Friday, 22 January 2021

እኛን ስለ ማጽደቅ ተነሣ!

Posted On %AM, %16 %218 %2017 %07:%Apr Written by

“ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።” ሮሜ 4፡24-25

ጳውሎስ ጥልቅ የሆነ የግሪክ እውቀቱን በመጠቀም እንዲሁም አብርሃምን ምሳሌ በማድረግ፣ የራሳችንን መልካም ሥራ ተጠቅመን በጌታ ፊት ጻድቅ ሆነን ልንቆም እንደማንችል በማያሻማ መልኩ ይነግረናል። ከሁሉ ይልቃል የምንለው ሥራችን እንኳን ሳይቀር በኃጢያት የጎደፈ ነው። በምትኩ ግን በፊቱ ጻድቅ ተደርገን ተቆጥረናል፤ ጸድቀንማል። ይህም የሆነው በእምነት ብቻ ነው። እኛም ልክ እንደ አብርሃም የህግን ሥራ በመፈጸም ሳይሆን የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሎች በማመን እንጸድቃለን። ለዚህም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በ ዘፍጥረት 15፡6 ላይ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት የሚሉት ቃላት ለእኛም እንደተጻፉ የሚያስቀምጠው (ሮሜ 4፡21-23)። ጳውሎስ በግልጽ አስቀምጦታል፤ እኛም ሆንን ከሙሴ ሕግ መሰጠት በፊት ወይም በኋላ የኖሩ አማኞች በጌታ ፊት ጻድቅ ተብለው የተቆጠሩት በማመናችን ብቻ ወደእኛ ሊተላለፍ በቻለው በክርስቶስ ፍጹም ጽድቅ አማካኝነት ነው።

ሮሜ 4፡24-25 ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው በእርሱ ለሚያምኑ እምነታቸው ጽድቅ ተደርጎ እንደሚቆጠርላቸው አጽንዖት በመስጠት ይህንን ሀሳብ ደግሞ ያጸናል። ሐዋርያው እዚህ ጋር የክርስቲያን እምነት ፍሬ ነገር ምን እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጥልናል። እኛም የምናምነው አብርሃም ያመነውን አምላክ ነው። እኛም ልክ እንደአብርሃም እግዚአብሔር የገባውን የተስፋ ቃል ሊፈጽም እንደሚችል ደግሞም እንደሚፈጽም ድፍረት አለን። እግዚአብሔር ለእኛ እና ለአብርሃም የገባው የተስፋ ቃል ተመሳሳይ ሆኖ ሳለ እኛ ግን የእነዚህን የተስፋ ቃሎች መፈጸም አባቶች ባላዩት መልኩ አይተናል። አብርሃም በምሳሌ እና በጥላ ብቻ ያውቀው የነበረ እኛ ግን ወደ ኋላ መለስ ብለን በግልጽ ልናየው የምንችለው በኢየሱስ ሞት እና ትንሣኤ ውስጥ ያሉ የጌታ ቃላት ተጨማሪ ማስረገጫ ሆነው አሉን። ዛሬ ላይ ሆንን ስለ መጽደቅ ማመን እግዚአብሔር ክርስቶስን “ስለ በደላችን አሳልፎ እንደሰጠውና እኛን ስለ ማጽደቅም እንዳስነሣው” ማመን ነው፡ ፡

የመጨረሻው ዐረፍተ ነገር ያዘለው ሥነ መለኮታዊ ክብደት ፈጽሞ ሊያልፈን አይገባም። በመጀመሪያ፣ የማስተሰረይ ሥራውን በዋነኝነት ሲከውን የነበረው ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር አብም እንደሆነ እናያለን። ስለ ኃጢያተኞች ሲል እግዚአብሔር ወልድ በፍቃዱ እራሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ። ነገር ግን አብም እንዲሁ አንድያ ልጁን ሰጠ። ወልድ በኃጢያት ላይ የወጣውን መለኮታዊ እርግማን ሲሸከም እግዚአብሔር ከእራሱ ጋር ግጭት ውስጥ አልነበረም፤ ለእግዚአብሔር ሕዝብ እርቅ ይሆንለት ዘንድ አብ እና ወልድ ሁለቱም ወልድን ለመለኮታዊ ፍርድ ሸክም አሳልፈው ሰጡ።

ፈጣሪያችን በተጨማሪም “እኛን ስለማጽደቅ” ክርስቶስን አስነሣው። ኢየሱስ እንደሞተ ቢቀር እስካሁን ድረስ በኃጢያታችን እንዳለን እንሆን ነበር (1 ቆሮንቶስ 15፡17)። ሞቱ ከማንኛው ሰው ሞት በተለየ ምልኩ ትርጉም ያለው ሊሆን አይችልም ነበር። ሞት ሥልጣን ያለው በኃጢያተኞች ላይ ብቻ ነውና ኢየሱስ እንደሞተ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ ኃጢያተኛ እንደሆነ ያመላክት ነበር ስለዚህም ስለእኛ ሊያስተሰርይ አይቻለውም ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ፍጹም ጻድቅ ስለነበር ሞት ሊይዘው አልቻለም (የሐዋርያት ሥራ 2፡24)።

ማርቲን ሉተር በሮሜ መልዕክት ላይ በሚያስተምርበት ጊዜ ስለ መድኃኒታችን ሞት እና ትንሣኤ ሲያትት “የክርስቶስ ሞት የኃጢያትን መወገድ በበቂ ሁኔታ ማርካት እንደሚችል ያመላከተ ብቻ ሰይሆን በእርግጥም ያከናወነ ነበር” ሲል ይናገራል። ከክርስቶስ ትንሣኤ የተነሳ ኃጢያታችን ሙሉ በሙሉ ደግሞም እንዳያዳግም ተደርጎ እንደተሰረየልን ድፍረት እንዲኖረን እንችላለን። ለኃጢያት ለመክፈል ልንሠራው የቀረልን ምንም ነገር የለም። በኢየሱስ ካመንን ለዘላለም በደሙ ተሸፍነናል።

ለተጨማሪ ጥናት የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች

ኢሳይያስ 53፡10-12

ዕብራውያን 9፡24-28

1 ጴጥሮስ 3፡18-22

1 ዮሐንስ 4፡9-10 


Originally posted on Ligonier Ministries, Translated by Joshua Terefe,  

Last modified on %PM, %06 %800 %2017 %21:%May
Ligonier Ministries

Ligonier Ministries is a Reformed international Christian organization headquartered in the greater Orlando, Florida area. It was founded by R. C. Sproul in the Ligonier Valley, Pennsylvania outside of Pittsburgh in 1970.

www.ligonier.org/

ምስጋና ለመስጠት 32 ምክንያቶች

እንግሊዛዊው ፓስተር እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ማቲው ሄነሪ (1662-1714) ከመሞቱ 2 ዓመት በፊት ስለ ጸሎት መጽሐፍ ጽፎ ነበር። ለጸሎት የሚሆን መንገድ...

Donny Friederichsen - avatar Donny Friederichsen

ጨርሰው ያንብቡ

የክርስቶስ ጠባሳዎች

“እጆቼን እና እግሮቼን ተመልከቱ፡እኔው ራሴ ነኝ ደግሞም ንኩኝ እና እዩ ይህንንም ብሎ እጆቹን እና እግሮቹን አሳያቸው” ሉቃ 24፡39 ...

Genaye Eshetu - avatar Genaye Eshetu

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.