እርግጥ ነው እንደ ጥሩ ክርስቲያኖች ኢየሱስን እንላለን ። ጥሩው ገጸ ባህሪ እርሱ ነው ። ታሪኩን ስናስታውስ ከጠላቶቹ ሁሉ ነጥቀን ልንጎትተው እንዘረጋለን ። እንደሸጠው ይሁዳ ፣ እንደካደው ጴጥሮስ ፣ እንደሚጠሉት ሊቀ ካህናት ፣ የሚያላግጥበት ሄሮድስ ፣ ስቀለው እያለ የሚጮህ ህዝብ ፣ እጁን ታጥቦ እንደፈረደበት ጲላጦስ እና ወንጀለኛ ሲሆን ግን ነፃ እንደተለቀቀው በርባን ያሉ ብዙ ጠላቶቹ ።
እስቲ አንዴ ቆዩማ ።
ወንጀለኛ ሲሆን ግን በነፃ የተለቀቀው በርባን!
ሉቃስ በ23ኛው ምዕራፉ እኛን ኃጢያተኞች በጥንቃቄ ባስቀመጠው ትረካ ውሰጥ ከበርባን ጋር እንድንተዋወቅ ይመራናል ። የኢየሱስ ፍርድ ከእያንዳንዱ ነገድ ፣ ቋንቋ ፣ ህዝብ እና ሀገራት ብዙ መንፈሳዊ እስረኞች እንዲለቀቁ እንዳደረገ የሞት ፍርዱም የበርባንን አካላዊ መለቀቅ አድርጓል።
በቁጥር 15 ላይ ሉቃስ ጲላጦስ “ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም” ያለውን ጠቅሶ የኢየሱስን ንፁህ መሆን ያሳየናል ። በቁጥር 19 ላይ ደግሞ በርባንን ጥፋተኛ እንደሆነ “ሁከትን በከተማ አንሥቶ ሰውን ስለ ገደለ በወኅኒ ታስሮ የነበር” ሰው በማለት ያስረዳል ።
በቁጥር 22 ላይ ህዝቡ የኢየሱስን መሰቀል ለሦስተኛ ጊዜ ከጠየቁ በኋላ ሉቃስ የኢየሱስን ንጹህ መሆን በድጋሚ ጲላጦስ “ምን ነው? ያደረገውስ ክፋት ምንድር ነው? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም” ያለውን በመጥቀስ ያረጋግጥልናል ። ህዝቡን ግን ስላላሳመናቸው የኢየሱስን ሞት አጥብቀው ጠየቁ፤ ከተአምርም በላይ ተአምር የሆነው ግን በእርሱ ምትክ ወንጀለኛ ተብሎ የተደነገገውን በርባንን ነፃ እንዲሆን መልቀቃቸው ነው ።
“ስለዚህ ጲላጦስ ያንን የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው” (ቁጥር 25) ። የመጀመሪያው የመስቀሉ ልውውጥ ይኸውላችሁ ። ንፁሁ ኢየሱስ ወንጀለኛ ተብሎ ሲፈረድበት ወንጀለኛውን በርባን ግን እንደንፁህ ሰው ለቀቁት ።
ዛሬም ቢሆን ንፁሁ ኢየሱስ በፍቃዱ በተደረገ ልውውጥ እንደ እኛ ያሉ በርባኖች ነፃ እንወጣለን ።
ንፁሁ ኢየሱስ በፍቃዱ በተደረገ ልውውጥ እንደ እኛ ያሉ በርባኖች ነፃ እንወጣለን ።
Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe