Monday, 15 July 2024

በደስታ መምራት

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

አንድ የማልረሳው የሽማግሌዎች ስብሰባ ነበር።

ከመጋቢ አገልግሎት ጋር ስለሚመጡ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች አንድ በአሜሪካ ውስጥ ያለ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን መጋቢ ከተናገረበት የመሪዎች ኮንፈረንስ እየተመለስኩ ነበር።

አገልግሎት መምራት በጣም ከባድ ሥራ እንደሆነ ተናገረ። አደጋዎቹ ዘላለማዊ ናቸው። ጠላታችን የ ክፋት ጣሪያ ነው። ኃይለኛ እና አታላይ ነው። ሰዎች እኛን አለመረዳት ውስጥ በቀላሉ ሊገቡ ይችላሉ። መልዕክታችንም በሁሉ ዘንድ የታወቀ አይደለም። ብዙዎቹ ሽልማቶቻችን ኋላ የሚጠብቁን ናቸው። ከምናገኘውም በላይ እንድንሰጥ እንጠየቃለን።

ከባድ በሚባል የአገልግሎት ጊዜ ውስጥ ስለነበርኩ ቃሉ በውስጤ አስተጋባ። በመዝሙር 73 ላይ እንዳው እንደ አሳፍ አገልግሎት የማያዋጣ ነገር እንደሆነ ማሰብ ጀምሬ ነበር።

በሚቀጥለው የሽማግሌዎች ስብሰባ ላይ የተናገረውን ለሌሎች ማካፈል ጀመርኩ። እንደ ፀሎት ጥሪ አድረጌ አቀረብሁት። እውነታው ግን ሰዎች እንዲያዝኑልኝ እና እንዲረዱኝ ነበር የምፈልገው። ነገር ግን ለእራሴ ከንፈር ወደመምጠጥ ከመዞሬ በፊት አንዱ የቦርድ አባል ዝም እንድል ነገረኝ።

እኔም ወዲያው ዝም አልኩ።

አያችሁ ይህ ሰው ጡረታ የወጣ ወታደር ነበር። ወደ ቬትናም 3 የጦር ጉዞዎችን አድርጓል። በወኔ ተዋግቶ ነበር የጦርነትንም አስፈሪ ጎን ተምሮ የመጣ ሰው ነው። ይባስ ብሎ ወደ ሀገሩ ሲመጣ ማፌዣ እና ማላገጫ ሆነ። ሀገሪቱ የጀብደኞች አቀባበል አልነበራትም። በአየር መንገድ ሳይቀር ተተፍቶበት ነበር።  

እኔን ለማስቆሙ ትክክል ነበር። ምን እያወራሁ እንደነበር አላውቅም ነበር። በአገልግሎት ውስጥ ስለሚገጥሙ ተግዳሮቶች እና ችግሮች የማውራት መብት የለኝም። እርግጥ ነው አገልግሎት የእራሱ የሆነ ተግዳሮቶች እና ከባድ ሁኔታዎች ይኖሩታል፤ ነገር ግን ቬትናም ለጦርነት መሄድ ጋር ሲነፃፀር በጣም ቀላል ስራ ነው። እውነታው ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ እያንዳንዱ የሥራ መደብ በችግር እና መከራ መተብተቡ ነው። አረም የሌለበት መናፈሻ የለም። 

ወዲያው ይቅርታ ጠየቅሁ። እርሱም ይቅርታዬን ተቀበለኝ።

የዚያን ቀን ወደቤት ስሄድ መቼም ቢሆን ስለሚገጥሙኝ ችግሮች እና ሸክሞች በሰዎች ፊት እንደ ትልቅ እድል ልናገራቸው እንጂ ላለማማረር ወሰንሁ። ለእራሴም “ማማረር የለም” የሚል ዘዬ አወጣሁ። የተመሠረተው እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እና መርሆች በማስታወስ ላይ ነው።

1. መሪነት ምርጫ ነው

እግዚአብሔር እያንዳንዱን አማኝ ወደ ደቀ መዝሙር ሕይወት እና የመንግስቱ አገልግሎት ጠርቷል። ነገር ግን መስመር የያዘ መሪነት ምርጫ ነው። ግዴታ እኔ መምራት የለብኝም። ማንም የለበትም። ምስጋና በተሞላ እና ደስተኛ በሆነ ልብ መምራት ካልቻልኩ እኔ ወርጄ ወይንም እረፍት ወስጄ ሌላ ሰው ስፍራውን መያዙ ለመንግስቱ የተሻለ ይሆናል። “በደስታ እንጂ በኃዘን አለማድረጋችን” (ዕብራውያን 13፡17) ጥቅሙ ለህዝባችን ነው።  

