Monday, 15 July 2024

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች እና ሥነ መለኮታዊ ትምህርቶችን የማስተማር ዓላማ እና ተግዳሮቶች እንዲሁም ለዚህ የሚያበቋችሁ የግል ባህሪዎች

Posted On %AM, %28 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ለመኖር ብቸኛው ምክንያት ትልቅ ስፍራ የሰጣችሁትን ነገር ማሳካት ነው። ማንኛውም ሰው ትልቅ ዋጋ ባለው ነገር ፈንታ ላነሰ ነገር ሲል መቼም ቢሆን ዋጋ መክፈል የለበትም። ትልቅ ዋጋ የምትሰጡት ነገር ምን እንደሆነ ለመወሰን መጣር አለባችሁ። ይሄ ካልሆነ ግን የሥራ ዓይነትን (ወይንም ሌላ ማንኛው ነገርን) ለመምረጥ ምንም ጠቃሚ እርምጃ ወደፊት መራመድ አትችሉም።

ከሁሉ የሚልቅ ዋጋ

ለእኔ ትልቅ ዋጋ ብዬ የያዝኩት እግዚአብሔር ሲከብር ማየት ነው። ይህንን ዋጋ እንዳይ እግዚአብሔር ያደረገበት መንገድ በማስተማር ውስጥ ነው። ስለዚህ በማስተማር ውስጥ ግብ ያደረኩት በተማሪዎች ላይ እግዚአብሔርን ለሚያከብር ትምህርታዊ ተቋም የሚሆን ተመጣጣኝ ችሎታን በውስጣቸው መፍጠር ነው። የማስተምርበት ክልል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የእግዚአብሔር ክብር በግልጽ እና በቀጥተኛነት የሚገለጥበት ሥፍራ ስለሆነ ሥራዬ ተማሪዎቹ በግልጽ ጅማሬ ችሎታ ውስጥ ደግሞም ከዛ ባሻገር ምን እንዳለ እንዲያዩ እንዲረዱ እና እንዲያደንቁ ደግሞም የፍቅርን ትክክለኛ ምላሽ ምንነት እንዲያውቁ ማስተማር ነው። ይህን በማድረጌ ተማሪዎቹ በተሻለ አጥርተው ማየት ስለሚችሉ ፣ በተሻለ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ስለሚረዱ እና የእግዚአብሔርን ክብር በተሻለ በጥልቀት ስለሚወዱ ዋጋ የሰጠሁትን ነገር አሳካለሁ። እንደዚህ ላለው አገልግሎት ቢያንስ የኔን አስተሳሰብ ለሚጋሩ ሽልማቱ እንደኔ አመለካከት ግልጽ ነው ባይ ነኝ።

እንደ አንድ አስተማሪ የሚታግሉኝ ከባድ ነገሮች የዐይኖቼ ለመታወር ማዘንበል አዕምሮዬም ታካች ለመሆን ማዘንበል እንዲሁም ልቤም ድንዙዝ ለመሆን ማዘንበላቸው ነው። በሌላ አገላለጽ ከባዱ ፈተና በራሴ አተያይ ፣ አስተሳሰብ እና ስሜት ተማሪዎቼ እንዲሆኑ የምፈልገውን መቅረጽ ነው። አንድ አባባል እንደሚለው “መላመድ መናቅን ይወልዳል”። ዘወትር ለውበት የቀረብን መሆናችን ደንዛዛ እና ላለው ኃይልም ዕውር እንድትሆኑ ሊያደርጋችሁ ይችላል። ዐይኖቻችንን የመክፈትም ሆነ የመዝጋት ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ጋር በመሆኑ ከልብ የመነጨ ቋሚ ጸሎት በትምህርቴ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነው።  

ታዲያ አስተማሪ ለመሆን ብቁ የሚያደርጓችሁ የግል ባህሪዎች ምንድን ናቸው?

• ማስረዳት ላይ በጣም ጎበዝ መሆን አለባችሁ። አንድን የተወሳሰበ ሀሳብ ወስዳችሁ ያለ ምንም ረዳት በተደራጀ አገላለጽ በማስቀመጥ ሀሳቡ ላልገባው አንድ ሰው ግልጽ ልታደርጉለት ትችላላችሁ? (በቡድኖች ውስጥ ሳላችሁ ለአዲስ መጪዎች አንድን ሀሳብ ለማስረዳት ምትመርጡት እናንተ ናችሁ?) በአስተሳሰብ የመጠቁ ሰዎች አንድን ሀሳብ ለመረዳት ሌላው ተራ ሰው እንደሚያደርገው ደረጃ በደረጃ የሆነ አመክንዮአዊ የሀሳብ አመሠራረት ስለሌላቸው ፤ ነገር ግን ወደ መረዳታቸው በፍጥነት ስለሚደርሱ ለማስተማር ጎበዝ አይሆኑም።

• ማሰብ ስላለው ትልቅ ዋጋ ማመን አለባችሁ። የሌሎችን አስተሳሰብ በመቅረጽ እና በማሰብ ያሳለፍነው ጊዜ ሁሉ የባከነ ህይወት እንዳልሆነ ልትረዱ ያስፈልጋል። ሃሳቦች ያላቸውን ዋጋ እና ህይወት የመቀይር ኃይልን ልታምኑ ያስፈልጋል። ይህ እምነት ከሌላችሁ ተራ “የትምህርት ጨዋታ” ትቀጥላላችሁ።

•ሥነ መለኮታዊ ጥያቄዎች በኖሩ ጊዜ እነዚህን ለመፍታት ከውስጥ የሚመነጭ ፍላጎት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል። በሚያነበው ወይንም በሚያደምጠው ነገር ውስጥ በሚያገኛቸው የሀሳብ ተቃርኖዎች ወይንም ግጭቶች አሊያም ጥልቀት የሌላቸው ትርጉሞች የሚረብሸው ሰው ልትሆኑ ያስፈልጋል። በሌላ አገላለጽ ወደ ምርመራ ጥሩ ዝንባሌ ሊኖራችሁ ያስፈልጋል። ለምን? እና እንዴት? የሚሉት ቃላት ወሳኝ ቃሎቻችሁ ሊሆኑ ያስፈልጋል። ነገር ግን የ3 ዓመት ህፃናት እንደሚያደርጉት ጥያቄ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን መልስም ለማግኘት መፈለግ አለባችሁ።  

• ወደ ሰዎች ባህሪ በጥልቀት የማየት ችሎታ ያስፈልጋችኋል። ይህ ባህሪ እንዳላችሁ ሊለካበት ከሚችልበት መንገድ አንዱ እራሳችሁን በምታውቁበት መጠን ነው። ጥሩ አስተማሪ እራሱን ለመፈተሽ በበቂ ሁኔታ ስለሚሰጥ ምን ግፊት እንደሚያሳድርበት ስለራሱ ጠንቅቆ ይረዳል። ሰዎች ምን ግፊት ሊያሳድርባቸው እንደሚችል ማወቅ የማስተማሪያ መንገዳችሁም ላይ ሆነ እንደ አስተማሪ ያላችሁ ኃይል ላይ ታላቅ ተጽኖን ያምጣል።

• በመጨረሻም በቀን ከ 10 እስከ 14 ሰዓት ቁጭ ብሎ ለማሰብ እና ለመጻፍ የሚሆን ሥነ ስርዓት ያስፈልጋችኋል።

ማጠቃለያ

• የማስተማር ትልቁ ተግዳሮት የማስተምረው ትምህርት ሀሳብ ኃልዎት የሆነውን የእግዚአብሔር ክብር ተማሪዎቼ አጥርተው እንዲያዩት ፣ በጥልቀት እንዲረዱት እና እንዲሰማቸው ማድረጉ ላይ ነው።

• ትልቁ ተግዳሮት ደግሞ በየዕለቱ ለሚገጥመኝ ድንቅ ክብር የእራሴን ዐይኖቼ መክፈት ፣ አዕምሮዬን በሥርዓት ማስገዛት እና ልቤም ክፍት እንዲሆን ማድረግ ነው።

የጥሩ አስተማሪ ባህሪዎች:-

ማስረዳት ላይ በጣም ጎበዝ መሆን አለባችሁ።

ማሰብ ስላለው ትልቅ ዋጋ ማመን አለባችሁ።

ሥነ መለኮታዊ ጥያቄዎችን የመፍታት ፍላጎት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል

ወደ ሰዎች ባህሪ በጥልቀት የማየት ችሎታ ያስፈልጋችኋል።

ሥነ ስርዓት ያስፈልጋችኋል።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %790 %2016 %20:%Dec
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

ኢየሱስ ያድናል

“የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” (ሉቃስ 19፡10) ክርስትና “ኢየሱስ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” በሚሉት ቃላት ሊጠቃለል ይች...

Jonathan Parnell - avatar Jonathan Parnell

ጨርሰው ያንብቡ

የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን? ነ…

ከአድካሚ የስራ ቀን በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያዬ እየሔድኩ ሳለሁ በውስጤ ብዙ ሃሳብ  ይመላለስ ነበር። ተስፋ የላቸውም ብዬ የምቆጥራቸው ነገሮች ሲበዙ ከፈረሰው...

Yodit Fantahun - avatar Yodit Fantahun

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.