Tuesday, 22 October 2024

የምንሰራበት ዋነኛው ምክንያት

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ማብሰል ስላልፈለጋችሁ ውጪ ወጥቶ መብላት ይሁን ወይንም የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያለማቋረጥ ማየት ቢሆን፣ ወይንም ሥራ ትቶ የማሕበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ማፍጠጥ፤ አሊያም ሥራን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ቢሆን ሁላችንም ስንፍናን በእራሳችን መንገድ እናውቀዋለን።

ያገባችሁ ከሆናችሁ ምንአልባት እንደ ማጽዳት፣ ምግብ ማብሰል ፣ እና ልጆችን ማሳደግ የመሳሰሉትን መሠረታዊ ኃላፊነቶችን እየዘነጋችሁ ሊሆን ይችላል። ተማሪዎች ከሆናችሁ ደግሞ ለማለፍ ለሚያስፈልገው ብቻ እየሰራችሁ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎ ሰነፍ ሰዎች ጊዜ የለኝም በሚል ሰበብ የዕለቱን ዋና ሥራ የሆኑትን መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብን እና መጸለይን ይዘነጋሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ለሰነፉ ሰው ታካች የሚል ስም አለው። ታካች ሰው ንቁ ያልሆነ ቀኑን ሙሉ መተኛት የሚፈልግ ሰው ነው። ታካች ሰው ለሥራ መነቃቃት የለውም ጥረት ለማድረግም አቅም የለውም፤ አስፈላጊ እንደሆነም አያምንምም። እናም ይህ ታካች ለመስራት መነቃቃትን እስካላገኘ ድረስ ለተፈጠረበት ነገር ተራ ጥላ ነው የሚሆነው። ታካች ሰው ደካማ ወላጅ፣ ደካማ የትዳር አጋር፣ ሰነፍ ተማሪ፣ ሰነፍ ሠራተኛ እና መጥፎ ጓደኛ ነው።

ለአንዳንዶች ሥራ በሕይወት የመቆያ መንገድ ነው የሚልን ውሸት ከመቀበላቸው ምክነንያት ሊመነጭ ይችላል። መንገድ ላይ አንድን ሰው የሥራ ትርጉሙ ምንድን ነው ብላችሁ ብትጠይቁት በሕይወት የመቆያ መንገድ እና ለሚያስፈልገው ነገር የአቅርቦት ምንጭ እንደሆነ ይነግራችኋል። የሚመችን ቤት ፣ ጥሩ መኪና እንደ ምግብ እና ልብስ ላሉ የየዕለት አስፈላጊ ነገሮች ማግኛ መንገድ ነው ይላችኋል። ሥራን በእዚህ መልኩ ስናየው ለመሥራታችን ምክንያት በተሳሳተ አቅጣጫ ይሄድ እና የምናደርገው ሁሉ የተበላሸ ይሆናል። ያለ ስፍራው ያለውን የሥራ ምክንያታችንን ለመቀለስ የሥራ ሥነ መለኮት ያስፈልገናል።

ለሥራ የተሠራን

ብዙዎች የሥራ ሥነ መለኮት ስለሌላቸው ሥራ ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ የመጣ እንደሆነ ያስባሉ። እግዚአብሔር ግን ሰው ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዲሠራ አስቦ ነው የፈጠረው። የምንሠራው የሠራን ሠራተኛ ስለሆነ ነው። የሰሠራንም በመልኩ ስለሆነ እርሱን እናንጸባርቃለን። እንደ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት አገላለጽ “እግዚአብሔር እርሱ እራሱ እንደሚሠራ ሰዎችም ሥራ የመሥራት ግዴታ እንዲኖራቸው ሥራን በትርጉም እና መለኮታዊ ዋጋ ሞልቶታል።”

በዘፍጥረት 2፡15 ላይ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔደን ገነት አኖረው።” ይሄ ሰው ከመውደቁ በፊት ፤ ኃጢያት ከመግባቱ በፊት ስለነበር ሰው ፍጹም በሆነ ዓለም ውስጥ እንኳን ሳይቀር እንደሚሰራ ያሳየናል። ሥራ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እንጂ እርግማን አይደለም። ይሁን እንጂ ስለ ሥራ ያለን አመለካከት ከውድቀት የመነጨ ሊሆን ይችላል። ኃጢያት ስለስራ ያለንን አመለካከት አቆሽሾታል። ስለዚህ እንደ ስጦታ ከማየት ይልቅ በሕይወት ለመቆየት የምናደርገው ቅጣት እንደሆነብን ልናስብ እንችላለን።

ሥራ እንደ መርገም የሚታይ ከሆነ ዓላማችን ያለ ሥራ መኖር የምንችልበት ዓለም መፍጠር ይሆናል። ነገር ግን ሥራ ልብስ ፣ ምግብ እና መጠለያ የማሟያ መንገድ ብቻ ሳይሆን ከዛም የዘለለ ነው። ኬን ማቲውስ ዘፍጥረት 2፡15 ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጠው፡-