ይሁን እንጂ የሚገጥሙን ተግዳሮቶች ከባድ እንዳልሆኑ ማስመሰል አለብን ማለት አይደለም። ነገር ግን ጌታችን አሉታዊ በሆነ አስተሳሰብ ስናገለግለው በሚገባ አላገለገልነውም ማለታችን ነው።

ጳውሎስ የኤጲስ ቆጶስነትን መስፈርት ሲያስቀምጥ መሪ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ እንዲጠቀምበት ለጢሞቴዎስ ያዘዋል (1 ጢሞቴዎስ 3፡1-7)። ኢየሱስም ስለ አገልጋይ መሪነት ሲናገር ለሁሉም ሰው እንደሆነ አልነበረም። ታላቅ ወይም ፊተኛ መሆን ለሚፈልጉ ብቻ ነበር ያንን ያቀረበው (ማቴዎስ 20፡25-28)።

ይህንን አትርሱ በመሪነት ቦታ ሆኖ ማገልገል ምርጫ ነው ብዬ እስከማምን ድረስ ላማርር የምችልበት ምንም ምክንያት የለኝም። የመረጥሁት መንገድ ነው።

2. አገልጋይ መሪ መሆን ማለት እንደ አገልጋይ መቆጠር ነው

አገልጋይ መሪ የሚለው ሀሳብ ደስ ይለኛል። ነገር ግን ሰዎች እንደ አገልጋይ ሲያዩኝ ያ ሌላ ነገር ነው። ይሁን እንጂ ኢየሱስ እየቀለደ አልነበረም። እውነተኛ አገልጋይ መሪ ማለት እንደ አገልጋይ መቆጠር ነው። አባባል ሳይሆን እውነታ ነው። 

አገልጋዮቹ የሚያደርጉለትን ነገር የሚወድድ ጌታ በጣም ጥቂት ነው። እንደውም ብዙውን ጊዜ ጌታዎች አገልጋዮቻቸውን በይገባኛል ስሜት ነው የሚመሯቸው። ስለዚህ ከመንጋዎቼ መሀል ጌቶቼ እንደሆኑ የሚሰማቸው ቢኖሩ ፣ መሪነቴን ቢቃወሙ ወይንም የማደርገውን ነገር አቅለው ቢያዩት ሊገርመኝ አይገባም። አብሮት የሚመጣ ክልል አለ። እናም ልኖርበት እና ላገለግልበት የመረጥሁት ክልል ነው።


ስለዚህ ከመንጋዎቼ መሀል ጌቶቼ እንደሆኑ የሚሰማቸው ቢኖሩ ፣ መሪነቴን ቢቃወሙ ወይንም የማደርገውን ነገር አቅለው ቢያዩት ሊገርመኝ አይገባም። አብሮት የሚመጣ ክልል አለ። እናም ልኖርበት እና ላገለግልበት የመረጥሁት ክልል ነው።


3. ሽልማታችን እየመጣ ነው 

እንደ አትሌት አስቸጋሪዎቹን “የገሀነም ሳምንት”* የሚባሉትን አልወድዳቸውም ነበር። ቢቻለኝስ እዘልላቸው ነበር። ነገር ግን ከዓመት ዓመት በፍቃደኝነት እና በጉጉት ወደ እዚህ “የገሀነም ሳምንት” መሄድ ጀመርኩ። ምክንያቱም በጨዋታ ለተሞላ ወቅት መጀመሪያ ስለነበር ነው።

በተመሳሳይ ሁኔታ የአገልግሎት ክፍል የሆኑትን “የሲዖል ሳምነቶቼን” በነገው ተስፋ እንጂ በዛሬው ህመም ሳልፈርጃቸው ልቀበላቸው ተምሬአለሁ። ጌታዬ በፊቱ ስላለው ደስታ በመስቀል ታገሠ (ዕብራውያን 12፡2)። ጳውሎስ መከራዎቹን እና ስደቶቹን ከዘላለም ክብር ጋር ሲያነጻጽራቸው ቀላል ናቸው ይላል (2 ቆሮንቶስ 4፡17)። እናም መንጋቸውን በውዴታ እና በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን የሚጠብቁ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ይቀበላሉ (1 ጴጥሮስ 5፡1-4)።

4. መከራ ታላቅ እድል ነው

የመሪዎቹ ስብሰባ ላይ ስለመጋቢዎች ተግዳሮቶች በድንቅ ሁኔታ የገለጸው አስተማሪ በመጠኑም ቢሆን ልክ ነበር። አገልግሎት ብዙውን ጊዜ ከባድ ጥሪ ነው። ከመጠን በላይ የሆኑ ነገሮች አደጋ ውስጥ ናቸው። ልባቸው በቀላሉ ለሚዝል አይደለም። እነዚህ ተግዳሮቶች በትክክል ከተረዳናቸው የምናለቅስባቸው ጉዳዮች አይደሉም። ክብር ያለባቸው ነገሮች ናቸው። ለኢየሱስ መከራን መቀበል እርግማንን ተሸክሞ እንደመቻል ሳይሆን ልንኮራበት የሚገባን ክብር ነው። ይሄ የሚያመለክተው የሚገባቸው አድርጎ እንደቆጠረን ነው (ፊሊጲስዩስ 1፡27-30)


አገልግሎት ብዙውን ጊዜ ከባድ ጥሪ ነው። ከመጠን በላይ የሆኑ ነገሮች አደጋ ውስጥ ናቸው። ልባቸው በቀላሉ ለሚዝል አይደለም። እነዚህ ተግዳሮቶች በትክክል ከተረዳናቸው የምናለቅስባቸው ጉዳዮች አይደሉም። ክብር ያለባቸው ነገሮች ናቸው። ለኢየሱስ መከራን መቀበል እርግማንን ተሸክሞ እንደመቻል ሳይሆን ልንኮራበት የሚገባን ክብር ነው። ይሄ የሚያመለክተው የሚገባቸው አድርጎ እንደቆጠረን ነው (ፊሊጲስዩስ 1፡27-30)


የአገልግሎት መሪነታችን ደስታ የሌለው ሸክም ሲሆንብኝ በመንፈሳዊ ሕይወቴ ታላቅ ችግር እንዳለ ማሳያ ነው። በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መሪነት ሸክም አይደለም። ማንም ሊሰጠው የሚችል ታላቅ እድል ነው። ኢየሱስ ለኃጢያቴ መክፈሉ ከአዕምሮ በላይ የሆነ ነገር ነው። ልጁ እንድሆን ቀይሮኝ አብሬው የምወርስ እንድሆን ማድረጉ ላስበው ከምችለው ሁሉ በላይ ነው። ሙሽራውን በእንክብካቤ እንድመግብለት እኔን የመሰለውን ሰው ማመኑ ደግሞ ከመረዳት ሁሉ በላይ ነው።

ቢሆንም ግን አደረገው። ለዚህም ለእኛ ለማይገባን ከአዕምሮ በላይ ለሆነ ታላቅ እድል ብቸኛው መልስ በጨለማ የአገልግሎት ሸለቆዎች ውስጥ ሳይቀር ከልብ የሆነን ደስታ እና ምስጋና ማቅረብ ነው። ወይንም ሁሌ ማለት እንደምወድደው “ከእንግዲህ ወዲህ ማማረር የለም”።

*የገሃነም/የሲዖል ሳምንት ወይም Hell Week ማለት ለወታደሮች የሚሰጡ ከባድ ስልጠናዎች ናቸው።
 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %896 %2016 %23:%Dec
Larry Osborne

Larry Osborne Larry Osborne is senior and teaching pastor at North Coast Church in Vista, California. He is author of ten books, including Accidental Pharisees and Sticky Teams. His newest book is Thriving in Babylon: Why Hope, Humility, and Wisdom Matter.

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች እና ሥነ መለኮታዊ ትምህርቶችን የማስተማ…

ለመኖር ብቸኛው ምክንያት ትልቅ ስፍራ የሰጣችሁትን ነገር ማሳካት ነው። ማንኛውም ሰው ትልቅ ዋጋ ባለው ነገር ፈንታ ላነሰ ነገር ሲል መቼም ቢሆን ዋጋ መክፈል ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

የእግዚአብሔርን የጸጋ ግምጃ ቤት ክፈቱ

ያጣችሁት ነገር ላይ ዓይንን እንደመጣል እምነትን የሚያደክም ነገር የለም።  እንደተረዳሁት ከሆነ ዓይኖቼን በቁሳዊ ማጣቶቼ ላይ ፣ በሌሉኝ ጥንካሬዎች እና በሌ...

Jon Bloom - avatar Jon Bloom

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.