Saturday, 04 February 2023

ጣፋጭ ወይንስ መራር ቅድስና?

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ጄሪድ ዊልሰን በ አንድ መጽሐፉ ላይ ሲጽፍ “ቅድስና እንድታጉረመርሙ ካደረጋችሁ እያደረጋችሁት ያለው ነገር ልክ አይደለም” ይላል። 

ዊልሰን የተናገረው ነገር ስል እና ጠንካራ ነው።ግን ለምን? በመታዘዝ እና በደስታ መሃከል ያለው መሠረታዊ ግንኙነት ምንድን ነው? 

ስለዚህ የሚናገር አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በ 1 ዮሐንስ 5፡3-4 ላይ አለ፡-

"ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።"

ጆን ፓይፐር በመጨረሻ ህያው ሆንኩ (Finally Alive) በሚለው መጽሐፉ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ሦስት ተያያዥ ሀሳቦችን ያሳያል፡-

የመጀመሪያው ተያያዥ ሀሳብ:- “ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ሸክም ባልሆነ መንፈስ ለትዕዛዛቱ በምናደርገው ታዛዥነት ይገለጻል።”

ሁለተኛው ተያያዥ ሀሳብ:- “ለእዚህ እሺታ ታዛዥነት መሠረቱ ዓለምን ለማሸነፍ አቅም የሚሆነን የአዲስ ውልደት ኃይል ነው።”

ሦስተኛው ተያያዥ ሀሳብ:- “ዓለምን የሚያሸንፈው ኃጢያትን የሚሰብረውና የእግዚአብሔርን ፍቃድ ውብ እንጂ ሸክም እንዳይሆንብን የሚያደርገው እምነታችን ነው።” 

ወንጌል ፣ አዲስ ውልደት ፣ እምነት እና በደስታ መታዘዝ አንድ ላይ የሚመጡት እዚህ ጋር ነው። ፓይፐር ተያያዥ ሀሳቦቹን እንደዚህ አያይዞ ያስቀምጣቸዋል ፡- 

አዲሱ ውልደት ሕያው ከሆነው ከእግዚአብሀሔር ቃል ወንጌል ጋር ስንገናኝ የሚፈጠር ነው። የአዲስ ልደት የመጀመሪው ውጤት እግዚአብሔርን እና ልጁን ሥራውን እና ፍቃዱን እንደ ታላቅ ውበት እና ዋጋ እንዳለው ነገር ማየት እና መቀበል ነው። ይሄ እምነት ነው። ይሄ እምነት ዓለምን ያሸንፋል። ማለትም ዓለም ታላቅ ሀብት እንድትሆንብን የሚያደርገውን የባርነት ሀይል ያሸንፋል።

እምነት የሚያብለጨልጨውን የዓለምን የባርነት መተብተቢያ ይሰብራል። በዚህ መንገድ እምነት በነፃነት እና በደስታ ወደመታዘዝ ይመራናል። እግዚአብሔር እና ቅዱሱ ውብ እንጂ ሸክም አይሆኑብንም። አዲሱ ልደት የዓይኖቻችንን መሸፈኛ አንስቷል። አሁን የነገሮችን እውነተኛ ማንነት ማየት እንችላለን። በደስታ ለመታዘዝ አሁን ነፃ ነን።

ስለዚህ ነው የቅድስናችን ትግል ጣፋጭ እንጂ መራር ፍለጋ ያልሆነው። ለዓለም መብለጭለጮች ባሮች መሆናችን በክርስቶስ ተሰብሯል። ሥሉስ የሆነው አምላክ በእምነት ታላቅ መዝገባችን ሆኗል። ደስተኞች ሆነን ለመታዘዝ ነፃ ነን። 

የቅድስናችን ትግል ጣፋጭ እንጂ መራር ፍለጋ ። ለዓለም መብለጭለጮች ባሮች መሆናችን በክርስቶስ ተሰብሯል።

ነገር ግን ስለቅድስናችን ያለን ሩጫ እንድናጉረመርም ካደረገን በትክክል እያደረግነው አይደለም። ምክንያቱም የዚህ ዓለም ማታለል ከብቦን የቅድስናን ምንነት ግራ እንዲገባን ስላደረገን ነው። ወይንም ደግሞ ዓለም ከወደፊት ደስታ ይልቅ አሁኑኑ በኃጢያት መርካት እንደሚሻል እንድናምን ስላምትፈልግ ነው።

ስጋችን ደካማ ስለሆነ ኃጢያታችንን እየተናዘዝን የወንጌልን ጸጋ በሕይወታችን ላይ እንለማመዳለን (1 ዮሐንስ 1፡8-10)። ነገር ግን በምንወድቅበት ጊዜ እንኳ ዳግም የተወለዱ የእግዚአብሔር ልጆች ተነስተው ከዚህ ዓለም ማታለል አሻግረው ይመለከቱና የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከማር ይልቅ ለዳነው ምላሳቸው ጣፋጭ እንደሆነ እና ደስታ ለዘላለም ወደሚፈስበት ቤታቸው (መዝሙር 16፡11) እየወሰዳቸው እንደሆነ በማመን በእምነት ይራመዳሉ።

ደስታ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ ፓስተር ጆን ይጽፋል። “እጃችንን እየቆረጥን የምንፋለምበት አይነት አሳሳቢ ጉዳይ" (ማቴዎስ 5፡30) ያለንን ሁሉ የሚያሸጠን (ማቴዎስ 13፡44) ደግሞም በቀራንዮ ከኢየሱስ ጋር መስቀል ተሸክመን የምንሄድበት ነው(ማቴዎስ 10፡38-39)። ጠባሳዎች አሉት። የደስታን መዝሙሮችን ከእንባ ጋር ይዘምራል። ያለፉትን ጨለማ ጊዜያት ያስታውሳል። የበለጠም እንደሚመጣ ያውቃል። ወደ መንግስተ ሰማይ የሚወስደው መንገድ በእርግጥ አስቸጋሪ መንገድ ነው ግን ደስታ የሌለበት አይደለም።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %888 %2016 %23:%Dec
Tony Reinke

Tony Reinke is a staff writer for Desiring God and the author of three books: 12 Ways Your Phone Is Changing You (2017), Newton on the Christian Life: To Live Is Christ (2015), and Lit! A Christian Guide to Reading Books (2011). He hosts the popular Ask Pastor John podcast, and lives in the Twin Cities with his wife and three children.

twitter.com/TonyReinke

የእግዚአብሔር ፍቅር ቀድሞ እና አሁን

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል (ሮሜ 5፡8)።

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች እና ሥነ መለኮታዊ ትምህርቶችን የማስተማ…

ለመኖር ብቸኛው ምክንያት ትልቅ ስፍራ የሰጣችሁትን ነገር ማሳካት ነው። ማንኛውም ሰው ትልቅ ዋጋ ባለው ነገር ፈንታ ላነሰ ነገር ሲል መቼም ቢሆን ዋጋ መክፈል ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.