የሜሶጶጣሚያ የፍጥረት አመጣጥ ጽሁፎች ውስጥ የሰው ልጆች ለሥራ እንደተፈጠሩ ያሳያል። የዚያን ጊዜ ግን የሚሰሩት ለስግብግብ አምላኮቻቸው ምግብን ለማሟላት ነው። በማያቋርጠው ልፋታቸው ላይ የአማልክቱ ጭንቀት የሚረካው ሠራተኛ በሆኑ የሰው ልጆች ፍጥረት ነበር። በተቃራኒው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የሰው ልጆች ለሚያስፈልጋቸው ነገር የሚያሟለው እግዚአብሔር እንደሆነ እና አንዱም መንገድ ደግሞ መሬትን ማረስ ነው። ሕይወት ያለሥራ ብትሆን የስው ልጆች አስፈላጊ አይሆኑም ነበር።

የሚያስፈልገንን ሁሉ የሚያሟላልን እግዚአብሔር ስለሆነ የምንሰራበት ምክንያት እና ስለ ሥራ ያለን አረዳድ መቀየር አለበት። ይሄ የተከበረ ትርጉም ያለው ልፋት እንደ አምልኮ የሚደረግ ነው። ለሰው ሳይሆን ለጌታ።

ለጌታ መሥራት

ሐዋሪያው ጳውሎስ በ ቆላስይስ 3፡23-24 ላይ እንዲህ እያለ ይጽፋል “ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና። የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነው።” ጳውሎስ ለባሮች ቢሆንም ለሁሉም ክርስቲያኖች ግን በያለንበት ጥሪ ይመለከተናል።

ስንሠራ “በቅን ልብ ጌታን እየፈራን እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምናሰኝ ለታይታ የምንገዛ እንዳንሆን” (ቆላስይስ 3፡22) መጽሐፍ ቅዱስ ያዘናል። ለሰዎች ለመታየት መሥራቱ ክፋቱ ምኑ ላይ ነው?

ሰው ውሱን ፍጥረት ነው። ውሱን ፍጥረት ደግሞ ውሱን የሆነን ነገር ብቻ ነው ሊያይ የሚችለው። የምናደርገውን የምናደርገው ሰዎች ሲያዩ ብቻ መሆኑ ልክ የማይሆነው በማያዩን ጊዜ አቋራጮችን ስለምንጠቀም ነው። በተጨማሪም ሰውን ለማስደሰት መሥራት ለእግዚአብሔር ይገባን የነበረን ክብር ለራሳችንን እየፈለግን እንደሆነ ልባችንን ይገልጻል። ሥራችን እኛን ሳይሆን አባታችንን ነው ሊያሳይ የሚገባው። የእግዚአብሔርን ክብር በተጋፋን በማንኛውም ጊዜ ለሰዎች አመለካከት ባሪያ ስለምንሆን የእራሳችንን ደስታ ነው የምንጋፋው።

ጳውሎስ ስለዚህ የምናደርገውን ሁሉ “ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንድናደርግ” (ቆላስይስ 3፡23) ያበረታታናል ። ይህም ማለት ለስራ ያለን መነሳሳት በአባታችን ባህሪ እና ተዕዛዝ ላይ የተመሠረተ ነው። ምስሉ ስላለብን የምንሠራው እርሱ ስለሚሠራ ነው።እንደ አባታችን መሆን እንፈልጋለን። በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ እንድንሰራ ያዝዘናል። እንደ አባታችን ትዕዛዙ ለእኛ መልካም እንደሆነ እናምናለን፤ እንደ ሠራተኞቹ ደግሞ እውነተኛ እና መልካም የሆነውን ጌታችንን ለማስደሰት እንሠራለን። ግን እንዴት? የምንሠራው እንዲቀበለን ወይንም ፍላጎቱን ለማሟላት አይደለም (ይሄ ስም ማጉደፍ ነው የሚሆነው)። ነገር ግን የምንሠራው ስለተቀበለን የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት ነው።

የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ አለቃችን ምንም አይነት ባህሪ ያለው ሰው ቢሆን የሥራ ጥራታችንን እናሻሽላለን። ቅን አለቃ ቢኖረንም ባይኖረንም መልካሙን የሰማይ አባታችንን ግን ለማስደሰት ጠንክረን በደስታ እንሠራለን።

የዚህ አይነቱ መረዳት የቅርብ አለቃ እንኳን ሳይኖረን እንዴት እንደምንሠራ ይቀይራል። በቤት ውስጥ ደግሞ በትጋት እቃ ምናጥበው ፣ ቤት የምናጸዳው ፣ ምግብ የምናበስለው እና ጓሮውን የምናጸዳው እንደ አባታችን ባህሪ እና ትዕዛዝ ስለምንሠራ ነው። የምንሠራው ለአንድ ተመልካች ነው።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %848 %2016 %22:%Dec
Phillip Holmes

Phillip Holmes served as a content strategist at desiringGod.org. He’s married to Jasmine. They have a son.

https://twitter.com/phillipmholmes

አንቀፅ 17፣ ነፃነት/ባርነት — ከአድዋ - ጎልጎታ

ይህ ታሪክ ከተፈፀመ እነሆ በዛሬዉ 122ኛ ዓመቱን ይዟል። ይህ ቀን ለአሁኗ ኢትዮጵያ ማንነቷን ያስጠበቀችበት፣ ከባርነት ራሷን ነፃ ያደረገችበት ቀን ነው። ከመ...

Misgana Kibret - avatar Misgana Kibret

ጨርሰው ያንብቡ

እኛን ስለ ማጽደቅ ተነሣ!

“ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።” ሮሜ 4፡24-...

Ligonier Ministries - avatar Ligonier Ministries

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.