Tuesday, 22 October 2024

የእግዚአብሔር ልጆች ኃይል እና ልዩ መብት

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ስለግል የፀሎት ጊዜያችሁ መለስ ብላችሁ የምታዩበት እና በመጪዎቹ ቀናት አንድ ወይንም ሁለት ነገሮችን ለማስተካከል የምታልሙበት ጊዜ አሁን ነው። በተለምዶ ለማደግ እና ረዘም ያለ መንገድን ለማቅናት የተሻለ የሚባለው አማራጭ አጠቃላይ እድሳት ሳይሆን አንድ ወይንም ሁለት የተወሰኑ ችግሮችን ለይቶ ማውጣቱ ነው።

ምናልባት የፀሎት ሕይወታችሁ ብዙ ክርስቲያን ነኝ እንደሚሉ ሰዎች ጥቂት ከሚባል አንስቶ የለም የምንለው አይነት ይሆንና ከባዶ መጀመር ሊኖርባችሁ ይችላል። ምንአልባት ፍራንሲስ ቻን “ለዚህ ትውልድ የሚያሳስበኝ ነገር ቢኖር ምንም ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ አለመቻላችሁ ነው ፤ ከምንም በላይ ደግሞ ፀሎት ላይ።” ያለው ስጋት እየሆነባችሁ ሊሆን ይችላል። እናም ለመቀየር ዝግጁ ልትሆኑ ትችላላችሁ።

እራሳቸሁን ለመፈተሽ አሊያም እንደጀማሪ ለመማር የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ ጥቂት ተግባራዊ ምክሮችን ስለግል ፀሎት ላካፍላችሁ እወዳለሁ። መጀመሪያ ግን “የግል ጸሎት” ወይንም “የእልፍኝ ጸሎት” የምንለው ለምን አስፈላጊ አንደሆነ እንነጋገር።

ምናልባት የፀሎት ሕይወታችሁ ብዙ ክርስቲያን ነኝ እንደሚሉ ሰዎች ጥቂት ከሚባል አንስቶ የለም የምንለው አይነት ይሆንና ከባዶ መጀመር ሊኖርባችሁ ይችላል። ምንአልባት ፍራንሲስ ቻን “ለዚህ ትውልድ የሚያሳስበኝ ነገር ቢኖር ምንም ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ አለመቻላችሁ ነው ፤ ከምንም በላይ ደግሞ ፀሎት ላይ።” ያለው ስጋት እየሆነባችሁ ሊሆን ይችላል። እናም ለመቀየር ዝግጁ ልትሆኑ ትችላላችሁ

“በእልፍኝ ገብቶ” መጸለይ 

የእልፍኝ ፀሎት ስሙን ያገኘው በብዙዎች ዘንድ ከሚታወቀ በማቴዎስ ወንጌል 5 እስከ 8 ላይ ባለው የተራራው ስብከት ከሚባለው ስብከት ላይ ነው። የኢየሱስ ትዕዛዝ አውዱ ሰዎች እንዲያዩን ብለን ጽድቅን በሰው ፊት ስላለመፈጸም ነው (ማቴዎስ 6፡1)።

"ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።" (ማቴዎስ 6፡5-6)

በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የአይሁድ እምነት ዙሪያ ሌሎች እንዲሰሙን መጸለይ የራሱ ዋጋ እንደነበረው አሁንም በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቤተክርስቲያን ማሕበረሰብ ዙሪያ በጉባዔ መካከል ይሁን በአነስተኛ ቡድኖች አልያም ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ባለ ፀሎት ተመሳሳይ ዋጋ አለው። ጸሎትን በማስረዘም ፣ ድምጽን በመቀየር ፣ የተወሳሰቡ ቃላትን እና ርዕሶችን በመምረጥ ሰውኛ ሰሚዎቻችን ላይ ብቻ የተለየ ውጤት ለማምጣት ሰዎችን ለመማረክ ባለ ተነሳሽነት ወደሚደረግ  ስህተት ልንገባ እንችላለን። 

በእርግጥ ውጥረት ያለበት መንገድ ነው። ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ሆነ ቤት ውስጥ አሊያም በሌላ ቦታዎች በጋራ መጸለያችን አስፈላጊ ነው። የጋራ ፀሎት ደግሞ ሰሚዎችንም ያማከለ መሆን አለበት። አደጋው ግን ያለው እግዚአብሔርን ወደ ጎን ትተን ትኩረታችንን የሚስብ ሆኖ ለመታየት ስናደርገው ነው።

