉ።

(ዕብራውያን 3፡13) በእምነት ጸንቶ መቆም የህብረት ሥራ ነው። እግዚአብሄር ያስቀመጠውን እርስ በእርስ የማጽናናትና የመመካከሪያ መንገድ ችላ ብንል ወደ መንግሥተ ሰማይ እንደርሳለን ብሎ ለማለት ምንም ዋስትና የለንም። 

12. ቦክሰኛ ተጋጣሚውን እንደሚፋለም ማራቶን ሯጭም ድካምን እንደሚፋለም የኃጢያት ፍላጎታችሁን በሙሉ አቅማችሁ ተፈለሙት።

(1 ቆሮ 9፡27 ፤ 2 ጢሞቴዎስ 4፡8)።

13. የህግን ሥራ (ገላትያ 3፡2፤5) ተጠንቀቁ። ውጊያችሁ ሁሉ በእምነት ሥራ (2 ተሰሎንቄ 1፤11) ይሁን።

ይህም ማለት ከኃጢያት ጋር ያላችሁ ውጊያ እግዚአብሔር በክርስቶስ ለእናንተ እንዲሆኑ ቃል በገባቸው የላቁ ደስታዎች ላይ ባላችሁ መተማመን ይሁን።  

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %AM, %11 %009 %2016 %02:%Dec
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

ጳውሎስ ነፍሰ ገዳይ እንዲሆን እግዚአብሔር ለምን ፈቀደለት

ጳውሎስ ገና ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔር ለሐዋርያነት እንደለየው እናውቃለን። “ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

ከሮሜ 8:35 ውስጥ ልንማራቸው የምንችለው ሦስት ነገሮች

ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? (ሮሜ 8፡35) ...

Jonathan Parnell - avatar Jonathan Parnell

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.