Saturday, 04 February 2023

ልንኖርበት የምንችልበት ተስፋ

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ” (ኢሳይያስ 41፡10)።

ለአስቸጋሪ ሥራዎች እጆቼን ለማበርታት ደጋግሜ የተጠቀምኩበት እንደዚህ ያለ ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ አይመስለኝም። አዕምሮዬ ውስጥ የሚስተጋባው ድምጽ ይህ ነው። ከማንኛውም ጥቅስ በላይ ለብዙ አስርት ዓመታት አገልግሎኛል። ግር የሚሉ ቦታዎች ጋር ስሄድ ፣ አዲስ ቋንቋ ስናገር ፣ የዶክትሬት ትምህርት ፈተናዬን ስወስድ ፣ ለሥራ ቃለ መጠይቅ ሲኖርብኝ ፣ ለብዙ ሕዝብ ስሰብክ ፣ ለካንሰር በሽታ ቀዶ ሕክምና ሲደረግልኝ ፣ ደስ የማይሉ ስልክ ጥሪዎችን ሳደርግ እና ይቅርታ ልጠይቅ ስል አበርትቶኛል።

ይሄን ክፍል ጠቃሚ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ስለ እግዚአብሔር በሦስተኛ መደብ (እርሱ ያበረታሀል ይረዳሃል…) ሳይሆን በአንደኛ መደብ (አበረታሃለሁ ፣ እረዳሃለሁ… ) ስለሚናገር ነው። ሁልጊዜ ስለው ለእራሴ በቀጥታ ሲናገረኝ ይሰማኛል። ይህ በሚደንቅ ሁኔታ ኃይል አለው። ከአጠገቤ ሆኖ “ሂድ፤ የምታደርገውን አድርግ እኔ እረዳሀለሁ። አቅምን እሰጥሃለሁ። እደግፍሃለሁ።” እንደሚል አይነት ይሰማኛል። 

ሌላ ጠቃሚ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ ሁሉንም ሊያጠቃልል መቻሉ ነው። “እረዳሃለሁ” ለማንኛውም ሁኔታ ሊሆን ይችላል። ሁልጊዜ ደግሞ እርዳታ ያስፈልገኛል። ስለዚህ ይህ ተስፋ ሁልጊዜ ለሁኔታዎቻችን ሁሉ የሚመጥን ነው፤ ላያስፈልገን የሚችልበት ሁኔታ የለም። 


ይሄን ክፍል ጠቃሚ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ስለ እግዚአብሔር በሦስተኛ መደብ (እርሱ ያበረታሀል ይረዳሃል…) ሳይሆን በአንደኛ መደብ (አበረታሃለሁ ፣ እረዳሃለሁ… ) ስለሚናገር ነው። ሁልጊዜ ስለው ለእራሴ በቀጥታ ሲናገረኝ ይሰማኛል። ይህ በሚደንቅ ሁኔታ ኃይል አለው። ከአጠገቤ ሆኖ “ሂድ፤ የምታደርገውን አድርግ እኔ እረዳሀለሁ። አቅምን እሰጥሃለሁ። እደግፍሃለሁ።” እንደሚል አይነት ይሰማኛል። 


ሌላኛው ጠቃሚ ምክንያት ደግሞ በእግዚአብሔር የጽድቅ ባህሪው ክፍሉን ስለሚዘጋው ነው። የእግዚአብሔር ጽድቅ ክብሩን ለማምጣት የሚያደርገው ጠንካራ መሰጠት ነው። ከዛ መንገድ ተዛንፎ አያውቅም። ስለዚህ የስሙ ክብር አደጋ ላይ ባለበት በሚመስል ቦታ ሁሉ በቅንዓት እንደሚገለጥ እርግጥ ነው። ለእምነታችንም ዋስትናው ይህ ነው። በጣም ብዙ መቶዎች ጊዜ አግዞኛል።

በመጨረሻም ይህ ክፍል ጠቃሚ የሚሆነው ምንም እንኳን ለአይሁዶች የታቀደ ቢሆንም ለእኔ ለአሕዛቡም ስለሚሰራ ነው። ይህም የሚሆንበት ምክንያት እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በ መሲሁ ኢየሱስ ናቸውና (2 ቆሮንቶስ 1፡20)። ይህም ማለት በወንጌል ምክንያት የእኔ ነው። በእርሱ ለሆኑት ሁሉ ይህ ተስፋ እውነት እንዲሆን ክርስቶስ ሞቷል። በማመኔ ምክንያት በእርሱ ነኝ። ስለዚህ ይህንን ተስፋ ጨምሮ ሌሎች ሁሉም ተስፋዎች የእኔ ናቸው። ለሞተው ደግሞም ለተነሳው ልጁ ታማኝ እንደነበረ ለዚህም ተስፋ የታመነ ይሆናል። የዚህን ያህል እርግጥ ነው።

የእኛ እግዚአብሔር፤ ባለፈ ቀን ረዳታችን 

ለመጪው ዘመን ተስፋችን

ከኃይለኛው ወጀብ መጠለያ

የዘላለም ቤታችን ማረፊያ

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %25 %858 %2016 %22:%Dec
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ

ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል! ክፍል ሁለት - የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ በቀደመው ክፍል ላይ ‘ፖርኖግራፊ’ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከ...

Ermias Kiros - avatar Ermias Kiros

ጨርሰው ያንብቡ

የሚያበረቱ 10 የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናት የምናሳልፈው ጊዜ ውድ እና ያልባከነ ጊዜ ነው። ረጃጅም ክፍሎችን እያጠናችሁ ቢሆን ወይንም ለአንድ ኃጢያት የሚሆን የውጊያ ጥቅስ አ...

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.