አሁንም በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቤተክርስቲያን ማሕበረሰብ ዙሪያ በጉባዔ መካከል ይሁን በአነስተኛ ቡድኖች አልያም ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ባለ ፀሎት ተመሳሳይ ዋጋ አለው። ጸሎትን በማስረዘም ፣ ድምጽን በመቀየር ፣ የተወሳሰቡ ቃላትን እና ርዕሶችን በመምረጥ ሰውኛ ሰሚዎቻችን ላይ ብቻ የተለየ ውጤት ለማምጣት ሰዎችን ለመማረክ ባለ ተነሳሽነት ወደሚደረግ  ስህተት ልንገባ እንችላለን።

ለእውነተኛነት ምርመራ  

የእልፍኝ ፀሎት ለጋራ ጸሎታችን መመርመሪያ ይሰጣል። ቲም ኬለር በ ማቴዎስ 6፡5-6 ላይ ማብራሪያ ሲሰጥ፡- 

"ለመንፈሳዊ ሀቀኝነታችን የማይሳሳት መመርመሪያ ኢየሱስ እንዳለው የግል የፀሎት ሕይወታችን ነው። ብዙዎች ማሕበራዊ ወይንም ባህላዊ ተፅዕኖ ሲደርስባቸው አልያም በተለያዩ ሁኔታዎች ምክንያት ጭንቀት ሲመጣባቸው ብቻ ይጸልያሉ። ከእግዚአብሔር ጋር እንደአባት እውነተኛ ግንኙነት ያላቸው ግን ከውጪ የሚጫናቸው ነገር ባይኖር እንኳን መጸለይን ከውስጣቸው ይፈልጋሉ። መንፈሳዊ ድርቀት ላይ እንኳን ቢሆኑ ምንም ማሕበራዊ ጥቅማ ጥቅም ባያገኙበት አጥብቀው ግን ይፈልጉታል።"

ፀሎት እውነተኛዎች ሆነን እንደሆነ መመርመሪያ ነው።

ላለመብቃታችን መድኃኒት

ነገር ግን የግል ጸሎታችን ለእውነተኛነታችን መመርመሪያ ብቻ ሳይሆን ብዙውን ጊዜ ለሚሰማን ለእግዚአብሔር ያለን የፍላጎት ማጣት እና አለመብቃት መድኃኒት ነው። ጆን ፓይፐር እንደሚለው “ፀሎት የልባችንን ትክክለኛ መሻት የሚገልጽ የልባችን መለኪያ ብቻ አይደለም ነገር ግን እግዚአብሔርን እንደሚገባን መፈለግ ሳንችል በምንቀርባቸው ጊዜያት ምትክ የማናገኝለት የልባችን መድኃኒት ነው።

ፀሎት በመንፈሳዊ ሕይወታችን ማን እንደሆንን በግልጽ ያሳያል፤ እራሳችንንም ተሰብረን ፣ ተቸግረን ፣ አጥተን ወይንም አመፀኛ ሆነን በምናገኝባቸው ቦታዎች ፈውስ ይሆንልናል። 

የግንኙነታችን አውድ 

ቲም ኬለር እንደተናገረው ፀሎት “ከእግዚአብሔር ጋር እንደ አባታችን ለምናደርገው ግንኙነት” አስፈላጊ ነው። የፀሎት ማዕከሉ እኛ ከእግዚአብሔር እንድናገኝ ሳይሆን እግዚአብሔርን እራሱን ማግኘት ነው። ፀሎት እግዚአብሔር በቃሉ ለሰጠን ድምፅ ምላሽ በመስጠት የምንናገርበትና ለጸሎታችን መልስ የማግኛ መንገድ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን እንደመጨረሻው ነገር አድርገን የምንደሰትበት እና የምንለማመድበት ነገር ነው። በፀሎት ውስጥ እግዚአብሔር ጆሮዎቹን ወደ እኛ የሚያዘነብልበት እና ባሮች ብቻ ሳንሆን ወዳጆች እንደሆንን (ዮሐንስ 15፡15) የምናውቅበት ታላቅ ስጦታ ነው። ቃሉን የምንሰማ ብቻ ሳንሆን የእርሱ ልብ ያለን ልጆቹ ነን (ሮሜ 8፡15-16፤ ገላትያ 4፡6-7)። ከእኛ መስማት ይፈልጋል። ይሄ ነው የፀሎት ኃይል እና ልዩ መብት። 

እዚህ ጋር ኢየሱስ ስለ እልፍኝ ፀሎት የሰበከውን ለምን በሚገባ እንደተገበረው እናያለን። እርሱ መድኃኒት የሚያስፈልገው ብቃት ማጣት አልነበረውም ስለ እውነተኛነቱም እንዲሁ። ነገር ግን ከአባቱ ጋር ሕብረት ማድረግ ይፈልግ ነበር። ስለዚህም በተደጋጋሚ ለብቻው ይጸልይ ነበር።

"ሕዝቡንም አሰናብቶ ይጸልይ ዘንድ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። በመሸም ጊዜ ብቻውን በዚያ ነበረ።" (ማቴዎስ 14፡23 ፤ ማርቆስ 6፡46) አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም ነገር ግን በተደጋጋሚ “ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር” (ሉቃስ 5፡16)። ከማለዳ ወይም ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ (ማርቆስ 1፡:35)። 

አስራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ከመምረጡ በፊት “ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ” (ሉቃስ 6፡12)። በጌቴሰማኒ እንኳን ሦስት ጊዜ እየሄደ ይጸልይ ነበር (ማቴዎስ 26፡36 ፣ 42 ፣ 44፤ ማርቆስ 14፡32-42)። አገልግሎቱን ከጀመረበት ቀን አንስቶ እስከተሰጠበት ቀን ዋዜማ ከአባቱ ጋር ላለው ግንኙነት የግል ፀሎት ልምምዱን ወሳኝ ክፍል አድርጎት ነበር።

ስለዚህ የግል ጸሎት በብዙ መልኩ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ማን እንደሆንን መለኪያ መንገድ ነው። ጄ. አይ. ፓከር እንደሚለው “እንዴት እንጸልይ የሚለው ሊገጥሙን ከሚችሉ ጥያቄዎች  ውስጥ ዋነኛው ነው።


የፀሎት ማዕከሉ እኛ ከእግዚአብሔር እንድናገኝ ሳይሆን እግዚአብሔርን እራሱን ማግኘት ነው።


ለግል ፀሎት የሚሆኑ አምስት ምክሮች

የግል ፀሎት ለክርስቲያን ጠቃሚ ደግሞም አስፈላጊ እንደሆነ ግልጽ ነው። የግል ጸሎታችንን የምናደርግበት መንገድ ግን ልምምዶቻችን እና ድግግሞቻችን ክፍት ነው። የእራሳችሁን ልምምድ በምትፈትሹበት ወይንም በምትጀምሩበት ጊዜ የግል ጸሎታችሁን ሊያበለጽጉላችሁ የሚችሉ አምስት ምክሮች።


1. የእራሳችሁን እልፍኝ አዘጋጁ

ዘወትር ልትጸልዩበት የምትችሉት የግል ቦታ አዘጋጁ። የተዘጋጀ ቦታ ማግኘት ካልቻላችሁ እራሳችሁ አዘጋጁ። ቀለል ያለ ዴስክ ወይንም የምትንበረከኩበት ቦታ ሊሆን ይችላል። ብዙዎች በአልጋቸው ውስጥ ሆነው ከመጸለይ ይልቅ ወርደው መጸለይ ፍሬያማ እንደሆነ አረጋግጠዋል። የግል የፀሎት ቦታን ማግኘት የግል ጸሎታችሁን ዘወትር እንድታረጉት መሄድ ያለባችሁ ቦታ እንዳለ እንዲሰማችሁ ያደርጋል።


2. በመጽሐፍ ቅዱስ ጀምሩ

ፀሎት እኛ የምንጀምረው ንግግር ሳይሆን እግዚአብሔር መነሳሳቱን ወስዶ በቃሉ የተናገረን ስለሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመር እንዳለብን ብዙዎቻችን ከሙለር ተምረናል። ሙለር ሲናገር ለአስር አመታት ዕለቱን በረጅም ፀሎት ይጀምር ነበር። ነገር ግን በጊዜ ቆይታ እንደተረዳው ለእግዚአብሔር ቃል ምላሽ በመስጠት ሲጀምር ጸሎቶቹ ትኩረት እና ክብደት የነበራቸው ሆኑ።

ከዚያን ጊዜ በኋላ ሙለር ቃሉን ማንብብ እንዲችል እግዚአብሔር እንዲረዳው በአጭር ፀሎት ይጀምርና ወዲያው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ይሄድ እና በቃሉ ውስጥ ጆሮውን ለእግዚአብሔር ክፍት ያደርጋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በማሰላሰል ይቀጥልና ወደግል ጸሎቱ ይሻገራል።


3. አድንቁ ፣ ተናዘዙ ፣ አመስግኑ ፣ ጠይቁ 

መጽሐፍ ቅዱስን ካነበብን እና ካሰላሰልን በኋላ ወደ ክፍት ፀሎት (በውስጣችን የሚሰማንን ሁሉ ማሰማት) ከመግባታችን በፊት መልክ ያለው ነገር መኖሩ ሊጠቅመን ይችላል። 

ማርቲን ሉተር ክርስቶሰ ባስተማረን ፀሎት መዋቅር በየዕለቱ እንደ አዲስ በትኩስ ቃላቶች ልንጸልየው እንደሚገባ ይመክራል። በጊዜ ውስጥ የነጠረ የተለመደ አንድ መዋቅር ማድነቅ ፣ መናዘዝ ፣ ማመስገን እና ልመና ነው። መጀመሪያ በእግዚአብሔር ቃል ስለተገለጠላችሁ እዉነት እግዚአብሔርን አደናንቁት፤ አመስግኑት። ቀጥላችሁ ኃጢያታችሁን ፣ መተላለፋችሁን እና ድካማችሁን ተናዘዙ። ከዛም ስለ ጸጋው እና ስለ ምህረቱ እግዚአብሔርን አመስግኑት። በመጨረሻም ስለእራሳችሁ ቢሆን ስለ ቤተሰባችሁ፣ አልያም ስለ ቤተክርስቲያናችሁ፣ ስለብዙ ነገሮች ልመናን አቅርቡ።


4. መሻቶቻችሁን ግለጧቸውና አሳድጓቸው።

ክፍት ፀሎት የልባችንን እና በዛን ቀን ወይንም ወቅት የከበደንን እና ያስጨነቀንን አውጥተን የምንጸልይበት ነው። በግል ፀሎት ጊዜያችን ለእግዚአብሔርም ሆነ ለእራሳችን ሃቀኞች ነን። ልባችሁን ለእግዚአብሔር ግለፁለት። አስቀድሞ ያውቀዋል፤ ከእናንተ ሊሰማውም ይፈልጋል። ይህ በቃላት ሊገለፅ የማይችል እድል ነው።

ፀሎት ግን ልባችንን የምንገልጥበት ቦታ ብቻ አይደለም መሻታችንንም የምናሳድግበት ቦታ ጭምር እንጂ። ኃይል አለ። ፀሎት ደግሞ ምንም ነገር ሊያደርገው ከሚችለው በላይ ልባችንን ይቀይራል። በተለይ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉትን እንደ መዝሙረ ዳዊት እና መልዕክቶች (እንደ ኤፌሶን 1፡17-21፤ 3፡16-19፤ ፊሊጵስዩስ 1፡9-11፤ ቆላስይስ 1፡9-12) እና ሌሎችንም ተከትለን ስንጸልይ መሻታችንን በመቅረፅ እና በእግዚአብሔር ፊት ለመግለፅ ድጋፍ በመሆን ይቀይሩናል። 


5. ትኩስ ይሁን 

በአዲስ ዓመት ወይንም በአዲስ ወር ወይንም በሕይወታችሁ አዲስ ወቅት ላይ ቀይሩት። በየጊዜው ወይንም አልፎ አልፎ ጸሎቶችን በጥንቃቄ እና በትኩረት ጻፉ ። ወይንም የፀሎት ፍቅራችሁን በጾም ሳሉት። ወይንም ከሕይወታችሁ ቀውስ ራቅ ብላችሁ በፀጥታ ለብቻችሁ ገዜ ውሰዱ።

እንደ ግል ፀሎት ኃይል እና ዕድል ሙሉ ትኩረታችንን ሊወስዱ የሚገባቸው ነገሮች በጣም ጥቂት ናቸው።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %869 %2016 %22:%Dec
David Mathis

David Mathis is executive editor for desiringGod.org, pastor at Cities Church in Minneapolis/Saint Paul, and adjunct professor for Bethlehem College & Seminary. He is author of Habits of Grace: Enjoying Jesus through the Spiritual Disciplines.

https://twitter.com/davidcmathis

እግዚአብሔር ህዝቡን የሚመራባቸው አራት መንገዶች

እግዚአብሔር ህዝቡን በፍቃዱ ውስጥ ሊመራባቸው የሚችላቸው ቢያንስ አራት መንገዶች ይታዩኛል።

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

ምስጋና ለመስጠት 32 ምክንያቶች

እንግሊዛዊው ፓስተር እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ማቲው ሄነሪ (1662-1714) ከመሞቱ 2 ዓመት በፊት ስለ ጸሎት መጽሐፍ ጽፎ ነበር። ለጸሎት የሚሆን መንገድ...

Donny Friederichsen - avatar Donny Friederichsen

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.